Postlar filtri


💬
❝የመጀመሪያው ነገር ለራስህ ሐቀኛ መሆን ነው። ራስህን ካልቀየርክ በኅብረተሰቡ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር አትችልም።❞
ኔልሰን ማንዴላ

💬
❝በሮችህን በዘጋጋህ፣ ክፍልህንም ባጨለምክ ጊዜ ከቶም ብቻዬን ነኝ ብለህ አታስብ። እግዚአብሔርና ታላቅነትህ አብረውህ ናቸውና ብቻህን አይደለህም። እነርሱ አንተ የምትሠራውን ነገር ለማየት ምን ብርሃን ያስፈልጋቸዋል?❞
ኤፒክቲተስ

💬
❝ትዕግስት የውጤታማነት አስኳል ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ጫን እያደረገ በር የሚያንኳኳ እንግዳ ከቤተኛው አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም።❞
ሄንሪ ዎድስዎርዝ ሎንግፌሎ

💬
❝ሌሎችን ድል የሚያደርግ በእርግጥ ጎበዝ ነው። በራሱ ላይ ድልን የሚቀዳጅ ግን በኃያልነቱ ከማንም ይልቃል።❞
ላኦ ትዙ

💬
❝በሕይወትህ ንጋት ሥራበት፤ በተሲዓቱ ምክር ስጥበት፤ ባመሻሹ ደግሞ ጸልይበት።❞
ሔዞይድ

💬
❝ራሱን ነፃ ማውጣት የጀመረ ማንኛውም ሕዝብ ለኢኮኖሚ ባርነት ለመዳረግ አንገቱን አያስገባም።❞
ክዋሜ ንክሩማህ

💬
❝ደህና አድርጎ ለሚኖር ሰው፣ ማንኛውም የሕይወት ዓይነት ተስማሚው ነው።❞
ሳሙኤል ጆንሰን

💬 💬


! ሁለት ዝንጀሮዎች። አንዱ ዕድለኛ ነው። ሁለተኛው ዕድለ ቢስ ነው። ሁልጊዜ ወደ ሙዝ እርሻው ሲሄዱ ዕድለኛው ዛፉ ላይ ወጥቶ ሙዝ እየቆረጠ ታች ወዳለው ዕድለ ቢስ ይወረውርለታል።

እንዲህ ሲሆን የሙዝ እርሻው ባለቤት ሌሎች ገበሬዎችን አስተባብሮ ታች ያለውን ዕድለቢስ ዝንጀሮ ይዘው በዱላ ይቀጠቅጡታል። ለብዙ ጊዜ ዕድለ ቢሱ ዝንጀሮ ሲደበደብ ከረመ።

ዕድለቢሱ ዝንጀሮ ሁልጊዜ መቀጥቀጡ ሰለቸውና "ዛሬ እኔ ከላይ ሆኜ ሙዙን ወደ ታች ልወርውርልህ" አለውና ቦታ ተቀያይረው ሙዝ መቁረጥ ጀመሩ።

ዝንጀሮዎቹን ያዩት ገበሬዎች ዱላ ይዘው ደረሱባቸው። በዚህን ጊዜ ገበሬዎቹ ታች ያለውን ዕድለኛውን ዝንጀሮ ይዘው ሊቀጠቅጡት ሲሉ የሙዙ ባለቤት እንዲህ አላቸው፣

"ይሄንን ዕድለ ቢስ ዝንጀሮ አትምቱት። ሁልጊዜ እንደቀጠቀጥነው ነው። ዛሬ ግን ከላይ የተሰቀለውን ዝንጀሮ አውርዱልኝ። ደህና አድርገን እንቀጥቅጠው"

! እኛ ዕድለ ቢሱ ዝንጀሮ ነን። ማንም ቢመጣ ያለርህራሄ ይቀጠቅጠናል። ቦታና ጊዜ ቢቀያየርም መቀጥቀጡ አይቀርልንም። ቀጥቃጩ ቢቀያየርም እኛ አንቀየርም። የዱላው ዓይነት ብዙ ነው ። የኑሮ ውድነት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የማያልቀው የታክስና ግብር አዋጅ፣ የማያልቀው መዋጮ ....... ዕድለ ቢስ ዝንጀሮ።


ከአንድ መንደር በላይ ካለ ተራራ ላይ እንዲት እንስት ንስር ጎጆዋን ቀልሳ እንቁላል ጥላለች። አንድ ቀን ታድያ አከባቢውን ከባድ የምድር መናወጥ ይንጠውና ከእንቁላሎቹ አንዱ በተራራው ቁልቁል ተንከባሎ እግርጌው ካለ የዶሮ እርሻ ውስጥ ይወድቃል።

ዶሮዎቹም ከራሳቸው እንቁላሎች እንደአንዱ ስላሰቡት እንቁላሎቻቸው ጋር ቀላቅለው ታቅፈውት  ይሰነብታሉ። ጊዜውም ሲደርስ  እንቁላሉ ይፈለፈል እና በጣም የተዋበ ንስር ይሆናል።

ዶሮዎቹ ከዶሮነት ሌላ ስለማያውቁ ንስሩን እንደ ዶሮ አድርገው ያሳድጉታል።

ንስሩ ቤቱን እና ቤተሰቡን ቢወድም ውስጡ ግን ከለመደው ነገር የሚበልጥ አቅም እንዳለው ይነግረው ነበር።

አንድ ቀን ከዶሮዎቹ መካከል ሆኖ ጥሬ እየለቀመ ሳለ ድንገት ወደላይ ቀና ሲል ታላላቅ ንስሮች አየሩን እየቀዘፉ ሲበሩ ያያል። ሳያስበውም ድምፁን አውጥቶ "አቤት ምናለ እኔም እንደነዚህ ንስሮች መብረር ብችል" ይላል።

ይህንን የሰሙት ዶሮዎች ሳቃቸውን መቆጣጠር እቅቷቸው፣ "ዶሮ መሆንህን ረሳኸው እንዴ? ዶሮ ከመቼ ወዲህ ነው የሚበረው?" እያሉ በተረብ አዋከቡት።

ንስሩ ግን ዘወትር በአይኑ እውነተኛ ቤተሰቡን መፈለጉን አላቆመም። አንዳንዴ እንዳውም እንደመንጠራራት እያለ ክንፎቹንም ይፈትን ነበር።

ነገር ግን ወደላይ ባንጋጠጠና ክንፎቹን ባራገበ ቁጥር ዶሮዎቹ የሚያወርዱበት ተረብ እየበዛበት ሲመጣ ዶሮ መሆኑን የበለጠ እያመነ መጣ። ከጊዜ በኋላም የመብረር ህልሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ እንደ ዶሮ ኖሮ ጊዜው ሲደርስ እንደዶሮ ሞተ።
------------------------------
የሰው ልጅ ሁሉ #ገደብ_የለሽ የሆነ- ፈጣሪ ሁሉንም ነገር መሥራት የሚችል ፍጡር አድርጎ የፈጠረው ሆኖ ሳለ ይህንን ኃይሉን ካጣበት ምክንያት አንዱ ልክ እንደ ንሥሩ ከአትችልም፣ አይሆንም፣ ትወድቃለህ፣ ... ወዘተ ከሚል ወይም ይህንን ካላስተማረ ማህበረሰብ ውስጥ ማደጉ ነው።

ይህ ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣው የልጅ አስተዳደግ ዘይቤያችን አስተሳሰባችን ላይም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል። ይህም ባህርያችንን ይቀርጻል።

ይህንን የበለጠ ለመረዳት እስከሆነ እድሜ ድረስ የነበረውን ልጅነታችንን አስቡ።

በጣም ነጻ፣ ደስተኞች፣ ደፋሮች፣ ጥሩዎችና ሁሉን ማድረግ የምንችል አይነት ስሜት የሚሰማን ነበርን። ነገር ግን እያደግን ስንመጣና የማህበረሰብ ሕጎችን እየተማርን ስንመጣ ፈሪዎች፣ ተጠራጣሪዎች፣ ንፉጎች፣ የተገደብን እና ነገሮችን እንደፈለግን ማድረግ የማንችል አይነት ስሜት እየተሰማን ይመጣል።

በእርግጥ አዕምሯችንና ሰውነታችን አደጋን በማስወገድ ሥራ ላይ የበለጠ ያመዝናል። በአብዛኛው ራስን ከአደጋ ለመከላከልና ውስብስብ ሥራዎችን በማስወገድ ሥራ ላይ ስለሚጠመድ 'ሪስክ' ለመውሰድ ችላ እንድንል ያደርገናል። ይህም የሆነበት ምክንያት አዕምሯችን እኛን ለመጠበቅ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው።

ይህ ከአስተዳደግ ጋር ተደማምሮ አዳዲስ ነገሮችን እንዳንሞክር፣ የውስጥ ተሰጥዖዎቻችንን በሚገባ እንዳናወጣ፣ ሙሉ አቅማችንን ተጠቅመን የተሻለ እንዳንሰራ እንቅፋት ይሆናል።

ሆኖም ግን ይህንን ሰብረው የወጡ ሰዎች ስኬታማ ሆነው እናገኛቸዋለን።

ስለሆነም ይህንን ለማስወገድና የተሻለ ውጤት ለማምጣት አዋዋልን ማሳመር፤ ራስን ለለውጥ ማዘጋጀት፤ የአስተሳሰብ ለውጥ ላይ የሚያተኩሩ ፅሁፎችን እና መፃሕፍትን ማንበብ፤ የተሻሉ ናቸው ከምንላቸው ሰዎች ጋር ማዘውተር፤ እንዲሁም ራስንና አካባቢን ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል።
        
------------------------------------------------------------------------------------------------------------------


TIKVAH-ETHIOPIA dan repost
ትውስታ ...

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?

በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።

ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።

በተለይ  ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።

በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ' ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ' ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።

ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ' አስራ አንድ ነው ! ' እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? "


ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።

" መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ?  ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? "

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች  የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

#AtoBulchaDemeksa

@tikvahethiopia


TIKVAH-ETHIOPIA dan repost
ትውስታ ...

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምን ይታወሳሉ ?

በኢህአዴግ ጊዜ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሀገራቸውን በሚመሩበት ወቅት ፓርላማ የነበሩት ጉምቱው ፖለቲከኛ እና የኢኮኖሚ ምሁር አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ጠንከር ያሉ ምሁራዊ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በማንሳት ይታወቃሉ።

ንግግራቸው ለዛ የነበረው ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ጨምሮ መላ የፓርላማ አባላትን ሳቅ በሳቅ የሚያድረግ ፤ ድፍረትና እውቀት የተሞላበት ነበር።

በተለይ  ደግሞ በኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ የዳበረ እውቀት ስለነበራቸው ሁሉም ሰው እሳቸው እድሉን አግኝተው እስኪናገሩ በጉጉት ነበር የሚጠብቀው።

በብዙዎች የሚታወሰው እና ሁሌም ተደጋግሞ የሚነሳው ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄና ፓርላማውን ሳቅ በሳቅ ያደረጉበት ንግግራቸው ነው።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ መንግስቱም ደጋግሞ ደጋግሞ ' ኢትዮጵያ በ110 ፣ በ111 አድጋለች ' ይላል ፤ እኔ ፣ እሳቸውም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶችም ያውቃሉ በ111 ማደግ ማለት ተአምር ነው። ይሄን ተአምር የሰራችው ቻይና እንደውም አሁን እየሰራች አይደለም ፣ ታይዋን ፣ ደቡብ ኮሪያ ናቸው።

ኢትዮጵያ እንዴት አድርጋ ነው በ111 ያደገቸው ? አንጎላ አሁን በ112 እያደገ ነው ለምንድነው በአንድ ጊዜ ብዙ ዘይት አገኙ፣ ዘይት ያገኙ ሰዎች ወይም ሌላ ነገር ያገኙ በ110 ወይም በ111 ቢያድጉ አይገርምም። 111 አደግን ብለን ለዓለምስ እንዴት አድርገን ነው የምንገልጸው ?

የዓለም የገንዘብ ድርጅት ኢትዮጵያ እና ሌሎች የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ቢበዛ በ106 ያድጋሉ ብሏል እኛ ግን እንቢ ብለን ' አስራ አንድ ነው ! ' እንላለን ይሄ ተገቢ ነው ? "


ሌላ በእጅጉ ከሚታወሱበት ንግግራቸው መካከል ደግሞ መንግሥት ስለሚሳተፍባቸው የተለያዩ ሽያጮች ጉዳይ ነው።

" መንግሥት ለምንድነው ማዳበሪያን የሚሸጠው ብቻውን ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ሆቴል ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ? ፤ መንግሥት ለምንድነው ቱሪዝም ውስጥ ገብቶ የሚነግደው ?  ፤ መንግሥት ለምንድነው ሲሚንቶ የሚሸጠው ? ፤ አልፎ ፍራፍሬ ሽንኩርት የሚሸጠው ለምንድነው ? መንግሥት ሶሻሊት ኢኮኖሚ አይደለም የሚያራምደው ? "

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በምዕራብ ወለጋ የተወለዱ ሲሆን በትላልቅ ዩኒቨርሲቲዎች  የተማሩ የተዋጣላቸው የኢኮኖሚ ምሁር ነበሩ። የአዋሽ ባንክ እንዲሁም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን (ኦፌኮ) መስራችም ነበሩ።

#AtoBulchaDemeksa

@tikvahethiopia


አንጋፋው ፖለቲከኛ እና የምጣኔ ሀብት ምሁሩ ቡልቻ ደመቅሳ ከእዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

በምዕራብ ወለጋ ዞን በቦጂ ብርመጂ ወረዳ በጊንቢ ዞን ከአባታቸው አቶ ደመቅሳ ሰንበቶ እና ከእናታቸው ነሲሴ ሰርዳ በ1923 ዓ.ም የተወለዱት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተወለዱ 94 ዓመታቸው አርፈዋል።

አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ሃገራቸውንና ህዝባቸውን የገለገሉ፣ የኢትዮጵያ ብሄሮች መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር የታገሉ፣ ሕብረብሔራዊት ጠንካራ ኢትዮጵያ ተፈጥራ ለማየት እድሜያቸውን በሙሉ የታገሉ መልካም ስብእናን የተለበሱ ሰው ነበሩ።

የደርግ መውደቅን ተከትሎ የፋይናንስ ስርዓት ለውጥ ሲደረግ ወዳጆቻቸውን በማስተባበር የአዋሽ ባንክ እንዲመሰረት ከፍ ያለ ሚና ከመወጣት ባሻገር የባንኩ ፕሬዚዳንት በመሆን ባንኩ ዛሬ ለደረሰበት እድገት የበኩላቸውን ደማቅ አሻራ ያሳረፉ፣ ለውጥ ለማምጣት ተመራጩ መንገድ ሰላማዊ የፖለቲካዊ ትግል ነው በሚል የጸና እምነት የፖለቲካ ፓርቲ መስረተው ፖርላማ በመግባት በመንግስት ላይ የሰላ ትችት ሲያቀርቡ የነበሩ አባትም ነበሩ።

በዛሬው እለት ዜና እረፍታቸው መሰማቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎችን ጨምሮ በርካቶች የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

የዝግጅት ክፍላችን ለጉምቱው ምሁር እና ፖለቲከኛ ህልፈተ ህይወት ማዘኑን እየገለፀ ለቤተ ዘመዶች እና አድናቂዎች መፅናናትን ይመኛል


አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ

በሕይወታችን የሚቻለዉንና የማይቻለዉን የሚወስነዉ ማን ነዉ? ገደባችንስ ምንድን ነዉ? ካለንበት ተነስተን መድረስ ወደምንፈልግበት ቦታ ለመድረስ የሚያስፈልገን ዋነኛ እዉነታ ምንድን ነዉ?

         እይታ

ጄምስ አርዊን ( James B. lrwin) እንደማንኛዉም ልጅ በአማካኝ በድሀ ቤት ዉስጥ ያደገ ሰዉ ነዉ። በዉስጡ ግን ያልተለመደ እይታ የነበረዉ ልጅ ነበር። በአንድ ምሽት ጄምስ ራቱን ከበላ በኋላ ሲጫወት ሳለ እናቱ፡ሰዓቷን ካየች በኋላ" መሽቷልና ወደ መኝታህ መሄድ አለብህ፡እኔ ስራዬን ስጨርስ እመጣለሁ" ብላ ወደ ክፍሉ ላከችዉ። በዚያ ጨረቃዋ ደምቃ በምትታይበት ብሩህ ምሽት ጄምስ ወደ ክፍሉ የሚወስደዉን ደረጃ ከወጣ በኋላ ክፍሉ ዉስጥ ተቀመጠ። እናቱ ከአንድ ሰአት በኋላ ሌታየዉ ስትሄድ ጄምስ በመስኮቱ አጠገብ ተቀምጦ ብሩኋን ጨረቃ ትኩር ብሎ ሲያይ አገኝችዉ። በመገረም፡

" ምን እያደረግህ ነዉ " በማለት ጠየቀችዉ።
" ጨረቃዋን እያየሁ ነዉ" አላት። የመኝታህ ሰዓት አልፏል፡መተኛት ነበረብህ እኮ " አለችዉ። በማንገራገር ወደ መኝታዉ እየሄደ እንዲህ አላት

" አንድ ቀን በጨረቃ ላይ እራመዳለሁ" አድጎ በበረራ ስልጠና የተመረቀዉ ጄምስ በአንድ ወቅት በልምምድ አይሮፕላን ላይ ከደረሰዉ የመከስከስ አደጋ ተርፋል። ከዚያም በተጨማሪ በተለያዬ የሕይወት ዉጣ ዉረዶች እንዳለፈ ይነገራል። ጄምስ ኢርዊን ያንን ራእይ የተሞላበትን ሃሳብ ለእናቱ ከተናገረ ከ32 ዓመታት በኋላ ጠረቃ ላይ እግራቸዉን ከረገጡት ሰዎች መካከል ራሱን አገኝዉ። የእይታ ጉልበት!

ምንጭ:- 25 የስኬት ቁልፎች መፅሀፍ

መርሕ የንባብ ቤት

ታህሳስ 2017 ዓ.ም


የኤሌክትሪክ አደጋን ለመከላከል የጥንቃቄ መንገዶች

የኤሌክትሪክ አደጋ በኤሌክትሪክ ምክንያት የሚመጣ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊከሰት የሚችል ሲሆን በሰው ህይወትና አካል፣ እንዲሁም በንብረት ላይ ጊዜያዊ ወይም ዘላቂ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፡፡

በመሆኑም ራስዎን ከኤሌክትሪክ አደጋ ለመጠበቅ፡-

👉 በረገቡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ሾልኮ ለማለፍ አይሞክሩ፤
👉 ኃይለኛ ንፋስ በሚነፍስበት ወቅት ከኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ርቀትዎን ጠብቀው ይንቀሳቀሱ፤
👉 ተበጥሶ የወደቀና የተንጠለጠለ የኤሌክትሪክ ገመድ ወይም ሽቦ ሲያዩ ከመንካት በመቆጠብ ለሚመለከተው አካል ያሳውቁ፤
👉 በከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌክትሪክ መስመሮች ስር ወይም አጠገብ ማንኛውንም የግንባታ ሥራ ከማከናወን ይጠበቁ፤
👉 ህንፃዎች ሲገነቡ ከኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ፤ዛፎች ሲቆረጡ የኤሌክትሪክ መስመሮች ላይ እንዳይወድቁ ጥንቃቄ ያድርጉ፤
👉 የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ከቆርቆሮ ጣሪያ፣ አጥር፣ ከልብስ ማስጫ ገመዶች ጋር እንዳይገናኙ ያድርጉ፤
👉 የቤት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋት በባለሞያ እንዲከናወን ያድርጉ፤
👉 ደረጃቸውን የጠበቁ የኤሌክትሪክ ቁሳቁሶችን ይጠቀሙ፤
👉 በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መሳሪያዎች ላይ ቃጠሎ ሲነሳ በውሀ ከማጥፋት በመቆጠብ ትክክለኛውን የእሳት ማጥፊያ ይጠቀሙ፤
👉 የኤሌክትሪክ መስመሩን ከመቆጣጠሪያው ሳያጠፉ በኤሌክትሪክ የተያዘን ሰው ለማዳን አይሞክሩ፤
👉 የኤሌክትሪክ ሀይልን ከራስዎ ቆጣሪ ወደ ሌላ ሰው ቤት አሳልፎ ከመዘርጋት ይቆጠቡ፤
👉 ብረት ነክ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከኤሌክትሪክ ሶኬቶች ወይም ማከፋፈያዎች ጋር በፍፁም አያገናኙ፤
👉 በአንድ ማከፋፈያ ላይ ብዙ ኬብሎችን ማገናኘት ለአደጋ ስለሚያጋልጥ በፍፁም አያድርጉ፤
👉 በኤሌክትሪክ ሥራ ሲሰሩ ርጥብ ነገሮች ለአደጋ ሊያጋልጥዎ ስለሚችሉ መጠንቀቅ አይዘንጉ፤


አንዳንድ እውነታዎች ስለ ካንሰር
━━━━━✦━━━━━

→ ሁሉም ሰው በካንሰር ሊጠቃ ይችላል።

→ ከ100 በላይ የካንሰር ዓይነቶች ያሉ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የካንሰር ዓይነቶችን መከላከል ይቻላል።

→ 90 በመቶ የካንሰር መንስኤ አካባቢያዊ ሲሆን 10 በመቶ ደግሞ ዘረ-መላዊ (ከወላጆች በዘር የሚወረስ) ነው።

→ በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ ትምባሆ ማጨስ 25 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል። 90 በመቶ የሳምባ ካንሰር መንስኤም ሲጋራ ማጨስ ነው።

→ አንዲት ሲጋራ ውስጥ ከ7 ሺህ በላይ ኬሚካሎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ70 በመቶ የሚበልጡት ካንሰር አምጪ ናቸው።

→ በዓለማችን በካንሰር ምክንያት ከሚፈጠረው አጠቃላይ ሞት ውስጥ አልኮል መጠጣት ከ3 እስከ 5 በመቶ ድርሻ ይይዛል።

→ ዓለም ላይ ሴቶችን በብዛት የሚያጠቃው የካንሰር ዓይነት የጡት ካንሰር ነው።

→ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ በጡት ካንሰር የመያዝ እድልን ከ25 - 30 በመቶ ይቀንሳል።

→ ወንዶችን በብዛት ከሚገድሉ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ የሳምባ ካንሰር፣  የጉበት ካንሰር፣  የጨጓራ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር እና የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ይጠቀሳሉ።

→ ሴቶችን በብዛት ከሚገድሉ የካንሰር ዓይነቶች ውስጥ የጡት ካንሰር፣ የሳንባ ካንሰር፣ የአንጀት ካንሰር፣ የማህፀን በር ካንሰር እና የጨጓራ ካንሰር ይጠቀሳሉ፡፡

→ ካንሰር የዓለም ኢኮኖሚን ክፉኛ እየጎዳ ይገኛል። የዓለም ሀገራት በዓመት ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ለካንሰር ሕክምና ያወጣሉ።

→ ትምባሆ ባለማጨስ፣ አልኮል ባለመጠጣት፣ ጤናማ አመጋገብ በመከተል እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ብቻ የካንሰር ተጋላጭነትን እስከ 30 በመቶ መቀነስ ይቻላል። 
━━━━━━


አራቱ ስህተቶቻችን

•  አጥብቀን መያዝ ያለብንን ነገር በቀላሉ መልቀቃችን፣ በቶሎ መልቀቅ የሚገባንን ነገር ደግሞ አጥብቀን መያዛችን!!!

•  ሰርተን ማግኘት የሚገባንን ነገር በነጻ መጠበቃችን፣ በነጻ የተሰጠንን ነገር ሰርተን አለማሳደጋችን!!!

•  የማይፈልጉንንና የማይጠቅሙንን ሰዎች መከታተላችን፣ የሚፈልጉንንና የሚጠቅሙንን ሰዎች ችላ ማለታችን!!!

•  መናገር በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ ዝም ማለታችን፣ ዝም ማለት በሚገባን ጊዜና ሁኔታ ላይ መናገራችን!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ


ቴሌግራም ላይ የሚላኩላችሁ ሊንኮች ከመረጃ መንታፊዎች ሊሆን ስለሚችል ከማታዉቁት ሰዉ የሚደርሳችሁን የቴሌግራም ሊንኮች እንዳትከፍቱ‼️

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁትም ይሁን ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት.


የኤለን መስክ ትንቢት!!!

በመጪው ዓመት መጨረሻ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ከሰው በሚበልጥ ሁኔታ የማሰብ ችሎታን ይላበሳል ሲል ቢሊየነሩ ኤለን መስክ ተነበየ፡፡

የቴስላ እና የስፔስኤክስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤለን መስክ ይህን ትንቢት የተናገረው፥ የኤአይ ኩባንያው ኤክስኤአይ አውሮራ የተሰኘውን የመጀመሪያውን የምስል አመንጪ ሞዴል ይፋ ሲያደርግ ነው፡፡

“በፈረንጆቹ 2025 መገባደጃ ላይ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የአንድን ሰው የማሰብ ችሎታ ይተካል፤ በፈረንጆቹ 2027/28 ደግሞ የሁሉንም ሰው የማሰብ ችሎታ የመተካት እድሉ እየጨመረ መጥቷል” ሲልም ነው መስክ በኤክስ ገጹ ላይ የገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በ2030 ከሰዎች ሁሉ የማሰብ ችሎታ በላይ የመሆን እድሉ መቶ በመቶ ነው ማለቱን የዘገበው አርቲ ነው፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ቁጥጥር ካልተደረገበት በከፍተኛ ደረጃ አደጋ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ታዋቂ የሆኑ ሰዎች እና የዘርፉ ተመራማሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፡፡

ከእነዚህም ውስጥ ባለፈው ወር በሞንትሪያል ዩኒቨርሲቲ የኮምፒዩተር ተመራማሪ ዮሹዋ ቤንጂዮ (ፕ/ር) የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች ብዙም ሳይቆይ የሰው ልጅ የግንዛቤ ችሎታዎች ሊኖሯቸው እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ይህም ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እየሆነ በመምጣቱ በሰው ልጅ ላይ ከባድ አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

ተመራማሪው በአሁኑ ጊዜ የሰለጠኑት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች የሰው ልጅን ያጠፋሉ የሚለውን ስጋትም አንስተዋል፡፡

ቤንጂዮ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምክንያት ማህበራዊና ፖለቲካዊ ልዩነት ሊያስከትሉ የሚችሉትን አደጋዎች በመጥቀስ፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጂኦ-ፖለቲካዊ መረጋጋትን አደጋ ላይ እንደሚጥልም ነው ያስጠነቀቁት፡፡

(መረጃው የFMC ነው)


በቀን ውስጥ የምንሸናው ሽንት መጠን መጨመር እና ማነስ ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?
ጤነኛ ሰው በቀን ውስጥ ስንት ጊዜ መሽናት አለበት?
የሽንት መጠን ከጾታ ጾታ ይለያያል?
በቀን ውስጥ የምንሸናው ሽንት መጠን መጨመር እና ማነስ ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?
የሰው ልጅ አብዝቶ የሚጨነቅበት ጉዳይ የጤናው ነገር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰው ልጆችን ህይወት እያቀለሉ የመጡ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ የራሳቸው ጥቅም እና ጉዳቶች አሏቸው፡፡
ሲኤንኤን የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ በሰራው ዘገባ የሰው ልጅ ሽንት ቀለም፣የመሽናት ድግግሞሽ መጠን የአንድን ሰው ጤና ሁኔታ አስቀድመን እንድንገምት እና ተጨማሪ ምርመራዎችን እንድናደርግ የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ባለሙያዎቹ አስተያየት አንድ ጤነኛ በአንድ ቀን ውስጥ በአማካኝ ከ6 እስከ 8 ጊዜ መሽናት ያለበት ሲሆን ይህም በአራት ሰዓት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ መሽናት ይኖርበታል፡፡
በቀን ውስጥ ሽንት የመሽናት ምጣኔው ከዚህ በላይ ከሆነ ግን የብዙ ጤና እክሎች መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡
ሌሊት ላይ ደግሞ አንድ ሰው ጭራሽ ላይሸና አልያም አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሸና የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ግን ትክክል ያልሆኑ ነገሮች ስላሉ ተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንዲደረግ የጤና ባለሙያዎቹ መክረዋል፡፡
ይሁንና አንድ ሰው በቀን ውስጥ በተለየ መንገድ ብዙ መጠን ለው ፈሳሽ ከወሰደ እስከ 10 ጊዜ ሊሸና ይችላልም ተብሏል፡፡
ከተለመደው መጠን በላይ ሽንት መሽናት አልያም ሽንት የመምጣት ምልክት ሊመጣ የሚችለው የፊኛ መቆጣት፣ እንደ ቡና እና መሰል የማነቃቃት ስሜት ያላቸው መጠጦችን አብዝቶ መውሰድ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በሙቀታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች የመሽናት መጠናቸው አነስተኛ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን ይህ ባልሆነበት ግን ድንገት የመሽናት ስሜት መምጣት ካለ የስኳር ህመም፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና መሰል ህመሞች ሊሆኑ ይችላሉም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ብዙ የመሽናት መጠን መጨመር እንደ ስትሮክ፣ የነርቭ ህመሞች መኖር ምልክት የመሆን እድሉም ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
ጭንቀት እና ድብርት አይነት ስሜቶች የሰው ልጅን ደጋግሞ ወደ መጸዳጃ ቤት ሊያደርጉ ይችላሉ የተባለ ሲሆን
ይህ በዚህ እንዳለ በቀን ውስጥ አራት እና ከዛ በታች ጊዜ የሚሸና ሰው በሰውነቱ ውስጥ በቂ ውሃ አለመኖሩን አልያም ከፊኛ ወይም ከኩላሊት ጋር የተያያዙ ህመሞች መኖሩን ሊያመለክት ስለሚችል ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ባለሙያዎቹ አክለውም አንድ ሰው በአማካኝ በሚወስደው የውሃ መጠን ላይ (የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን ጨምሮ) ከጾታ ጾታ የሚለያይ ሲሆን ሴቶች በአማካኝ በቀን ውስጥ 2 ነጥብ 7 ሊትር ውሃ ወንዶች ደግሞ 3 ነጥብ 7 ሊትር ውሃ እንዲጠጡም መክረዋል፡፡
ነገር ግን በቂ ውሃ እየጠጡ ቶሎቶሎ የማይሸኑ ሰዎችም የኩላሊት እና ፊኛ ጤናን ስለሚጎዳ ሰዎች ከዚህ መጠንቀቅ አለባቸውም ተብሏል፡፡


* በቅፅበት ከፍተኛ ደረጃ እደርሳለሁ አትበል፡፡
ከትምህርት ቤት አንደወጣህ ወዲያው ሃብታም፣ ባለስልጣን፣ ወይም ስኬታማ እሆናለሁ ብለህ አትጠብቅ፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ቢኖርህ እንኳ ስኬታማ ለመሆን ብዙ ልምድ ያስፈልግሃል፡፡

* ስለ ስህተቶችህ ሌሎችን ሳይሆን ራስህን ውቀስ ተማርባቸው፡፡
ስህተቶች እንድንቆጭባቸው ሳይሆን እንድንማርባቸው ካደረግን ደግመን አንሰራቸውም፡፡

* በተቀጣጠለ መንፈስና መሰጠት ስራ፡፡
መርጠህ ወይም ፈልገህ የምትሰራውን ስራ በከፍተኛ ትጋት፣ መሰጠት፣ መቀጣጠል የምታደርግ ከሆነ ስራ አስደሳችና ቀላል ይሆንልሃል፡፡ የምትሰራው ስራ ውስጥ እነዚህ ነገሮች ከጠፉ ወይም የምትሰራው የሚሰለችህ ከሆነ የምትሰራው ነገር የውስጥ ፍላጎትህን ማንፀባረቁ አጠራጣሪ ነው፡፡

* ምርጡ ትምህርት ቤት ኮሌጅ ሳይሆን ህይወት ነው፡፡
ምንም ያህል መፅሀፎች ብታነብ፣ ፈተናዎችን ብትወስድና ብታልፍ፣ በህይወት ሂደት የምትማረውን ያህል ብቁ አያደርጉህም፡፡ ስራዎች እና የስራ ሃላፊዎች ያስተምሩሃል፣ ያበቁሃል፡፡

* እውነተኛ ኑሮና ህይወት በቴሌቪዥን እንደምታየው አይደለም፡፡
ኑሮ ቲቪ ላይ ስታይ እንዳለው ካፌዎች ሄዶ ዘና ማለት ከመሰለህ ተሳስተሃል፡፡ ስራ ሰርተህ ኑሮህን ህይወትህን ለመለወጥ ተንቀሳቀስ፡፡

* ህይወት ሁሌም የቀና አይደለም፡፡
በህይወት ጉዞህ ትገጫለህ ትወድቃለህ፡፡ ኑሮ ፈተና ነው፣ ጌም መሳይ ነው፣ ተነስተህ እስኪሳካልህ ጉዞህን ቀጥል፡፡
* የራስ ስራ መስራት ድፍረትና ብከስርም እሰራለሁ ማለትን ይጠይቃል፡፡

ቢዝነስ በአንድ ጎኑ አንደ ቁማር ነው፡፡ 100% ማሸነፍ መቻልህን ቀድመህ እርግጠኛ መሆን አትችልም፡፡ ከቁማር የሚለየው ግን ማጥናት፣ ማቀድና፣ ሁኔታዎችን እያየህና እየቀያያርክ በጥንቃቄ መተግበር መቻልህ ነው፡፡
* ለስኬታማነት ትእግስት እና ጠንክሮ መስራት ያስፈልግሃል፡፡ በአቋራጭ የሚመጣ ዘላቂ ስኬት የለም፡፡

የላቁ እይታዎች


ሩሚ_የሰጣቸው_ውብ_መልሶች !!
🦹‍♀️
፨ አንድ ሰው ለጠየቀው ጥያቄ ሩሚ የሰጠው መልስ...
🦹‍♀️
መርዝ ምንድነው?
🦹‍♀️
ማንኛውም ከሚያስፈልገን መጠን በላይ የሆነ ነገር ሁሉ መርዝ ነው። ስልጣን ፣ ሀብት፣
ድህነት፣ ንዴት፣ ስግብግብነት፣ ስንፍና፣ ጥላቻ ፣ ራስ ወዳድነት፣ ፍቅር፣ ጉጉት፣ ወይንም
ሌላ ማንኛውንም ነገር ሊሆን ይችላል።
🦹‍♀️
፨ ፍርሃት ምንድነው?
🦹‍♀️
እርግጠኛ አለመሆንን አለመቀበል ነው። እርግጠኛ አለመሆናችንን ብንቀበል ፣ ፍርሃት
ገድል ይሆናል።
🦹‍♀️
፨ ቅናት ምንድነው?
🦹‍♀️
የሌሎችን በጎ ነገር አለመቀበል ነው። የሌሎችን በጎነት ብንቀበል ፣ መነሳሳት ይፈጥርልናል

🦹‍♀️
፨ ንዴት ምንድነው?
🦹‍♀️
ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮችን አለመቀበል ነው። ያንን
ብንቀበል ትእግሥት ይሆነናል።
🦹‍♀️
፨ ጥላቻ ምንድነው?
🦹‍♀️
ጥላቻ አንድን ሰው እንዳለ በሰውነቱ መቀበል አለመቻል ነው። አንድን ሰው ያለ ምንም
ቅድመ ሁኔታ መቀበል ብንችል ግን፣ ያ ጥላቻ ፍቅር ይሆናል።
"አንድን ነገር በጥሞና እና በጥልቅ ከተረዳህ፣ በዛ ውስጥ ሁሉንም ነገር ትረዳለህ"
ሩሚ


___

ዛፍ በሁለት በኩል ያድጋል፤ አንድም በስሩ - ወደ ጥልቁ ወደ ጨለማው፣ አንድም በቅርንጫፉ - ወደ ብርሃን ወደ ከፍታው።

--

ወደ ጨለማው ስሩን በሰደደ ቁጥር ወደ ከፍታው ይመነደጋል፤ በስሩ ዓለት ይሰባብራል - በቅርንጫፉ አየሩን ይቀዝፋል፤ የቁመናው ጥንካሬ ከስርገቱ ልኬት ይወለዳል፣ የፍሬው መጎምራት ከብርሃንና ጨለማ ይሰራል።

--

ከጥልቁ የምድርን በረከት ይወስዳል፣ ከብርሃን የፀሐይና አየርን ስጦታ ይቋደሳል - ለሕልውናው ሁለቱም ያስፈልጋሉ።

--

ጽልመትና ፈተና ሲገጥምህ ብርሃንና ምቾትህ የሚወለድበት ቦታ ላይ እንዳለህ አስብ። 

--

ዝቅ ብለህ መሰረት ካላቆምክ ቀና ብለህ አትራመድም፤ ቁልቁል ወርደህ ጨለማውን ካልተጋፈጥክ ከፍ ብለህ ብርሃን አታይም።

--

ተረቱን እርሳው!... ካሮት ቁልቁል የሚያድገው ፍሬ ለማፍራት ነው።

--


አስገራሚ የጉዞ እውነታዎች


• አብራሪዎችና ረዳት አብራሪዎች፣ ከበረራ በፊት አንድ አይነት ምግብ አይበሉም።


ይሄ የሚደረገው በምክንያት ነው፡፡ አብራሪዎችና ረዳት አብራሪዎች ከበረራ በፊት አንድ ዓይነት ምግብ ከበሉ ድንገት የምግብ መመረዝ (ወይም ከዚያም የከፋ) ቢከሰት አውሮፕላኑን ማን ሊያበረው ነው? ስለዚህ አንድ አይነት ምግብ አይመገቡም። አያድርስና ከሁለት አንዳቸው ቢታመሙና አቅም ቢከዳቸው (መታጠቢያ ቤት ቢቀሩ) ሌላኛው አብራሪ ሃላፊነቱን ሊረከብ ይችላል።


• የህንድ ባቡሮች በየቀኑ ወደ 23 ሚሊዮን ገደማ መንገደኞችን ያጓጉዛሉ።

ይሄ ማለት ምን መሰላችሁ? በየቀኑ አጠቃላይ የአውስትራሊያ ህዝብን ያጓጉዛሉ እንደማለት ነው፡፡


• ሳኡዲ አረቢያ ወንዝ የሚባል የላትም፡፡


በአረብ ባሕረ- ገብ መሬት ውስጥ ያለችው ሳኡዲ፤ ቋሚ ወንዞች የላትም። አንድም ወንዝ ከማይፈስባቸው 17 የአለም ሀገራት አንዷ ነች።

• ሩሲያ ቢራን ከአልኮል መጠጥ የመደበችው እ.ኤ.አ በ2011 ዓ.ም ነው፡፡


በሚያስገርም ሁኔታ፣ ከዚያ በፊት ከ10 ፐርሰንት በታች የአልኮል መጠን ያለው ማንኛውም መጠጥ እንደ ‘የምግብ ነገር’ ይቆጠር ነበር፤ በአገረ ሩሲያ፡፡


አዲሱ የሶርያ መሪ ማናቸው?

አቡ ሞሃሙድ አል ጁላኒ በ1982 በሪያድ ሳውዲ አረቢያ ተወለዱ። አባታቸው በፔትሮሊየም መሀንዲስነት ይሰሩ ነበር። ቤተሰቡ በ 1989 ወደ ሶሪያ ተመለሰ። ከዛም በደማስቆ አቅራቢያ ሰፍረዋል። አል ጁላኒ እ.ኤ.አ. በ 2003 ወደ ኢራቅ በመሄድ አልቃይዳውን ተቀላቅለዋል። በአሜሪካ ኃይሎች በ2006 ተይዘው ለአምስት ዓመታት በእስር ቆይተዋል።

ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሶሪያ ውስጥ የአልቃይዳ ቅርንጫፍ የሆነውን የአል-ኑስራ ግንባርን የማቋቋም ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር። ይህም በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ፣በተለይም ኢድሊብ አካባቢ ነው።እ.ኤ.አ. በ2013 አል-ባግዳዲ ቡድናቸው ከአልቃይዳ ጋር ያለውን ግንኙነት ማቋረጡን ቢያስታውቅም አል-ጁላኒ ግን ለውጡን ውድቅ አድርገውታል። እ.ኤ.አ. በ 2016 አሌፖ በአል-አሳድ ጦር እጅ ስትወድቅ እና የታጠቁ ቡድኖች ወደ ኢድሊብ ሲያመሩ አል-ጁላኒ ቡድናቸው ስሙን ጀብሃት ፋቲህ አል ሻም ብሎ መቀየሩን አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. በ2017፣ አል-ጁላኒ ቡድናቸው ኤችቲኤስን ለመመስረት ወደ ኢድብሊብ ከሸሹ ሌሎች በርካታ የታጠቁ ቡድኖች ጋር እየተዋሃደ መሆኑን አስታውቋል። የኤችቲኤስ አላማ ሶሪያን ከአል አሳድ መንግስት ነፃ ማውጣት ፣የኢራን ሚሊሻዎችን ከአገሪቱ ማባረር እና በእስላማዊ ህግ ትርጓሜ መሰረት መንግስት መመስረት ነው ሲል በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የስትራቴጂክ እና አለም አቀፍ ጥናት ማዕከል አስታወቀ።


የሶርያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ከስልጣን ተወግደው ከሀገር ኮበለሉ

በሶሪያ ዋና ከተማ የሚገኘውን የህዝብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ህንፃን አማፂያኑ ተቆጣጥረዋል ። የህዝብ ራዲዮ እና ቲቪ ህንፃ በሶሪያ ውስጥ ጠቃሚ፣ ተምሳሌታዊ ቦታ ነው። ህንፃው በደማስቆ እምብርት ውስጥ ከመገኘቱ በተጨማሪ በሶሪያ በ 1950 ዎቹ እና 60 ዎቹ ተከታታይ መፈንቅለ መንግስት በነበረበት ጊዜ አዳዲስ መንግስታትን ስልጣን መያዛቸውን ለማወጅ ጥቅም ላይ ውሏል ።የአማፂው ቡድን ኤች ቲ ኤስ ወደ ሶሪያ ዋና ከተማ መግባት መጀመሩን ባሳወቀበት ወቅት የበሽር አላሳድ ከሀገር መኮብለል ዘገባዎች ወጥተዋል።

አማፅያኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ደጋፊዎቻቸው ተሰቃይተዋል እና ተገድለዋል ከተባለበት ከሳይድናያ እስር ቤት እስረኞችን ማስፈታታቸውን ተናግረዋል።የታጠቁት ተቃዋሚዎች "አዲሲቷ ሶሪያ" ሰላማዊ አብሮ የመኖር ቦታ ትሆናለች፣ ፍትህ የሚሰፍንበት እና የሁሉም የሶሪያውያን ክብር ይጠበቃል ሲሉ ተደምጠዋል። ያለፈውን ገጽ ቀይረን ለወደፊቱ አዲስ አድማስ እንከፍታለን ሲሉ አማፅያኑ ባወጡት መግለጫቸው ተናግረዋል።

የሮይተርስ የዜና ወኪል ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው በሺዎች የሚቆጠሩ በመኪና እና በእግር የሚጓዙ ሰዎች በማዕከላዊ ደማስቆ “ነጻነት!” እያሉ በመሰብሰብ ላይ ናቸው። በኦንላይን የተለጠፉት ቪዲዮዎች በአልጀዚራ የተረጋገጠ በኡማያድ አደባባይ ላይ በርካታ ሰዎች በወታደራዊ ታንክ ላይ ቆመው በደስታ ሲዘፍኑ ያሳያሉ።

የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ አውሮፕላን ተሳፍረው ወዳልታወቀ ቦታ ሄደዋል። ከሀገር መኮብለላቸውን የሚያውቁ ሁለት ስማቸው ያልተጠቀሰ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ቅዳሜ ቀደም ብሎ አል አሳድ ደማስቆን ለቀው መጥተዋል መባሉን የሶርያ መንግስት አስተባብሏል። የሶርያ መንግስታዊ የዜና ወኪል በደማስቆ እንዳሉ እና ስራቸውን ከዋና ከተማዋ እያከናወነ መሆኑን ገልጾ ነበር። ሆኖም ፕሬዚዳንቱ የት እንዳሉ አይታወቅም እና ለቀናት እንዳልታዩ ተዘግቧል።


ምንም ያህል ሊቅ ብትሆን ስሜትህን መግራት ካልቻልክ ፊደል መቁጠር ከማይችለው ብታንስ እንጂ በምንም አትሻልም፡፡ዕውቀትህን ስሜትህ ካሸነፈው ዋጋ የለህም፡፡ ፍላጎትህ ጥበብህን ድል ከነሳው የፍላጎትህ ባሪያ ሆነህ ዕድሜህን ትጨርሳለህ፡፡ስምና ዝና ቢኖርህም እራሱ ፍላጎትህን መቆጣጠር፣ ደመነፍስህን ማስተዳደር ካልቻልክ ምንም ነህ፡፡ባዶነትህን ካልሞላህ እንደጎደልክ ትኖራለህ፡፡ ስሜትህ እንዳሻው እንጂ አንተ እንዳሻኸው አትሆንም።

የሥሜት ማጣት ስሜት የአንተነትህ ጌታ ይሆናል።ማወቅህ ስሜትህ ላይ ካልሰለጠነ፤ ዕውቀትህ ፍላጎትህን ካልተቆጣጠረ፣ ስምና ዝናህ ስሜትህን ካልገራ እንደብረት ድስት ሲጥዱህ ቶሎ ትግላለህ፤ ሲያወርዱህም ቶሎ ትቀዘቅዛለህ፡፡ አንተ ግን ክቡር ሰው ነህ ከብረድስትም በላይ!! ስለዚህ ሰው ሁን!

( ሾፐን ሀወር )

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.