የተውሒድ ዳዕዋ በወሎ–ወረኢሉና አውራጃዋ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


የተውሒድ ዳዕዋ በወረኢሉ
وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ zariyat :56

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
አንዳንድ እህቶች ኒካሕ ሲቃረብ አባቶቻቸው ሺርክ ላይ እንደሆኑ በመጥቀስ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ይጠይቃሉ።
1- በመጀመሪያ የእውነት ሺርክ መኖሩን በተጨባጭ ማረጋገጥ ይገባል። ኹራፋት፣ ቢድዐዎች፣ ተወሱላት ብቻቸውን ሺርክ ላይ ላይደርሱ ይችላሉ። ችግሩ እዚያ የሚደርስ መሆን አለመሆኑን በትክክል መለየት ይገባል።
2- በተጨባጭ አባት ሺርክ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚችሉትን ሁሉ ጥረት በማድረግ ለመመለስ መጣር ይገባል። ይሄ የኒካሕ ሰሞን ሳይሆን ቀድሞ ነው ሊሰራበት የሚገባው። ከኒካሑ የበለጠ የሚያሳስበው ይሄ ነው። "ክፉ ደግ አይቶ፣ ለፍቶ ያሳደገኝ አባቴ ኒካሕ አታስርም ሲባል በጣም አዘንኩኝ፣ ከፋኝ፣ ..." የሚል የዓጢፋ (ስሜት) ንግግር ዋጋ የለውም። ሺርክ ከኢስላም የሚያስወጣ፣ ዘላለማዊ ክስረትን የሚያስከትል፣ እስከወዲያኛው ከሚወዱት የሚለያይ ከባድ ጥፋት ነው። ከኒካሑ በፊት ሺርክ ውስጥ ሲኖሩ ያልተሰማን ስሜት "ወሊይ አይሆኑም" ሲባሉ ከተሰማን ችግሩ ከራሳችን ነው። ገና ያልጠራ ነገር አለ ማለት ነው። እናጥራ።
3- በተረፈ ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ከተቀበሉ ወሊይ ሆነው ኒካሑን ያስራሉ። ከኢስላም የሚያስወጣው ትልቁ ሺርክ መኖሩ በተጨባጭ ተረጋግጦ፣ ተመክረው ተዘክረው ለመቀበል አሻፈረኝ ካሉ ግን ወሊይ ሆነው ኒካሕ ሊያስሩ አይፈቀድም። ከዚህ ዝቅ ባለ ጉዳይ ሶላት የማይሰግዱ ሆነው እንዲሰግዱ ቢመከሩም ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ለኒካሕ አይሆኑም። የሶላት ጉዳይ በንፅፅር ከተውሒድ ያነሰ ከመሆኑ ጋር ማለት ነው።
4- እንዲህ አይነት ሁኔታ ከገጠመ ወሊይነቱ ወደሌላ ቅርብ ቤተሰብ ይሻገራል። ኒካሑ በነሱ በኩል ይታሰራል። ለኒካሕ የሚሆን ቤተሰብ ከሌለ በቃዲ ይታሰራል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor


ዛሬ እሁድ ሸዕባን 25/1446 (የካቲት 16/2017)
አሸዋ ሜዳ ዘህራእ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


ARBA MINCH UNIVERSITY dan repost
የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዋ ዶ/ር ዛኪራ ተባረክ ••• ኒቃብ ከመማር፣ ከመሸለም፣ከመምራት እንደማያግድ በተግባር አስመስክራለች! ዶክተር ዛኪራ ጀመዓውን በማስተባበርም በቀዳሚነት ስትንቀሳቀስ የነበረች እህታችን ናት።

ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በሜዲስን 3.87 አምጥታ በዛሬው እለት ተመርቃለች:: መመረቅ ብቻ ሳይሆን ደግሞ በሶስት ዘርፍ ተሸላሚ ሆና ነው የተመረቀችው:: ከሁሉም የህክምና ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች:: ከሁሉም ሴቶች አንደኛ ወጥታ ተሸልማለች:: ከሁሉም ተማሪዎች አንደኛ ወጥታ የወርቅ ሜዳለያ ተሸልማለች::

እንኳን ደስ አለሽ! እንኳን ደስ አላቹህ!


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ከታሪክ አምባ
(ክፍል አራት)
~
ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:—

"በሐጅ ወቅት መካ ውስጥ ነበርኩ። አንድ ከኹራሳን የሆነ ሰው ‘እናንተ ሑጃጆች ሆይ! እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ! ነዋሪዎች! መጤዎች! አንድ ሺህ ዲናር የያዘ ከረጢት ጠፍቶብኛል። የመለሰልኝ ሰው አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ከእሳትም ነፃ ያድርገው። በምርመራው ቀንም ምንዳና ሽልማት ይኖረዋል’ ሲል ሰማሁት።

በዚህን ጊዜ ከመካ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ትልቅ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳኒዩ ሆይ! ሃገራችን ሁኔታዋ የከፋ ነው። የሐጅ ቀናት ጥቂት ናቸው። ክብረ በአላቱም ውስን ናቸው። የስራ በሮች ተዘግተዋል። ምናልባትም ይሄ ገንዘብ ከድሃ አማኝ፣ ከትልቅ አዛውንት እጅ ወድቆ ወሮታውን እንድትሰጠው ቃል እንድትገባለት ሊከጅል ይችላልና ገንዘቡን ቢመልስ ትንሽ ሐላል ገንዘብ ትቸረዋለህ ወይ?’ አለ።

ኹራሳኒዩ:— ስንት ነው ወሮታው? ስንት ይፈልጋል?
አዛውንቱ:— አንድ አስረኛ ይፈልጋል። መቶ ዲናር። የአንድ ሺው 10%።
ኹራሳኒዩ:— አልተስማማም። ‘አላደርገውም። ይልቅ የዚህን ሰውዬ ጉዳይ ወደ አላህ አስጠጋለሁ። በምናገኘውም (የቂያማ) ቀን ወደሱው እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን፣ ያማረ የሆነ መመኪያ’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪይ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ድሃ ሰው የተባለው ይሄ ሽማግሌ መሰለኝ። ምናልባትም የዲናሮቹን ከረጢት አግኝቶት ከሱ ትንሽ ፈልጎ ነው። ተከተልኩት። ወደቤቱ ተመለሰ። እንደጠረጠርኩት ነበር።

‘ሉባባ ሆይ!’ ብሎ ሚስቱን ሲጣራ ሰማሁት።
‘አቤት የጊያሥ አባት!’ አለች።
‘የገንዘቡን ባለቤት እያፈላለገ ሲጣራ አገኘሁትኮ። ላገኘለት ሰው ምንም ሊሰጥ አይፈልግም። ከሱ ላይ መቶ ዲናር ስጠን ብየው ነበር። እምቢ ብሎ ጉዳዩን ወደ አላህ አስጠጋ። ምን ባደርግ ይሻላል ሉባባ? የግድ መመለስ አለብኝ። እኔ ጌታዬን እፈራለሁ። ወንጀሌ እንዳይደራረብ እሰጋለሁ’ አለ።
በዚህን ጊዜ ሚስቱ እንዲህ አለች:— ‘ሰውየ! እኛኮ ካንተ ጋር ከአምሳ አመት ጀምሮ በድህነት እየማቀቅን ነው። አራት ሴት ልጆች፣ ሁለት እህቶች፣ እኔ፣ እናቴ አለን። አንተ ዘጠነኛችን ነህ። ፍየል የለን፣ የግጦሽ ቦታ የለን። ገንዘቡን ሁሉንም ውሰድ። ተርበናል አጥግበን። ያለንበትን ታውቃለህ አልብሰን። ምናልባትም አላህ — ዐዘ ወጀለ— ከዚያ በኋላ ያብቃቃህ ይሆናል። ያኔ ቤተሰብህን ካበላህ በኋላ ገንዘቡን ትሰጠዋለህ። ወይ ደግሞ በትንሳኤ ቀን እዳህን አላህ ይከፍልልሃል’ አለች።

ሰውየው:— ሉባባ ሆይ! እድሜዬ 86 አመት ከደረሰ በኋላ ሐራም ልበላ ነው? ድህነቴን ይህን ያክል ከታገስኩ በኋላ አካሌን በእሳት ላቃጥል? ለቀብሬ ከቀረብኩ በኋላ የኃያሉን ቁጣ በራሴ ላይ ላስወስን? በፍፁም አላደርገውም ወላ፞ህ!’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር እዚህ ላይ እንዲህ ይላሉ:— "የዚህ ሰውዬና የሚስቱ ነገር እያስደነቀኝ ተመለስኩኝ። በነጋታው ያ የዲናሮቹ ባለቤት ልክ እንደ ትላንቱ ሲጣራ ሰማሁት። ያ አዛውንት ተነሳና
‘አንተ ኹራሳኒዩ! ትላንት ያልኩትን ብዬህ መክሬህ ነበር። ሃገራችን ወላ፞ሂ አዝመራውና እላቢው የቀለለ ነው። ገንዘቡን ያገኘው ሰው ሸሪዐን እንዳይፃረር ትንሽ ገንዘብ ብትሰጠው፤ ላገኘው ሰው መቶ ዲናሮችን ስጠው ብልህ እምቢ ብለሃል። ገንዘብህ አላህን — ዐዘ ወጀለ— ከሚፈራ ሰው እጅ ላይ ቢወድቅ በመቶው ፋንታ አስር ዲናሮችን ብቻ ብትሰጠው ምናለበት? እነሱንም ይሰትራቸዋል፣ ይሸፍናቸዋል፣ ቀለብም ይሆናቸዋል’ አለ።

ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ገንዘቤን ከጌታዬ ዘንድ እተሳሰበዋለሁ። በትንሳኤ ቀንም ወደሱ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው’ አለ።"

"በቀጣዩም ቀን የዲናሮቹ ባለቤት እንደቀደሙት ቀናት ጥሪውን አስተጋባ። አሁንም ያ ሽማግሌ ተነሳና እንዲህ አለ:—
‘አንተ ኹራሳኒዩ! የመጀመሪያ ቀን ላይ ገንዘቡን ላገኘው ሰው መቶ ዲናር ስጠው ብዬህ እምቢ ብለሃል። ከዚያ አስር አልኩህ እምቢ አልክ። እሺ አንድ ዲናር ብትሰጠውና በግማሿ የሚፈልጋትን ነገር ቢሸምት፣ በግማሿ ደግሞ የሚያልባት ፍየል ቢገዛና ሰዎችን እያጠጣ ገቢ ቢያገኝ፣ ልጆቹን እያጠጣም ምንዳውን ቢያስብ ምናለበት?’
ኹራሳኒዩ:— ‘አላደርገውም። ለአላህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በቂያማ ቀንም ከጌታዬ ዘንድ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው።’
ሽማግሌው:— ሰውየውን ልብሱን ጎተተውና ‘ና ተከተለኝ። ዲናሮችህን ውሰድና ሌሊቱን እንድተኛ ተወኝ። ይህንን ገንዘብ ካገኘሁበት እለት ጀምሮ ሰላም አላገኘሁም’ አለ።

ኢብኑ ጀሪር ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ባለ ዲናሩ ሰውየ ከሽማግሌው ጋር ሄደ። ተከተልኳቸው። ሽማግሌው ከቤቱ ገባ። መሬት ቆፍሮ ዲናሮቹን አወጣና ‘ገንዘብህን ውሰድ። አላህን ይቅር እንዲለኝና ከትሩፋቱ እንዲለግሰኝ እለምነዋለሁ’ አለ።”
ኹራሳኒዩ:— ተቀበለና መውጣት አሰበ። በሩ ጋር ሲደርስ እንዲህ አለ:— ‘አንተ አዛውንት ሆይ! እኔ አባቴ ሶስት ሺህ ዲናር ትቶ ሞቷል፣ አላህ ይዘንለትና። እና ‘ሲሶውን አንተ ይበልጥ ይገባዋል ለምትለው ስጥ’ ብሎኝ ነበር። በዚህ ከረጢት ውስጥ ያስቀመጥኩት ለሚገባው ለመስጠት ነው። በአላህ ይሁንብኝ! ከኹራሳን ከወጣሁ ጀምሮ እዚህ እስከምደርስ ድረስ ካንተ የበለጠ የሚገባው ሰው አላየሁም። ስለዚህ ውሰደው አላህ ይባርክልህና። አማናህን ስለተወጣህ፣ በድህነትህ ላይ ስለታገስክ አላህ በመልካም ይመንዳህ’ አለና ገንዘቡን ትቶ ሄደ። ሽማግሌው ተነስቶ አላህን እየተማፀነ ማልቀስ ያዘ። እንዲህም አለ:— ‘የዚህን ገንዘብ ባለቤት (ሟቹን) በቀብሩ ውስጥ አላህ ይዘንለት። በልጁም ይባርክለት።’

ምንጭ:— [ጀምሀረቱል አጅዛኢል ሐዲሢያ፞ህ: 251]

ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:—
{ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا (٢) وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا}
"ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰፅበታል። አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።" [አጦ፞ላቅ: 2–3]
=
https://t.me/IbnuMunewor


ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus dan repost
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ያ ጀመአ ሰላም ናችሁ የ1000 ብር ፕሮግራማችን ተጀምሯል አንዳንድ ወንድሞች ማስገባት ጀረዋል አላህ በዛችሁን ይክፈላችሁ።

የ50K አላማችንን ተባብረን እንወጣዋለን!!

Account
:1000392464305 NAME:MISBAH ALI

ከላካችሁ በኋላ  በ👇👇 አሳውቁን!!
User Name:
@Miss2425
                    :
@Biniyamin23
መጠየቅ የምትፈልጉት ነገር ካለ!
Phone no_=
+251924253738
                   =
+251965561416

جزاكم الله خير الجزاء ونفع بكم
https://t.me/tuaifetumensurah


ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus dan repost
የብዙዎቻችሁ መልክት ደርሶኛል ለሁላችሁም ጀዛኩሙሏህ ኸይረን ለዱዓችሁ ለሁሉም የሱና ወንድም እህቶቻችን አሏህ ያቆይልን አላህ ይጠብቅልን እናንተንም !

አሏህ ምንም ሳያጎድለን መልሶ ላገናኘን አልሃምዱሊላህ !


ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus dan repost
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

ያጀመዓ እንዴት ናችሁ ...?

በአሏህ እገዛ ትላንት ከእስር ቤት ተፈተናል አልሃምዱሊላህ !

ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ አቡ መርየም

اللهم لك الحمد

ولله الحمد والمنة


قنات لشيخ جمال الذهبي الصباح dan repost
🔗 📌 بِسْــــمِ ﷲِ الرَّحْمـٰــــــــنِ الرَّحِيمِ 📌


🎁በሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ተቀርተው የተጠናቀቁ ቂርአቶች


📚الأصول الثلاثة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/130

📚الأصول الستة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/139

📚القواعد الأربعة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/139

📚أصول السنة
https://t.me/SheikhJemalZehabi/160

📚لمعة الإعتقاد
https://t.me/SheikhJemalZehabi/173

📚العقيدة الواسطية
https://t.me/SheikhJemalZehabi/199

📚العقيدة الإسلامية
https://t.me/SheikhJemalZehabi/226

📚  شروط لا إله إلا الله ونواقض الإسلام
https://t.me/SheikhJemalZehabi/287


=ሪከርዶችን በነዚህ ሊንኮች ታገኙታላቹህ

🔗 https://t.me/SheikhJemalZehabi


ጃዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የዳዕዋና የቂርዓት ማዕከል {Official Channel } dan repost
የደዕዋ ድግስ በደሴ ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ


ታላቅ የምስራች ለደሴ እና አከባቢዋ ሙስሊም ማህበረሰብ  በሙሉ እነሆ የፊታችን እሁድ በቀን 25/05/2017 ዓ·ል  በአላህ ፍቃድ የወሎ መናገሻ እና እንብርት በሆነችው  ደሴ  ከተማ ወሎ ባህል አምባ አዳራሽ  ከአድስ አበባ ፣ ከአፋር፣ ከኸሚሴ፣ እና  ከሌሎችም ሀገራት በሚመጡ ብርቅዬ መሻይኾችና ኡስታዞች   ከጧቱ 3:00 ጀምሮ  እጅግ በደመቀ እና ባማረ መልኩ  የደዕዋ ድግስ ተዘጋጅቶ ሲጠብቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው
 
የዕለቱ ተጋባዥ መሻይኾችና ኡስታዞች


① ሸይኽ አወል አህመድ አል ኸሚሴ
ርዕስ:– ረመዷንን እንዴት እንቀበለው

② ኡስታዝ አብዱረህማን ሰዒድ(አቡ ሒዛም)
ርዕስ:–ሱናን አጥብቆ መያዝና ቢድዓን መራቅ(መጠንቀቅ)

③ ኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ:– የተውሂድ አሳሳቢነትና የሽርክ አደገኝነት እንድሁም በምን ላይ ነው  አንድ የምንሆነው

④ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር (ሙሀመድ አህመድ)
ርዕስ:–ኢልምን በመፈለግ ላይ መበርታት፣የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን ምን መምሰል አለበት እና መልካም ስነ ምግባር

ማሳሰቢያ:–ለሴቶችም በቂ ቦታ አለ‼

N·B :– የቻናልና የግሩፕ ባለቤቶች በሙሉ ሼር በማድረግ ተደራሽ አድርጉት 

አዘጋጅ፦ የጀዕፈር ኢብኑ አቢ ጧሊብ የደዕዋና የቂርዓት ማዕከል


URGENT: - የደሴ ከተማና በዙሪያዋ ያላችሁ ሙስሊም ማህበረሰብ በሙሉ ፕሮግራሙ ዘንድ ትታደሙ ዘንድ ጥሪ አድርገንላችኋል።

ጆይን ይበሉ ቻናል

t.me/yedesse_selfyochi_yedewa_channel
ግሩፕ

https://t.me/yedesse_selfyochi_group


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ
=
1- ቅደመ ሁኔታ ላይ የተንጠለጠለ ፍቺ (الطلاق المعلق) ማለት ለምሳሌ ሚስቱ ከሆነች ጓደኛዋ ዘንድ መሄዷ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ተረዳ። "አትሂጂ" ቢላት ልትቆም ፈቃደኛ አልሆነችም። በዚህን ጊዜ "ዳግመኛ እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" በማለት ተናገረ። ይህንን ካለ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ወርዶ ፍቺው ይቆጠራልን?
=> ይህንን ሸርጥ የተናገረው ብትሄድ የእውነትም ሊፈታት ወስኖ ከሆነ በመሄዷ ብቻ ኒካሑ ይወርዳል። ፍቺ ተፈፅሟል።
=> ሸርጡን ያስቀመጠው መፍታትን አስቦ ሳይሆን ለማስፈራራት ከሆነ ኒካሑ አይወርድም።

2- ያስቀመጠው ቅድመ-ሁኔታ ቀድሞ በተፈፀመ ጉዳይ ላይ ይሰራልን? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀመጠ። ይህን ከማለቱ በፊት ቀድማ ሄዳ ከሆነ ፍቺው ይቆጠራልን?

=> ቅድመ ሁኔታውን ሲያስቀምጥ ሃሳቡ ቀድማ ሄዳም ከሆነ "ፈትቻለሁ" የሚል እሳቤን የሚያጠቃልል ከሆነ ፍቺው ይቆጠራል። ከዚህ በኋላ ቢከሰት የሚለውን ብቻ ነይቶ ካወራ ግን በቀደመ ተግባር ፍቺ አይታሰብም።

3- "ይህንን ካደረግሽ ፍቺ ነሽ" ቢልና አውቃ ሳይሆን ረስታው ያንን ነገር ብትፈፅም ኒካሑ ይወርዳልን?
=>አይወርድም።

4- ካስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መመለስ ይችላል? ለምሳሌ "እከሊት ቤት ከሄድሽ ፍቺ ነሽ" የሚል ሸርጥ አስቀምጦ ነበር። ያስቀመጠውን ሸርጥ አንስቶ ቢፈቅድላትና ከዚያ በኋላ ብትሄድ ኒካሑ ይወርዳል?
=>ትክክለኛው አቋም አይወርድም የሚለው ነው።

5- ሚስቱን በሆነ ሰበብ ከፈታ በኋላ ሰበቡ ልክ እንዳልሆነ ካወቀስ? ለምሳሌ፦ ሚስቱ በሆነ ጉዳይ ላይ እንደዋሸችው ወይም ከቤቱ ወንድ እንዳስገባች ተረድቶ ፈታ። ሲያጣራ ግን ጉዳዩ እሱ እንዳሰበው እንዳልሆነ አወቀ። ኒካሑ ይወርዳል ወይ?
=>ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ እና ኢብኑ ዑሠይሚን ኒካሑ አይወርድም ብለዋል።
=
ከሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ፈትሑል ዐላም ኪታብ (8/543 - 554) ተጨምቆ የቀረበ።
ማሳሰቢያ:- መልእክቱ እንዲህ አይነት ጉዳይ ከገጠመ ሑክሙ ምን እንደሆነ ለማስታወስ የቀረበ እንጂ የኒካሕ እና የፍቺ ጉዳይ በሃላፊነት ሊያዝ ተገቢው ክብደት ሊስሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ኢብኑ ሐዝም እንዲህ ይላሉ፦
"ወደ ጓደኛህ ነፍሱን የሚያሳምመው እና በማወቁ የማይጠቀምበት የሆነን ነገር አታድርሰው። ይሄ የወራዶች ተግባር ነው።" [ረሳኢሉ ኢብኒ ሐዝም፡ 106]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
9. ኢብኑ ዐብዲል በር አልማሊኪ (463 ሂ.)፡-
“አላህ የት ነው?” የሚለውን ሐዲሥ አውስተው እንዲህ ብለዋል፡-
فَعَلَى ذَلِكَ جَمَاعَةُ أَهْلِ السُّنَّةِ وَهُمْ أَهْلُ الْحَدِيثِ وَرُوَاتُهُ الْمُتَفَقِّهُونَ فِيهِ وَسَائِرُ نَقَلَتِهِ كُلُّهُمْ يَقُولُ مَا قَالَ اللَّهُ تَعَالَى فِي كِتَابِهِ ﵟ‌ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰﵞ وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ فِي السَّمَاءِ وَعِلْمَهُ فِي كُلِّ مَكَانٍ
“የአህለ ሱና ጀማዐ በዚህ ላይ ነው ያሉት። እነሱም የሐዲሥ ባለቤቶች፣ ዘጋቢዎቹ፣ በሱ ላይ አዋቂዎቹና ሌሎችም አቀባባዮቹ በሙሉ የላቀው አላህ በመፅሐፉ {አረሕማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ} ያለውን ያስተጋባሉ። አሸናፊውና የላቀው አላህ በሰማይ እንደሆነና እውቀቱ በሁሉም ቦታ እንደሆነም እንዲሁ።” [አልኢስቲዝካር፡ 7/337]
وفيه دليلٌ على أنَّ اللهَ عزَّ وجلَّ في السَّماءِ على العَرْشِ، مِنْ فَوْقِ سَبْعِ سَمَاوَاتٍ، كما قالتِ الجماعةُ، وهوَ منْ حجَّتهم على المعتزلةِ، والجهميَّةِ، في قولهم: إنَّ الله عزَّ وجلَّ في كلِّ مكانٍ، وليسَ على العرشِ
“በዚህ ውስጥ አህሉ ሱና ወልጀማዐ እንዳሉት አላህ - ዐዘ ወጀል - ከሰባት ሰማያት በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ ማስረጃ አለ። ይሄ አላህ - ዐዘ ወጀል - ‘ሁሉም ቦታ ነው፤ እንጂ ዐርሽ ላይ አይደለም’ በሚሉት ሙዕተዚላና ጀህሚያ ላይ ከሚጠቅሱ ማስረጃ ነው።” [አተምሂድ፡ 7/129]

10. ኢስማዒል ብኑ ሙሐመድ አተይሚይ (532 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
أهل السّنة يَعْتَقِدُونَ أَن الله ... عَلَى الْعَرْش كَمَا قَالَ تَعَالَى: {ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰ} وَأَنه ينزل كل لَيْلَة إِلَى السَّمَاء الدُّنْيَا كَمَا جَاءَ فِي الحَدِيث
“የሱና ሰዎች የላቀው አላህ {አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} እንዳለው በዐርሹ ላይ እንደሆነ በየሌሊቱም ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ ያምናሉ። [አልሑጃ፣ ተይሚይ፡ 2/432]

11. የሕያ ብኑ አቢል ኸይር አልዐምራኒይ (558 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
عندَ أصحابِ الحديثِ والسُّنةِ أنَّ الله سبحانهُ بذاتهِ، بائنٌ عَنْ خَلْقِهِ، على العرشِ استوى فوقَ السَّمواتِ
“የሐዲሥና የሱና ተከታዮች ዘንድ የሚታመነው አላህ ጥራት ይገባውና በዛቱ ከፍጡራን ተነጥሎ ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነ ነው።” [አልኢንቲሷር፣ ዐምራኒይ፡ 2/607]

12. ኢብኑ ሩሽድ አልማሊኪይ (595 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
القولُ بالجهةِ: وأمَّا هذهِ الصِّفَةُ فلمْ يزل أهلُ الشَّريعةِ منْ أولِ الأمرِ يثبتونها لله سبحانه وتعالى، حتَّى نَفَتْها المعتزلةُ ثمَّ تبعهم على نفيِّها متأخرو الأشعريةِ، ... وظواهرُ الشَّرعِ كلُّها تقتضي إثباتَ الجهةِ
“በ(ላይ) አቅጣጫ ማመን፡ ይህቺ መገለጫ ከመጀመሪያው ዘመን ጀምሮ የሸሪዐ ባለቤቶች ለአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ከማፅደቅ ወደ ኋላ ብለው አያውቁም። ሙዕተዚላዎች እስከሚያስተባብሏትና የኋለኛው ዘመን አሽዐሪዮች በማስተባበል ላይ እስከሚከተሏቸው ድረስ ማለት ነው። … የሸሪዐ ግልፅ ማስረጃዎች እንዳለ የ(ላይ) አቅጣጫን ማፅደቅን ያመላክታሉ።” [መናሂጁል አዲላህ ፊ ዐቃኢዲል ሚላህ፣ ኢብኑ ሩሽድ፡ 176]

አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ለሚለው አንዳች ማስረጃ ባይኖር እንኳን “... ከላይም፣ ከአለም ውጭም፣ ከአለም ተነጥሎም አይደለም” ብሎ ለማመን ወይ የቁርኣን ወይ የሐዲሥ ወይ ደግሞ የኢጅማዕ ማስረጃ ማቅረብ ግድ ነበር። ይህም ይቅር። ቢያንስ ከሶሐቦች፣ ከታቢዒዮችና ከአትባዑ ታቢዒን ይህን የሚያስረዳ ሀሳብ ማቅረብ ነበረባቸው። ይህንን የሚያሳይ ደግሞ ቅንጣት የላቸውም። ይልቁንም የቁርኣንም፣ የሐዲሥም፣ የኢጅማዕም ማስረጃዎች ያሉት ከነሱ ተቃራኒ ነው። እኛ እንደምናቀርበው ተፃራሪ ማስረጃ ቢያቀርቡ ሁለቱም ተፈትሾ፣ ተመዝኖ ሚዛን የሚደፋው ይታይ ይባል ነበር። እነሱ ግን ባዶ ኪሳቸውን እያፏጩ መጥተው የኡማውን ኢጅማዕ እንደ ዋዛ ሊንዱ ነው የሚገላገሉት። የጌታ ቃል፣ የመልእክተኛው ንግግር፣ የቀደምቶች ኢጅማዕ በአንድ ቃለ ያስተጋቡትን ሐቅ በ‘ተእዊል’ም ይሁን በሌላ ማመሀኛ ለማስተባበል መሞከር ድርቅና እንጂ ምን ሊባል ይችላል?!

እንግዲህ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ቁርኣኑም፣ ሐዲሡም፣ ኢጅማዑም አረጋገጠ። ከዚህ በኋላ ግራ ቀኝ ማማተር ከሙስሊም ይጠበቃል ወይ?! ዐብዱላህ ብኑ ዐዲይ አሷቡኒይ “ወይ ቁርኣን፣ ሱናና ኢጅማዕ ነው። ካልሆነ ግን (እንደ መነኩሴዎች) ዝናር መታጠቅ፣ ቢጫ መልበስና ጂዝያ መክፈል ነው የሚቀረው” ይላሉ። [ዘሙል ከላም፡ 1/27] አደገኛ ምርጫ! በነዚህ አካላት የተሸወድክ ወገኔ ሆይ! ግዴለህም ንቃ። መንቃትህ የሚጠቅመው አንተን ነው። አላህ ልብህን ለሐቅ ክፍት ያድርግልህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
በአሕ ^ባሽ ስብከት ለተሸወዳችሁ ወገኖች!
~
አላህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለው ዐቂዳ ከጊዜ በኋላ የመጣ እንግዳ እምነት አድርገው ሲሞሏችሁ አትሸወዱ። የቀደምት ዑለማኦችን ንግግር ተመልከቱ። ከዚህ በፊት በሂጅራው አቆጣጠር ከ300 አመት በፊት የሞቱ ዓሊሞችን ኢጅማዕ ዝርዝር አሳልፌያለሁ። አሁን ደግሞ ከዚያ በኋላ ግን ከኢብኑ ተይሚያ መምጣት በፊት ያለፉ ዓሊሞችን እጠቅሳለሁ።

1. አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ (324 ሂ.) የአህሉ ሱናን ኢጅማዕ ሲዘረዝሩ ዘጠነኛው ኢጅማዕ ላይ እንዲህ ብለዋል፡-
وأجمعوا على... أنه تعالى فوق سماواته على عرشه دون أرضه، ... وليس استواؤه على العرش استيلاء كما قال أهل القدر؛ لأنه عز وجل لم يزل مستولياً على كل شيء
“የላቀው አላህ ... በምድሩ ሳይሆን ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነም ኢጅማዕ አድርገዋል። የኢስቲዋኡ ፍቺ ቀደሪያዎች (ሙዕተዚላዎች) እንደሚሉት መቆጣጠር ማለት አይደለም” ብለዋል። [ሪሳላህ ኢላ አህሊ ሠግር፡ 130 - 131]

2. አቡ አሕመድ አልከርጂይ አልቀሷብ (360 ሂ.) ከዐርሹ ላይ መሆኑን መካድን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡-
مكابرة العقول ومقابلة الأمة عالمهم وجاهلهم بالخلاف فيما ليس فيه لبس ولا إشكال
“ይሄ ህሊናን መቃረን፣ መድበስበስና ችግር በሌለው ጉዳይ ላይ ከአዋቂ እስከ መሀይም ህዝበ ሙስሊሙ ጋር በልዩነት መላተም ነው።” [ኑከት፣ ቀሷብ፡ 1/429]

3. አቡበክር አልኢስማዒሊይ (371 ሂ.)፡- የሐዲሥ ምሁራንን ጥቅል ዐቂዳ ባሰፈሩበት ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-
ويعتقدون أن الله تعالى مدعو بأسمائه الحسنى وموصوف بصفاته التي سمى ووصف بها نفسه ووصفه بها نبيه ﷺ، خلق آدم بيده، ويداه مبسوطتان ينفق كيف يشاء، بلا اعتقاد كيف، وأنه عز وجل استوى على العرش، بلا كيف.
“የላቀው አላህ እራሱን በሰየመባቸው፣ እንዲሁም መልእክተኛው ﷺ እሱን በጠሩበትና በገለፁበት መልካም ስሞቹና መገለጫዎቹ የሚጠራና የሚገለፅ እንደሆነ፤ ኣደምን በእጁ እንደፈጠረ፣ - አኳኋን ሳይሰጡ - እጆቹ የተዘረጉ እንዳሻው የሚለግስባቸው እንደሆኑ፣ እርሱ - ዐዘ ወጀለ - ያለ እንዴት ከዐርሹ በላይ ከፍ ያለ እንደሆነ ያምናሉ።” [ኢዕቲቃዱ አኢመቲል ሐዲሥ፡ 49 - 50]

4. ኢብኑ አቢ ዘይድ አልቀይረዋኒይ አልማሊኪይ (386 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
“ምሁራኖች ከተስማሙባቸው ሃይማኖታዊ ጉዳዮች፣ እንዲሁም ቢጥጣሱ ቢድዐና ጥመት ከሆኑት ሱናዎች ውስጥ አንዱ እርሱ፡-
فوقَ سماواتِهِ على عَرْشِهِ دونَ أرضِهِ وأنَّهُ في كُلِّ مكانٍ بِعِلْمِهِ
“በምድሩ ሳይሆን ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ ላይ እንደሆነና በእውቀቱ ግን በሁሉም ቦታ እንደሆነ ማመን ነው።” [አልጃሚዕ፣ አልቀይረዋኒይ፡ 107 - 108]

5. ኢብኑ በጧህ አልዑክበሪይ (387 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
أجمعَ المسلمونَ مِنَ الصَّحابةِ والتَّابعينَ، وجميعُ أهلِ العلمِ مِنَ المؤمنينَ أنَّ الله تباركَ وتعالى على عَرْشِهِ، فَوْقَ سَمَاواتِهِ، بائِنٌ منْ خَلْقَهِ، وعِلْمُهُ مُحِيطٌ بجميعِ خَلْقِهِ
“ሙስሊሞች ሁሉ ከሶሐቦችና ከታቢዒዮች፣ ከአማኞች የሆኑ ሁሉም ምሁራኖች የላቀው አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከሰማያቱ በላይ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ በአንድ ድምፅ ተስማምተዋል። እውቀቱ ሁሉንም ፍጡሮቹን ያካበበ ነው።” [አልኢባናህ፣ ኢብኑ በጧህ፡ 7/136]

6. ኢብኑ አቢ ዘመኒን አልማሊኪይ (399 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
وَمِنْ قَوْلِ أَهْلِ اَلسُّنَّةِ: أَنَّ اَللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ خَلَقَ اَلْعَرْشَ وَاخْتَصَّهُ بِالْعُلُوِّ وَالِارْتِفَاعِ فَوْقَ جَمِيعِ مَا خَلَقَ، ثُمَّ اِسْتَوَى عَلَيْهِ كَيْفَ شَاءَ، كَمَا أَخْبَرَ عَنْ نَفْسِهِ فِي قَوْلِهِ: ﵟ‌ٱلرَّحۡمَٰنُ ‌عَلَى ‌ٱلۡعَرۡشِ ‌ٱسۡتَوَىٰﵞ
“ከአህሉ ሱና አቋሞች ውስጥ አላህ - ዐዘ ወጀለ - ዐርሹን እንደፈጠረና ከፈጠረው ሁሉ ለይቶ በላይ በመሆንና ከፍ በማለት ለይቶታል የሚለው ነው። ከዚያም እንደሻው በሱ ላይ ከፍ አለ። {አረሕማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ} ሲል ስለ ራሱ እንደተናገረው።” [ኡሱሉ ሱና፣ ኢብኑ አቢ ዘመኒን፡ 88]

7. አቡ ዐምር አዳኒይ (440 ሂ.) ረሒመሁላህ፡-
የአህሉ ሱናን መዝሀብ ዐቂዳዊ ነጥቦች ባሰፈሩበት ኪታባቸው ውስጥ እንዲህ ብለዋል፡-
ومنْ قولهم: إنَّهُ سُبْحَانَهُ فَوْقَ سماواتهِ مستوٍ عَلَى عرشه، ومُسْتَوْلٍ على جميعِ خلقهِ، وبائنٌ منهم بذاتهِ، غيرُ بائنٍ بعلمهِ، بلْ علمهُ محيطٌ بهم
“ከአቋሞቻቸውም ውስጥ እርሱ ጥራት ይገባውና ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ ከፍ ብሎ ነው ያለው የሚለው ነው። በሁሉም ፍጡሮቹ ላይ ተቆጣጣሪ ነው። በዛቱ ከነሱ የተለየ ሲሆን በእውቀቱ ግን የተለየ አይደለም። ይልቁንም እውቀቱ እነሱን ያካበበ ነው።” [አሪሳለቱል ዋፊያህ፡ 129 - 134]

8. አቡ ዑሥማን አሷቡኒይ (449 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
ويعتقدُ أهلُ الحديثِ ويشْهدونَ أنَّ الله سبحانه وتعالى فوقَ سَبْعِ سَمَاوَاتٍ على عَرْشِهِ كمَا نطقَ بهِ كتابُهُ، ... وعلماءُ الأمَّةِ وأعيانُ الأئمَّةِ مِنَ السَّلفِ رحمهمُ الله لم يختلفوا في أنَّ اللهَ تعالى على عَرْشِهِ، وعَرْشُهُ فَوْقَ سَمَاوَاتِهِ، يُثْبتونَ لهُ منْ ذلكَ ما أثبتهُ الله تعالى ويؤمنونَ بهِ ويُصدِّقونَ الرَّبَّ جلّ جلاله في خبرهِ، ويُطْلقونَ ما أَطْلقهُ سبحانه وتعالى من استوائهِ على العرشِ ويُمرُّونهُ على ظاهِرِهِ
“የሐዲሥ ተከታዮች: የጠራውና ከፍ ያለው አላህ - ቁርኣኑ እንደተናገረው - ከሰባቱ ሰማያ በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ ያምናሉ፤ ይመሰክራሉ። … የህዝበ ሙስሊሙ ምሁራን፣ የቀደምት ታዋቂ ኢማሞች - አላህ ይዘንላቸውና - የላቀው አላህ ከዐርሹ በላይ በመሆኑና ዐርሹም ከሰማያቱ በላይ በመሆኑ ላይ አልተወዛገቡም። በዚህ ላይ የላቀው አላህ ያፀደቀውን ለሱ ያፀድቃሉ። ያምኑበታልም። ልቅናው ከፍ ያለውን ጌታም በንግግሩ ያምኑታል። የጠራውና የላቀው አላህ ከዐርሹ በላይ ስለመሆኑ የተናገረውን ያስተጋባሉ። በይፋዊ (በዟሂር) መልእክቱም ያስኬዱታል። [ዐቂደቱ ሰለፍ ወአስሓቢል ሐዲሥ፡ 36 - 37]


ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus dan repost
በአካውንቴ ላይ የገባ 5000 ብር (አምስት ሽህ ብር ) አለ የኔ ነው የሚል ማንኛውም አካል የባንክ ሪሲትና ስክሪን ሹት ይዞ መቅረብና መውሰድ ይችላል ::
0933519871
ጀማል እንድሮ

@JemalEndroAbuMeryem

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15427


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
(من رأى منكم منكرا فليغيره بيده فإن لم يستطع فبلسانه فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان).
"ከናንተ መጥፎን ነገር የተመለከተ በእጁ ይቀይረው (ያስወግደው)። ካልቻለ በምላሱ። ካልቻለ ደግሞ በልቡ። ይሄ ግን ደካማው ኢማን ነው።" [ሙስሊም: 186]
ከሐዲሡ የሚወሰዱ ቁም ነገሮች:–

① ከመጥፎ መከልከል ነፍስ ወከፋዊ ሃላፊነት እንደሆነ፣
② ከመጥፎ መከልከል የተለያዩ ደረጃዎች ስላሉት ሁኔታዎችን እና ተገቢ እርምጃዎችን መለየት እንደሚያስፈልግ፣
③ በእጅ ወይም በአንደበት ጥፋትን ለማስወገድ አቅም እንደሚያስፈልግ፣
④ ጥፋትን በልቡም የማይጠላ ሰው ኢማኑ ከዝቅተኛ ወለልም በታች በመውረዱ ከባድ አደጋ ላይ እንደሆነ
⑤ ኢማን ከልባዊ እምነት ባለፈ ተግባርንም እንደሚጨምር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
#አስቸኳይ የቁርኣን አስተማሪ ይፈለጋል
መርከዝ አት ተውሒድ የቁርኣን ሒፍዝ አስተማሪዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል
~ቁርኣንን በጥሩ ሁኔታ የሐፈዘ እና ጠንካራ ሙራጀዓ ያለው
~የቁርኣን ሸሃዳ ያለው ቢሆን ይመረጣል
~መሰረታዊ የዐቂዳ እና የፊቅህ እውቀት ያለው
~ብዛት: 1
~ፆታ: ወንድ
~የቅጥር ሁኔታ: አዳሪ ሙሉ ሰዓት
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኡስታዞች ከታች ባሉት አድራሻ ያናግሩን
@durise


ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ታላቅ የምስራች ለእህቶቻችን

በእህታችን ኡሙ ሙንዚር ቁርአን ከቃኢዳ እስከ ሂፍዝ መቅራት ለምትፈልጉ በውስጥ ግቡና አናግሯት !

@Umumunzirazg32

በቁርአንም በመንሃጅም ጠንካራ እህታችን ነች አላህ ይጨምርላት አላህ ኢኽላሱንም ይወፍቃት !


https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/15417


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
የደዕዋ ፕሮግራም
~
ዛሬ ቅዳሜ ቀጥታ ከዙህር ሶላት በኋላ
ቦታ፦ አፍንጮ በር ፣ አቅሷ መስጂድ

ተጋባዥ እንግዶች
አቡል ዐባስ
እና
ኢብኑ ሙነወር

በ 6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማ0 የተሰናዳ


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ካለመማር የማይሻል መማርማ አለ
~
አዎ አለመማር ያሳፍራል፣ ያስቆጫል እንጂ አያኮራም። በተለይ በዚህ ዘመን ያለው አለመማር ቀደም ባለው ዘመን ከነበረው አለመማር የከፋ ጉዳት አለው። ቆም ብሎ ያስተዋለ ብዙ ሰበዞችን መምዘዝ ይችላል።
መማር የአስተሳሰብ አድማስን ያሰፋል። የማስተዋል አቅምን ያዳብራል። ሌላው ቀርቶ በሃገራችን ተጨባጭ የዲን ሰዎች እንኳ አካደሚ ትምህርት መማራቸው ይህንን ካላገኙት የተሻለ ብስለትና አቀራረብ ሲንፀባረቅባቸው፣ ያልተማሩት ደግሞ በዚህ ረገድ የጎላ ክፍተት ሲታይባቸው ያጋጥማል። ሁሉን ማለቴ አይደለም።
ግን መማር ምንድነው? ካምፓስ ደርሶ መመለስ ነው መማር? ዲግሪ መቁጠር ነው መማር? እንግሊዝኛ መቀላቀል ነው መማር? መማር ምንድነው?
በርግጥ መማር ብዙ እርከን አለው። ቀለም መቅመስ፣ ክፍል መቁጠር፣ ዲግሪ መደርደር ብቻውን መማር አይደለም። መማር መለወጥ ነው። መማር ለህይወት ዋጋ መስጠት ነው። መማር በህሊና መኖር ነው። መማር ለወጡበት ማህበረሰብ ቅን መሆን ነው። መማር ለራስ የማይወዱትን ነገር ሌሎች ላይ አለማድረስ ነው። ይሄ ደግሞ ጥልቅ ንባብ፣ ማሰላሰል፣ አእምሮን ማስፋት፣ የተማሩትን ሆኖ መገኘት ይጠይቃል። በሃገራችን ተጨባጭ አብዛኛው "ምሁር" በዚህ ረገድ ሲታይ ተምሯል ለማለት ይከብዳል።

የትምህርት ስርአታችን በራሱ በሳል ትውልድ የሚመረትበት ከመሆን ይልቅ ለሃገር ፀር፣ ለወገን ጠንቅ የሆኑ መርዛማ ትውልዶችን ወይም ሻል ካለ ካንገት በላይ ሳይሆን ካንገት በታች የሰፉ ሆድ አደር አድር ባይ የሃገር ሸክሞችን ነው እያመረተ ያለው። የትምህርት ስርአታችን አባት አጥቷል። የተቋቋመበትን አላማ ዘንግቷል። በርካሽ ጥቅማጥቅም ፍትህ እየሸጠ ያለው ዳኛ፣ ethicሱን የረገጠ ሃኪም፣ የህዝብ እንባ የማይገርመው civil servant፣ የሃገርን እድገቱ በራሱ የተንጣለለ ቪላ እና የተንደላቀቀ ህይወት የሚመዝን ሹመኛ፣ ጥላቻ እየቸርቸረ በህዝብ ስም የሚነግድ የደም ነጋዴ የሆነ ፖለቲከኛ፣ ሚዲያን ያክል ትልቅ የለውጥ መሳሪያ ይዞ ሳለ ድባቡን እንዳለ በክፋት፣ በአድር ባይነት፣ በአርቲቡርቲ የሞላው ጋዜጠኛ፣ ... የትምህርት ስርአታችን እንዲህ አይነት ጃርቶችን ነው ያፈራውና እያፈራ ያለው።

የማህበረሰብን ለዘመናት የዘለቀ በሰላም አብሮ የመኖር እሴት የሚንድ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ፣ በህዝብ መሃል መርዝ የሚዘራ መርዝ ትውልድ ቢማርም አልተማረም። ይህ ዘር እየመነዘረ ለተማሪዎቹ ውጤት የሚሰጥ "ምሁር" ተምሯል ሊባል አይችልም። ይሄ ሃይማኖት እየለየ ታዳጊ ልጆችን ከትምህርት ገበታ እየገፋ ያለው ገ ልቱ ፍጡር ለስሙ ካምፓስ ተመላልሷል እንጂ አእምሮው የሸረሪት ድር ያደራበት ኦና ቤት ነው። አልተማረም። የገዛ ወገኑ በኑሮ ስንክሳር ጎብጦ፣ በመከራው ላይ መከራ፣ በችግሩ ላይ ችግር የሚደራርብ ህሊና ቢስ ፖለቲከኛ ከተማሩት የሚቆጠር አይደለም። ወጣቱ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሲሄድ እየተመለከተ እውነቱን የማይጋፈጥና መንጋ የሚፈራ አድር ባይ ምሁር ከመሀይም አይሻልም። ከወጣበት ማህበረሰብ ይልቅ ለአላፊ ስርአት ጥብቅና እየቆመ በወገኑ መከራ ላይ አይኑን ጨፍኖ ምናባዊ የተድላ ዓለም ያለን ያህል ሰርክ የሚያሰኩር "ሊቅ" ሞኑን ተማረው?! ይሄ መደ ንቆር እንጂ መማር አይደለም።

እና ምን ለማለት ነው? ሰው በሃገራችን ተጨባጭ መማርን ቢወቅስ አትፍረዱበት ለማለት ነው። ሃሳቡ ልክ ባይሆንም ጤነኛ ምሳሌ አጥቷል። ከተማሩት የሚያየው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው። የመማር ትርጉሙ ምን እንደሆነ እንዲደበዝዝበት ተደርጓል። ተምሯል፣ ተመራምሯል፣ ለሃገር ለወገን ይጠቅማል ብሎ ተስፋ የጣለበት አካል ጭራሽ ተስፋውን የሚነጥቅ ሲሆንበት እንዴት ግራ አይጋባ?!
"እዩልኝ ስሙልኝ ሰው ይፈርዳል በኔ
በግንቦት አግብቻት ወለደች በሰኔ" አለ ግራ የገባው። ግራ የገባው ሰው ብዙ ይላል። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ምሁር ነገር ላልተማረው ቀርቶ ህሊና ላለው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው። እና ያልተማረው ምን ያድርግ? ባየው ፈረደ። ቢሆንም! ቢሆንም! ቢሆንም አለመማር አያኮራም። አለመማር ይሻላል እያልክ በነውርህ እንዳትመፃደቅ። አለመማር ስንኩልነት እንጂ ጌጥ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.