༆ የፍቅር ክሊኒክ ༆™🥀🌹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Kitoblar


🔔🔔 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ 🔔🔔❓
📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
📱➡️የ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
📱➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
📱➡️የ ድርጅት ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሚዲያ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች ✅📢 በተመጣጣኝ ዋጋ💯💯💯💯💯💯
@Yefiker_clinic98

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ከBETTING ውርርድ እንዴት ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንደሚችሉ ማወቅ ይፈልጋሉ? በወር ከ100,000 እስከ 1,000,000 ብር! አው ከሆነ መልስህ/ሽ Join✅
የምትለውን በመንካት ይቀላቀሉን! ህይወትህን አሁኑኑ ቀይር ❗️✅


ማርያምን ዝም ብላችሁ join በሉ
😂😂😂ጥርሳችሁ እስኪሰበር ነው ምትስቁት ግን በዋላ ጥርሳቹ ተሰብሮ ክፈል የለም😁😁 ስሞትላቹ ተቀላቀሉት 🙏


እንዲያ_ነኝ 🥹

:
:
« ሳቄ መለያዬ ነው። ለመሳቅ መስፈርት የለኝም። ሰዎች በሳቄ ነው የሚያስታውሱኝ። ለመደሰት ትንሽ ነገር የሚበቃኝ ሰው ነኝ። ተው ዝም ብለክ አትገልፍጥ ሲሉኝ ግራ ይገባኛል። አሁን መሳቅ ፈገግ ማለት ምን ችግር አለው እላለሁ። አይገርምም ግን እያደግኩ ስመጣ ግን ነገሮች እየተቀያየሩ መጡ። ሰዎች ቁም ነገር አልባ እና ሁሌም ህፃን አድርገው ይመለከቱኝ ጀመር።
አንተ አይገባህም! አንተ ምን አለብህ? እንተስ የደላው የለም ይሉኛል። ከፍቶኝ እንኳ ከፍቶኛል ስላቸው ከቀልድ ይቆጥሩታል!
ለካ አንዳንዴ ፈገግታና ሳቀ ሰው ያሳጣል! ለካ ከቁም ነገረኛ ለመቆጠር ትንሽ መጨፈገግ፣ ሳቅና ፈገግታን ማፈን ይጠይቃል። አሁን አሁን እንደ ድሮው ባይሆንም እስቃለሁ፣ ግን እንደ ድሮው ሳቄ ቶሎ አይመጣም።
እኔኮ ስንት ነገር በውስጤ አፍኜም እስቃለሁ። የሚያባብለኝ ስለሌለም እንዲሁ እስቃለሁ። የሚጠይቀኝ ባይኖር ሳቅና ፈገግታ ለሚያበዛ ሰው ስለ ልቡ ደህና መሆንና ደስተኛ ስለመሆኑ መጠየቅ ነውር ተደረገ እንዴ እላለሁ። ደስተኛ ነው ተብሎ ተፈርዶበት አድማጭ አጥቶ፣ የልቡን ለማውራት ሲሞክር አትቀልድ እየተባለ እንዲሁ እንደሚስቅ ሰው ግን የሚያሳዝን ሰው ግን አለ? ሃሃሃ… ነገሩ ግን ያስቃል። እኔ ግን አሁንም መሳቅ አላቆምኩ ምኑ ጋር ነው ጥፋቴ እስኪ ንገሩኝ እእእእእ.............

{ ብቻ እኔ እንዲያ_ነኝ! » }


ከተመቻቹ ÷

                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


.     ም.1 #የመጨረሻው ክፍል

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_24

...ላይ ሊያሳርፈው ሲል ራሴን ከሆስፒታሉ ጥግ ላይ ተኮራምቼ ሳላስበው ይዞኝ ከተመመው የሰመመን እንቅልፍ ጉዞ ተመልሼ ከእንቅልፌ ነቃሁ ደህና መሆኔን አላመንኩም ራሴንም ጠርጥሬ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ደጋግሜ ሰውነቴን እየደባበስኩ ደህንነቴን አረጋገጥኩ...እኔ ብዙ ጊዜ ነፍሴን ያስጨነቃትን ነገር ነው በህልሜ ማየው...እየደባበስኩ ደህንነቴን እየተመለከትኩ ሳለ አይኔ የቅድስቴ በድን ላይ አረፈ እዛው እንደተንጋለለ ነበር ማንም አልነካውም ቀስ ብዬ ተጠጋሁ በእጄም እጇን ነካሁት ገላዋ ከቀረዶ በልጦ ቀዝቅዟል የሷን በድን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩኝ ሳለ በድንገት የእግር ኮቴ ሰማሁ ወዲያውኑ አጠገቤ ካለው ክፍል ገብቼ ራሴን ከሚመጣው ሰው ሸሸኩኝ እየመጣ የነበረውም ሰው ያ አረመኔ ጨካኝ ገዳይ ነበር በድኑን ሊወስድ እንደመጣ ገመትኩኝ ልክም ነበርኩ ልክ በድኑ ጋ ሲደርስ በርከክ አለና እላዯ ላይ የደረቀውን ደም በጣቱ ፈቅፍቆ ወደ አፉ ሰደደው ቀምሶትም በደም የበለዘ ጥርሱን ፈገግ አደረገ...ከዛም ፀጉሯን ይዞ እያንፋቀቀ መሬት ላይ እየጎተተ ይዟት መሄድ ጀመረ እኔ ካለሁበት ክፍል ትንሽ ራቅ ሲል ርቀቴን ጠብቄ መከተል ጀመርኩኝ በድን ሳይና በደም ስጨማለቅ የመጀመሪያዬ ነው ነገር ግን ከዚህ በፊት ይህን ሁሉ ክስተት እንደተመለከተ ሰው ልቤ ደንዳና ሆኗል...ብቻ አንድ ነገር መሆን አለበት ከዚህ አካባቢ እነዛን ሶስት አረመኔዎች ገድዬ እወጣለሁ ወይ ደግሞ እንደጓደኞቼ እዚሁ እቀበራለሁ ስጋዬንም ይቀራመቱታል እንጂ መቼም ቢሆን አልሸሽም...ትንሽ እንደተጓዘም በህልሜ ወዳየሁት መበለቻ ክፍል ይዟት ገባ ይሄን ሰው ማጥቃት ካለብኝ እንደዚህ ክፍል ሊያመቸኝ የሚችል የለምና እራሴን በጥንቃቄ አዘጋጀሁ ልክ ክፍሉ በር ጋር ስደርስ አንገቴን ወደ ውስጥ አስግጌ ተመለከትኩ ክፍሉ ፀጥ ረጭ ብሏል አንድም ሰው አልነበረም የቅድስቴም በድን የለም ወደ ክፍሉም ዘለቅ ብዬ ገባሁ እስካሁን ያላየሁት የተለየ በር ተከፍቷል ወደሗላም ተመልሼ የሚከተለኝ ሰው አለመኖሩን አረጋገጥኩ በተከፈተው በርም ቀስ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ነገር እጅግ የሚሰነፍጥ ከባድ የስጋ ሽታ ክፍሉ ላይ ሰፎበታል ሽታውን መቋቋም ስላልቻልኩ ወዲያውኑ ተመለስኩኝ ከዛም አንድ ሀሳብ አሰብኩኝ ከውስጥ የለበስኩን ቲሸርት ቀድጄ አፍንጫዬንና አፌን ሸፈንኩበት ወደ ውስጥም አመራሁ አልፎ አልፎ ቢሆን ሽታው ወደ ውስጤ ይገባል ነገር ግን ከመጀመሪያው የተሻለ ነበር ይህ ክፍል የተለየ ክፍል ነው እንደሌሎቹ ያን ያህል ብርሃን የለውም ጨለም ያለ ነው...አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ውስጥ ገብቻለሁ ነገር ግን ከፊት ለፊቴ ከሚታየኝ የላስቲክ መጋረጃ በቀር አንዳች ነገር አይታይም ወደ ላስቲኩም እርምጃዬን ጀመርኩ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው እንቅስቃሴዬን የማረገው ከቅድሙ ይልቅ ነበር እየበረታ መጣ ቢሆንም ግን ገዳይን ለመግደል ጉዞ ላይ ነኝ ላስቲኩን ገለጥ አድርጌ ወደ ውስጥ ገባሁ አይኔም ቀድሞ ያረፈው ወደላይ ከተንጠለጠሉት በላስቲክ የታሰሩ ነገሮች ላይ ነበር ምን እንደሆኑ ግን መለየት አልቻልኩም በእያንዳንዱ በተሰቀሉት ነገሮች በታች ለሁላቸውም ጠረጴዛ አለ መስመራቸውን ጠብቀው ነበር በረድፍ የተደረደሩት እየተጓዝኩም ወደ መሃላቸው ተጠጋሁ ወደ አንዱም የታሰረ ላስቲክ ቀረብ ብዬ ስመለከት ውስጡ ነጫጭ የስጋ ትሎች ይርመሰመሳሉ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ወደሗላ ስመለስ ከአንዱ የላስቲክ እስር ጋር ተጋጨሁ ሲንቀሳቀስም ድምፅ አወጣ በሁለት እጆቼም ይዤ ለማቆም ሞከርኩኝ ነገር ግን ያ ክፉ ሰው ድምፁ ወደተሰማበት ቦታ ሲመጣ ኮቴው ተሰማኝ ይሄንንም ባረጋገጥኩ ጊዜ ከአንዱ ጠረጴዛ ስር ተደበኩኝ የሆነ ስለት መሬት ላይ እየጎተተ እንዳለ ከሚሰማው የሚሰቀጥጥ ድምፅ ተረዳሁ እኔም የያዝኩን ስል ቢላ አሰናድቼ መጠበቄን ጀመርኩ ጠረጴዛዎቹ ረዘም ባለ ላስቲክ ስለተሸፈኑ  ከስር ያለውን ነገር ካልተገለጠ በቀር በቀላሉ አያሳዩም ይሄ ነገር ትንሽም ቢሆን ሰላም ሰቶኛል መሬት ላይ ሲጎተት የነበረው የስለት ድምፅ አሁን ላይ ወደ ጠረጴዛዎቹ ላይ የተቀየረ ይመስላል...ይህንንም ከምሰማው ድምፀሸ ለይቻለሁ...እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትምዝግጁ ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ  ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...................


                 "
#የጠፋው_ሬሳ"
                "
#የጠፋው_ሬሳ"
               "
#የጠፋው_ሬሳ"
              "
#የጠፋው_ሬሳ"

  ምዕራፍ
#አንድ በዚህ መልኩ ተጠናቋል
  ምዕራፍ ሁለትንም ለመቀጠል የእናንተ ፍላጎት ይወስናል በcomment box ውስጥ ተነጋገሩ
         በቅርብ ቀን እንጀምራለን


አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ በውስጥ መስመር አድርሱኝ

👉
@Chanaz_72
👉
@Firaan90

ምዕራፍ 2  ___በቅርቡ....

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


ዘንድሮስ Nursing ተማሪ በዛ

አለመማር Ayshalm😂

እየሄዳችሁ✌️


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_23


...የማየውን ማመን አቃተኝ ኮቴውን ወይም ድምፁን አልሰማሁኝም ግን አጠገባችን ተገኝቷል ቅድስቴ እንዳለችውም ይህ ሰው በአንድ መናፍስታዊ አገዛዝ ስር እንዳለ ውስጤ አረጋገጠልኝ...ሰውዬውን ከጀርባዋ እንደተመለከትኩት የቅድስቴ ስም ጠርቼ ወደራሴ ጎተትኳት ተያይዘንም እሷ ከላይ እኔ ከታች ሆኜ ወለሉ ላይ ወደቅን አንገቴን ከፍ አድርጌ ስመለከት ሰውዬው የለም ትቶን እንደሄደ አስቤ ደስ አለኝ "አይዞሽ ቅድስቴ ተርፈናል ሌሎቹን ፈልገን ከዚ እንሄዳሀን" አልኳት ነገር ግን መልስ አልሰጠችኝም...አይርገበገብም እንጂ አይኖ ተከፍቷል በጣም ግራ ተጋባሁ ሰውዬው ምንም ሲያረግ አልተመለከትኩትም ነበር እና ምን ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል...ደግሜ ደጋግሜ ስሟን ጠራሁት ግን ምንም አይነት ምላሽ አልሰጠችኝም ነበር ፊቷ ላይ የመጎዳት ነገር አይነበብበትም ቀስ አድርጌ ከላዬ ላይ አንስቼ ወገቧን ደገፍ አድርጌ በጀርባዋ ሳስተኛት የዛገ የሚመስል ስለታማ ብረት በጉሮሮዋ ወጣ ከድንጋጤዬ የተነሳ እጅግ በብዙ ድምፅ ጮውኩኝ ደጋገምኩት አይኔንም ከሷ ላይ መልሼ በዳዴ ከአጠገቧ ሸሸሁ አንዱ ጥግ ላይ ሆኜ ተኮራምቼም አነባሁኝ ያ አረመኔ ሰውዬ እኔን ለምን እንደማይገድለኝ ትንግርት ሆኖብኛል... ቅድስቴ ወለሉ ላይ እንደተንጋለለች ነው እኔ ደግሞ እሷን ማየት ፈርቼ ከአንዱ ጥግ ላይ ነኝ...አሁን መቋቋም የማልችለው ገደብ ያጣ ቁጣ ውስጤ መንፎልፎል ጀመረ ግን ደግሞ የቅድስቴን ሞት ሳይ ጓደኛዬን ያላተረፈ እልህ ብዬም ራሴን አኮማሽሻለሁ...የተቀመጥኩበት ሆኜ ራሴን ከግድግዳው እያጋጨሁ ምንም ሳላወራ መራር እንባዬን አፈሰስኩ አለቀስኩ የእንባ ከረጢቴም እስኪደርቅ ድረስ...ክፉኛ ራስ ምታትም ስቃዬን አበዛው...ሳላስበው እዛው ከተቀመጥኩበት ስፍራ እንቅልፍ አሸለበኝ በስቃይ የዛለ ሰውነቴ ከዚ በላይ የመቆየት አቅም አልነበረውም ነበር...ይመስለኛል ለሰዓታት ያህል ቁጭ ባልኩበት ስፍራ ተኝቻለሁ...እንደነቃሁም እንደምንም ብዬ ወደ ቅድስቴ በድን ዞር አልኩኝ ነገር ግን ቅድስቴ አልነበረችም ነበር ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነሳሁ አይኔንም ጠራርጌ በድጋሜ ተመለከትኩ ቅድስቴ ፈፅሞ የለችም...እንደ ፈጣሪ ቃል የጓደኞቼ በድን ከአፈር ሳይዋሃድ በሰው አውሬ ተበልቶ አለቀ ይሄ ምነኛ የሚያም እና የማይሽር ቁስል እንደሆነ እኔና እኔ ነኝ የምናውቀው...ቀስ ብዬ በድኗ ወደነበረበት ወለል ተጠጋሁ መሬት ላይ እየጎተተ እንደወሰዳት የደም ምልክቱ ያሳያል የጣልኩትን ቢላ አንስቼ ደሙን እየተከተልኩ ቀስ ባለ እርምጃ መሄድ ጀመርኩኝ እነሱ ወዳሉበት ክፍል በሚወስደው በር በኩል ይጠቁማል የደም ምልክቱ እኔም ያለ አንዳች ፍራቻ በተረጋጋ እና ማስተዋል በሞላበት እርምጃ መጠጋቴን ቀጠልኩ..."ከሞት በላይ ምንም ሊመጣ አይችልም ቀኔ ከሆነ ትንታም ይገለኛል አይደለም ይሄ ክፉ አረመኔ ሰው" እያልኩኝ ውስጤን ለጭካኔ እያነሳሳሁ እና እያጀገንኩ ገዳይን ለመግደል በተጠንቀቅ ራሴን አዘጋጀሁ...የደሙ ምልክት ብዙ ጋውኖች ወደተሰቀሉበት ክፍል ይጠቁማል የሮቤል በድን ወደነበረበት...አሁን በጣም ድንጋጤዬ መጣ እነዛ ንፋስ የሚቆርጡ የሚመስሉ ስለቶች የቅድስቴ ገላ ላይ ሊያርፉ እንደሆነ ገብቶኛል ይሄኔ እርምጃዬን ጨመር አድርጌ ግን ደግሞ ጥንቃቄ ሳይለየኝ ወደ በሩ ተቀረብኩኝ አልተዘጋም ነበር ገርበብ እንዳለ ነው አንገቴን ወደ ውስጥ ቀስ ብዬ ላኩት ሰውዬው ለሮቤል ሲያረግ የነበረውን ሁሉ አድርጓል ከጋወን እስከ ጓንት ድረስ ትጥቁን አማልቷል የቀረው ቢኖር ያ የዋይታ እና የሰቆቃ ነገር ግን እሱን የሚያስደስተው እና ሰላም የሚሰጠው ድምፅ ብቻ ቀርቷል እንደጠበኩትም ያንን የሚሰቀጥጥ የስቃይ ዋይታ ከፈተው አሁን በይበልጥ ከፊል ሰውነቴን ወደ ውስጥ አስገብቼ ሁኔታውን መከታተል ጀመርኩ ለሮቤል እንዳረገው ሁሉ ለቅድስቴም ዘይት ጥዷል እያፏጨ እና እየተንቀሳቀሰ ስለቶቹን መመራረጥ ጀመረ በድንገት ዋይታው ፀጥ አለ ሰውዬውም ከእንቅስቃሴው ተገታ ባለበትም ቦላ በአርምሞ ቆመ እኔም አመሉን ስለማውቀው ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረኩም ነበር ትንሽ እንደቆየ ጩኸቱ ጀመረ በዚ ጊዜ የሰውነቴ ክብደት በበሩ ቀድሞ በገባው እግሬ ላይ ስለበር ድካም ተሰማኝና ራሴን ለማሳረፍ ወደነበርኩበት ቦታ ልመለስ ስል አነስ የምትለዋ ሴትዮ ከፊት ለፊቴ ነጭ ጋወን ለብሳ የብረት መዶሻ ይዛ ቆማለች በጣም ደነገጥኩኝ ደነዘዝኩኝም ሴትየዋ ጊዜ አልፈጀችም ነበር ወዲያውኑ በመዶሻው ግንባሬን ስትለኝ በሩን በርግጄ ወለሉ ላይ ተዘረጋሁ እይየተስለመለመ ወደላይ ስመለከት አረመኔው ሰውዬ መጥረቢያውን ከፍ አረጎ መሀል ጭንቅላቴ...........


part #24  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

7.2k 0 18 62 108

 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_22

...ብልጭ ድርግም በሚለው የሆስፒታሉ መብራት የሆነ ሰው ይታየኛል አሁን ፊቴን አኮሳትሬ ግንባሬን ጨምድጄ እልሄን ሰብስቤ ወደፊት መጠጋቴን ጀመርኩ የጓደኞቼን ደም ለመበቀል ከመፈለጌ የተነሳ ወደኔ እንኳን እስኪመጣ አልጠበኩትም ራሴ ተጠጋሁት የያዝኩትን ቢላ ዘቅዝቄ እጀታውን በማርያም ጣቴ ጋር አድርጌ ስለቱን ወደ ክርኔ አስደግፌ በለዘበ አረማመድ መጠጋቴ ቀጠልኩ ነገር ከኔ ተቃራኒ ጥግ ላይ ያለው ሰው አይንቀሳቀስም ለምን እንደሆነ ባላውቅም እኔ ግን በድፍረት እና በንዴት እየተጠጋሁት ነው...የሆስፒታሉ መብራት ብልጭ ድርግሙን ትቶ ቀጥ ብሎ በራ ጥግ የተመለከትኩት ነገር አይደለም ሊገለኝ ይልቁና በፍርሃት ተሸማቆ ራሱን አሳንሶ ተኮራምቶ ፊቱን ሸሽጎ ተቀምጧል..."እንደ ወንድ ተነስተህ ና እንደ ፈሪ አትሸፋፈን እንደ ገዳይ ፊት ለፊት ውጣ አትርመጥመጥ" አልኩት ንግግሬን በእርጋት ጀምሬ ንዴቴ ሲብስ እየጮውኩኝ ነገር ግን አሁንም ዝምታ ነበር መልሱ...ወደሗላ አድርጌ የነበረውን ስለት ወደ ፊት መልሼ ደረቱ ላይ ለመሰንቀር ወደ ተቀመጠበት ስፍራ ኮቴ ቢስ በሆነ እርምጃ ተጠጋሁት ነገር ግን ከሗላይ በሰከንድ ሽርፍራፊ እጅግ ፈጣን ሰው አለፈ...ከመቅፅበትም ፊቴን መልሼ የያዝኩን ስለታማ ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን አንዳች ያጠቃሁት ፍጡር የለም ከአጠገቤ ያለው የሆስፒታሉ ክፍል አሁን እንደተከፈተ ያስታውቃል እንቅስቃሴውን እንኳን አላቆመም...በጥሞና ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ግን ማንም አልነበረም ከቆምኩበት ሁለት ከፍል አለፍ ብሎ የሚገኘው ሶስተኛው ክፍል ሲከፈት ተሰማኝ ሆስፒታሉ ፀጥ ብሎ ስለነበር ሲከፈት ያለው የበር ድምፅ ይሰማል "ሲጢጥ" ሲል....አሁን መሃል ላይ ገብቻለሁ ከፊትለፊት የሆነ ሰው አለ ከሗላ ደግሞ ተኮራምቶ የተቀመጠው ፡...ዞር ብዬ ጀርባዬን ቃኘው ማንም ያ ሰው አሁንም ኩርምት  እንዳለ ነው የመግደልም አቅም ያለው አልመሰለኝም ልክ እንደኔና ጓደኞቼ ጥቃት የደረሰበት ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ ይሄን ሁላ ማሰላስለው ሲከፈት ድምፁ ወደተሰማኝ በር እያመራሁ በአይኖቼም መለስ ብዬ ጀርባዬን እየተመለከትኩ ነው አሁን ክፍሉጋ ልደርስ አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶኛል የቀረኝንም እርምጃ እግሬን አንስቼ ልራመድ ስል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ ከመቅፅበትም አጠገቤ ያለው ግድግዳ ላይ ተደግፌ ቁልቁል ወርጄ ድምፄን አጥፍቼ ፀጥ አልኩኝ በጨለማው መሀል የትልቅ ከስክስ ጫማ  ድምፅ ተሰማኝ ሰፋ ያለ የእግር አጣጣል እንዳለው ከምሰማው የእግር ኮቴ ተረዳሁ ውስስጤ ፍርሃት የሚባል የለም በቀል እንጂ ነገር ግን ጨለማወው ነገሮችን በብዙ እያከበደብኝ ነው "ቢሆንም ግን ገድዬው ወይ ገሎኝ ከዚ አረመኔ ነፍሰ በላ ጋር እለያያለሁ" አልኩኝ ለራሴ እርምጃው እየቀረበኝ ነው የያዝኩትን ስለት በተጠንቀቅ አዘጋጅቼ እየጠበኩ ነው...በድንገት መብራቱ ፏ ብሎ በራ ከተቀመጥኩበት ተስፈንጥሬ ተነስቼ የእግር ዱካው ይሰማኝ ወደነበረው ስፍራ የያዝኩትን ስለታም ቢላ ሰነዘርኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያውኑ ጎላና ጎርነን ባለ ድምፅ ልብን የሚያርድ ሳቅ ተሰማ ባለሁበት ተንበረከኩ እንደሚዲህ ህፃን ቀዳዴ እየሄድኩ ግራና ቀኜን ተመለከትኩ ነገር ግን ምንም የለም ነበር ሳቁ ሳቅ ብቻ አይደለም አንዳች ሃይል አለው ቁጣዬን ነጠቀኝ እልሄን በፍርሃት ለወጠው በቀሌን የሽሽት አደረገው በጣም ተደነኩኝ አብዝቶም ገረመኝ ካልመጣ ስል የነበርኩት ቤት ልውጣ ብዬ ተጨነኩኝ ጣቶቼ ቢላውን መጨበጥ እስኪያቅታቸው ተብረከረኩ በዛ የውድቅት ምሽት ከየት መጡ የማይባሉ ቁራዎች ሆስፒታሉ ውስጥ ተመሙ ራሳቸውን ከግድግዳ ጋር እያጋጩ ኮሪደሩን በደም አጨቀዩት አብዝተውም ይጮሁ ነበር መሃል ላይ ሆኜ በግንባሬ ከወለሉ ተዋድጄ ሞቴን መጠበቅ ጀመርኩኝ አቀርቅሬ ባለሁበት ጊዜ አንገቴ ላይ ያለው የብር ሃብል ወለሉ ላይ ተመለከትኩት ግንባሬንም ቀና አድርጌ የዓለም ሁሉ ቤዛ የሆነው አንድ አምላክ የተሰቀለበት መስቀል ነበር መስቀሉ ላይም የኔ እና የዓለሙ አዳኝ እንዳላቀረቅር አቀርቅሮ አየሁት ህመሜን ታሞልኝ ተቸንክሮ አየሁት....እሱን ባየው ጊዜ ንዴቴ እና እልሄ መታደስ ጀመረ ስልቱን ጨብጬ በሁለት እግሬ ቆምኩኝ ነገር ግን ሆስፒታሉ በደም ጨቅይቶ የነበረው በቁራ ድምፅ የታወከው ስነሳ ግን ሰላም ነበር...መጀመሪያ ጥግ ላይ ካየሁት ሰው በቀር በድጋሜ ማንም አልነበረም ወደዛም ሰው ቀጥ ብዬ ተጠጋሁ ስደርስም "እባክህ አትግደለኝ እባክህ" እያለች ሳግ እየተናነቃት የምትማፀን ሴት ነበረች "አይዞሽ አልጎዳሽም ተነሺ" ስላት "ሜርሲዬ" ብላ አቀፈችኝ የመየውን ማመን አልቻልኩም ሞቱ ካልኳቸው ጓደኞቼ መሃል ቄድስቴ ነች "ቅድስቴ አንቺ ነሽ እንዴ ተጎዳሽ የሆንሽው ነገር አለ?" ብዬ ጠየኳት ሰውነቷን እየደባበስኩ "ምንም አልሆንኩም ባባን ወስዶታል ባርሳ ደሞ የት እንዳለች አላውቅም" አለችኝ "አታልቅሺ እናገኛቸዋለን" ብዬ አባበልኳትና እጇን ይዤ ወደ መውጫው ሳመራ "ሜርሲዬ ይሄ ለመገለን የሚፈልገው ሰው ትዝ ካለሽ ከወር በፊት ጠፋ የተባለ ሬሳ ነበር ሰዎችም እንደሚሉትም ሞቶ የተነሳ የመናፍስት እጅ ያለበት...እያለች እየነገረችኝ ሳለ ዞር ብዬ የምትለው ገርሞኝ እንግዳ ሆኖብኝም ልሰማ ስቆም ሰውዬው ከየት መጣ ሳይባል የእግሩ ዱካ ሳይሰማ አንዳችም ነገር ሳይታወቀን በንፋስ ፍጥነት ከቅድስታ ጀርባ ቆሟል..............


part #23  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

8.8k 0 20 40 131

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

             ተከታታይ ትረካ

#ክፍል_21


...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች አፌን በእጆቼ አንስቼ አይኔ እስከተከፈተልኝ ድረስ አፈጠጥኩኝ እሷ ግን ምንም አይነት ነገር ሳታወራ ረጋ ብላ በአትኩሮት ተመለከተችኝ ቁመቷ አጠር ያለ ነበር ከመደንገጤ የተነሳ ቃሎቼ መክነው አንደበቴም ተሳስሮ ነበር ትንሽ ወደ ቀልቤ ስመለስ አይኔን ወደታች ልኬ በእጇ አንዳች ነገር ከያዘች ብዬ ተመለከትኩኝ ነገር ግን ምንም አልያዘችም ነበር  በትንሹም ቢሆን ራሴን ማረጋጋት ችያለሁ ቀስ እያለች ወደኔ መጠጋት ጀመረች ቤቱ ያለው አንድ መውጫ እሱንም ደግሞ እሷ ዘግታዋለች ወደሗላ እንዳልሸሽ ጭራሽ ወደ ገዳዩ ነው ምገባው በዚ ግዜ አንዳች ነገር መወሰን እንዳለብኝ ተረዳሁ...እኔም ቀስ እያልኩ እጆቼን ጨብጬ ውስጤን አጠንክሬ ወደሷ መጠጋት ጀመርኩ መሞት እንደው የማይቀር ነው ቀኔ ከሆነ ልሙት ብዬ ራሴን አጀገንኩኝ በጣም ተቀራረብን ሳይቀደሙ መቅደም ነው ራሴን አዘጋጅቻለሁ "እሷ ቀድማ ከመታችኝ ነፍሴን እዚሁ ነው ምነጠቀው ስለዚህ መወሰን አለብኝ" ብዬ ለራሴ ነገርኩት በመሃላችን የአንድ እርምጃ ልዩነት እንደቀረን አሽቀንጥሬ ገፈተርኳት አጠገባችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ሄዳ ተዘረጋች እላዩ ላይ ያለውንም ዕቃ ናደችው ቤቱ ውስጥ ከፍተኛ የሁካታ ድምፅ ተሰማ ወዲያውኑ ከዛ ቤት በፍጥነት ወጣሁ ገፍትሬ የጣልኳት ሴትዮ "አንድዬ" ብላ ስትጣራ ሰማሁት አሁንም ከዛ ቦታ ለመውጣት የጀመርኩትን ሩጫ አላቆምኩም ዞር ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ላይ ቆሞ እየተመለከተኝ ነው ልክ ደረጃው ጋ ስደርስ በእጁ የያዘውን ወደኔ ወረወረው አንድ ደረጃ ከፍ ብል ኖሮ መጥረቢያው የሗላ ጭንቅላቴ ላይ ይሰነቀር ነበር...ነገር ግን ደረጃውን አልወጣሁትም ነበር "ትረፊ ያላት ነፍስ" አልኩኝ ለራሴ መጥረቢያው እንዳልመታኝ ሲመለከት ሴትየዋን ስጥላት ከወደቀው ዕቃ መሃል ብራማ አብረቅራቂ ቢላዋ ይዞ ወደኔ መገስገስ ጀመረ እኔም ለማምለጥ መሮጤን ቀጠልኩ ደረጃው እንደጨረስኩ ወደ ደረጃው የሚያስገባውን በር ዘጋሁት ነገር ግን ሰውዬው ለመክፈት ቅንጣት አላዳገተውም ነበር መጥረቢያውንም ቢላውንም ይዞ እየተከተለኝ ነው በጣም ፈጣን ነው ሲሮጥ አሁን ኮሪደሩ ላይ ወጥቻለው ከሆስፒታሉ ወጥቼ ወደ ውጪ ልሩጥ ወይስ ወዴት ልደበቅ አልኩና ትንሽ አመነታሁ ከዛም ሌሎቹን የታካሚ መኝታ ክፍሎችን ነበር ዝም ብዬ ከፈትኳቸው ከዛም እኔ ሆስፒታሉ አጠገብ ወዳለው ጫካ ውስጥ ተደበኩኝ የነበርኩበት ቦታ የሆስፒታሉን ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ነገር ግን ሰውዬውን አላየሁትም ነበር በጣም ተደናገጥኩኝ ይህ አወዛጋቢ ሰውዬ ወዴት እንደተሰወረ አስደነገጠኝ ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁኝ ሰውዬው አሁንም የለም ነገር ግን ከሆስፒታሉ ውስጥ የጫጫታ እና የዋይታ ድምፅ ተሰማኝ ይህ ሰው ጓደኞቼን አንዳች ነገር እንዳደረጋቸው ጠረጠርኩ ከዛም ካለሁበት ቦታ ስምዘገዘግ ወደ ውስጥ ገባሁ ሁሉንም ክፍሎች ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ጓደኞቼን ትቼ ከሄድኩበት ስፍራ አጣሗቸው ተንበርክኬም አፌን ከፍቼ ጮውኩኝ የቀረሁት እኔ ብቻ ኀኝ "ወንድ ከሆንክ ና ውጣ እንደ ድመት ተደብቀህ አታድን" ብዬ ጮውኩኝ ደጋግሜም አልኩት ያገኘሁትን ዕቃ ሁሉ ገለባበጥኩኝ ነገር ግን እሱ ዝርም አላለም ነበር ግድግዳውን ታክኬ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩኝ ከዛም ወዲያውኑ ማልቀሴን አቆምኩኝ ከተቀመጥኩበትም ተነሳሁ ቀጥ ብዬ መኪናችን ወደቆመበት ስፍራ አመራሁ ሻንጣዬን አውርጄ የእጅ ባትሪ አውጣሁ የለበስኩትን ቱታ በጅንስ ቀየርኩት ከስክስ ጫማዬንም አደረኩኝ ወፈር ያለ ጃኬት ደረብኩኝ ለምግብ ማብሰያ ከያዝናቸው ዕቃዎች ውስጤ ቢላ አነሳሁ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ለመወሰን ወስኛለሁ "ጓደኞቼን አስበልቼ እኔ ቆሜ አልሄድም ወይ እሱ ቆሞ አይሄድም" ብዬ ራሴን የንዴቴ ጥግ ላይ አድርሼ የሚያሳድደኝን ማሳደድ ጀመርኩ የሚፈልገኝን መፈለግ ጀመርኩ የሚያስፈራራኝን ደፈርኩት የሚያስጨንቀኝ ተዳፈርኩት በአንድ ነፍሴ አንድ ጊዜ ማልኩኝ ፍራቻ ከውስጤ ተመንቅሮ ወጣ ደም እንደጠማው መንፈስ ያን ክፉ ሰው እስካገኘው ጊዜው ረዘመብኝ ሴት ነች ወንድን የምትወልደው ሴት ነች የወንድ ልክ ሴትነት ምን እንደሆነ አሳየዋለሁ....የሆስፒታሉ መብራት አሁንም መጣ ቀረት እያለ ነው ነገር ግን ለኔ ምንም ነበር ቀድሞ ጨለማው ያስፈራኝ ነበር አሁን ግን እሱ ከፈራ ይፍራኝ...ጉዞዬን ቀጥያለሁ ሁሉም ክፍሎች እየገባሁ ተመለከትኩኝ ማንም አልነበረም ከጓደኞቼ ጋ የነበርኩበት ክፍልም ገባሁ አሁንም ማንም የለም ነገር ግን አንድ ነገር ቀልቤን ያዘው "ያ ሰው ጓደኞቼ ላይ ጥቃት ካደረሰ እንዴት ደም አልፈሰሰም" ብዬ ራሴን ጠየኩኝ "አምልጠው ቢሆንስ" እያልኩም ከራሴ ጋ ማውራት ጀመርኩኝ ደግሞም ቢያመልጡ እንደዛ አይነት የዋይታ ድምፅ ለምን...ከዛም ከክፍሉ ወጣሁ ወደገባሁበትም ስፍራ ተመለከትኩ ምንም የለም ነገር ግን በተቃራኒው ጥግ ላይ........

Part "22".............ይቀጥላል

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


አንድ ባለትዳርና የስድስት ልጆች አባት የሆነ ጎልማሳ ኦሾ ጋር ይመጣና  “በዘመኔ ሌላ ሴት ተመኝቼ አላውቅም በፍፁም! አሁን ግን አንዲት ሴት ማለም ከጀመርኩኝ ውዬ አድሬያለሁ፤ የአርባ ስምንት አመት ጎልማሳና የስድስት ልጆች አባት በዚያ ላይ ባለትዳር ሆኜ ሳለ ወደ ሌላ ሴት የመሳቤ ነገር ተገቢ ነው ትላለህ ?” ይለዋል። 

ኦሾም “ይልቁኑስ ተገቢ የማይሆነው ለአርባ ስምንት አመታት ራስህን ጨቁነህ መኖርህ ነው፤ ለዚህ እኮ ነው ወደ ሴት ልጅ መሳብ የጀመርከው። የሴት  ቁንጅና ሲታይህ ወደ ወጣትነትህ ተመለስህ ማለት ነው። ዛፎች ለምልመው ፣ አበቦች አብበው ፣ አታክልት አፍርተው ስታይ አልኖርህምን ሴትስ በውበቷ ተገልጣ አምራ ብትታይህ ችግሩ ምንድን ነው ? ፍርሃትህ የፍጥረትን ቁንጅናን እንዳያስክድህ ተጠንቀቅ..”



                     ፦ O S H O


                    


  ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

             ተከታታይ ትረካ

#ክፍል_20

....ሰውዬው ነበር እሱ ነገር ግን አልተመለከተኝም ነበር...ወደ ውስጥ ሲገባ ውጪ ላይ አንዳች የረሳው ነገር ያለ ይመስል ወደሗላ እየተመለከተ ነበር እኔም ይሄን ቅፅበት ተጠቅሜ ተደብቄ ወደ ነበረበት ስርቻ ተመለስኩ ግን ወደ ውጪ ሲመለከት የነበረው ሰውዬ ወዲያውኑ ከውስጥ አንዳች ነገር በልቡን የሳበው ይመስል በፍጥነት ዞረ ይመስለኛል ስደበቅ ያሰማሁት ኮሽታ ነው...ለደቂቃዎች በአፍንጫው እያነፈነፈ ቤቱ ውስጥ የገባውን እንግዳ ነገር ማሰስ ጀመረ ቅርቤ ስለነበር ይበልጥ ሰውዬውን መመልከት ቻልኩኝ ሁለቱም አይኖቹ ትክክል አይደሉም አቀማመጣቸውም ይለያል ከአይኖቹ ይልቅ አፍንጫውን አብዝቶ ይጠቀምበታል ነገር የአይኑ ብሌኖች ምስል ይከስቱ አይከስቱ እንጃ...በዚ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ሰውዬውን እየተመለከትኩት ሳለ በዕድሜ አነስ የምትለዋ ሴት "ለምን እዚጋ ቆም አንድዬ" አለችው በማይገባ ቋንቋ የሆነ ነገር ብሎ መለሰላት "ምንም የለም ሁሉም ሰላም ነው እናትህ እንደ ድሮው ፀጉርህን ልታበጥርልህ ነው ና ወደ ውስጥ እንግባ" አለችው እያባበለችና የሚወደውን ነገር እየነገረችው እሱም በሃሳቧ ተስማምቶ እቅፍ አርጓት ወደ ውስጥ ገቡ...ውስጤ ለሰውዬው እንደ ማዘን አረገው በሆነ አንዳች ክፉ ክስተት እና ገጠመኝ ለዚ እንደተዳረጉ ለማሰብ ሰከንድ አልፈጀብኝም "ብቻ ከዚ በፊት መልካም ቤተሰቦች የነበሩ እሱም መልኩና አስተሳሰቡ ልቡም ጨካኝ ሳይሆን ሩሩህ ሰው ነበር" እያልኩኝ ከራሴ ጋር ስለ ሰውዬው መነጋገር ጀመርኩ ከዛም ከተደበኩበት በጥንቃቄ ተነስቼ ከኔ ቀጥሎ የሚከሰተውን ትዕይንት ወደሚያሳየኝ የመጋረጃ ሽንቁር ተጠጋሁ ወዲያውኑ ትልቋ ሴትዮ ባለመደገፊያ የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጣለች እሱ ደግሞ አነስተኛ ወንበር ላይ ጀርባውን ሰጥቷት እግሯ መሃል ተቀምጧል በያዘችው ማበጠሪያ ሉጫ ፀጉሩን ወደሗላ በማበጠሪያ ታስተኛዋለች አንዳች አትናገርም ቃልም አይወጣትም ነገር ግን ከአይኗ የሚፈሰው እንባ ከእልፍ ድምፅ አልባ ቃላት የበለጠ ይናገራሉ በሚወርደው የእንባዋ ቦይ ላይ ብዙ ብሶቶቿ እና ችግሮቿ በግልፅ ይነበባሉ ፊቷ እንኳን እንደሚያለቅስ ሰው አልተኮማተረም አልተጨማደደም የማትናገረው ውስጧ ሚብሰለሰል እያደር ሚበላት ግን የማታከው አንዳች ነገር እንዳለ አሰብኩኝ..."አንዳንዴ ጥፍር ደርሶ የማያከው ቆዳ ስጋና አጥንትን አልፎ ከውስጥ የሚበላ ክፉ እከክ" አለ አልኩኝ ለራሴ ደሞም ልክ ነበርኩ በሴትየዋ ሁኔታ ከገባሁበት ሰመመን ስነቃ ሳላስበው ጉንጬ በእንባ ርሷል በጣም ደነገጥኩኝ ግራም ተጋባሁኝ እንዴት ሊሆን እንደቻለም ለራሴ ገረመኝ ግን በቃ ሆነ ልቤ እና አይኔ ተስማምተው በአንድነት አዘኑ በእንባዬም ገለፁት..."ግን የእውነትም እጅግ ያሳዝናሉ አንጀትም ይበላሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሰው ስጋ ይበላሉ እዚህ ቤተሰብ ላይ የተከሰተው አንዳች ክፉ ገጠመኝ ምን ሊሆን ይችላል እንዴትስ ሊሆን ቻለ" እያልኩኝ ራሴን መጠየቄን ተያያዝኩትን ከራሴ ንግግር ተመልሼ በድጋሜ አይኔን በመጋረጃው ሽንቁር ወደ ውስጥ ሰደድኩት ትልቋ ሴትዮ ፈትል የሚመስለው ነጭ ፀጉሯ ከጀርባዋ ላይ ተንጋሏል ከፊት ያለው የፀጉሯ ክፍል አልፎ አልፎ ጥቁር ጣል ጣል ብሎበት የተለየ ውበት ሰጥቷታል ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ማበጠሯን ተያይዛዋለች አነስ የምትለዋ ሴትዮ ግን ሰውዬውን ካስገባች በሗላ ደግሜ አልተመለከትኳትም ከነሱጋ አለመሆኗ ቢያስገርመኝም "ለምን" ብዬ ምጠይቀው ሰው የለ ግን ከአይኔ መሰወሯን አልወደድኩትም ውስጤ ተረብሿል... ነገር ግን ቀልቤ አሁንም እናትና ልጁ ላይ ነው...ከዛም እሱ በተራው ወደ ውስጠኛው ክፍል ገብቶ ውሃና የእግር መታጠቢያ አምጥቶ ቀስ እያለ አጠባት ከዛም ቅባት ነገር ይመስለኛል አነስቶ ከእናቱ ትይዩ ባለው የምግብ ወንበር ላይ ተቀምጦ በእርጋታ ያሻት ጀመር እሷም ፈገግ እያለች አይን አይኑን ትመለከተዋለች ነገር ግን አሁንም አይኗ ከማንባት አልቦዘኑም ነበር ያለመታከት ያነባሉ የእግር ጣቶቿን አንድ በአንድ እያረገ ዘና እንድትል የተቻለውን ይጥራል ደግሞም ከተቀመጠበት ተነስቶ ጉንጯ ላይ ሚንከራተተውን እንባ በመዳፉ ጠርጎ ግንባሯን ይስማታል...ምን አለ አንዳች ነገር ተከስቶ ወደ ቀድሞው በመለስኳቸው ብዬ ተመኘሁ...እዚ ቦታ ላይ ከዚ በላይ መቆየት እንደሌለብኝ ግልፅ ነው ቶሎም ተመልሼ ጓደኞቼን ከዚ አካባቢ ይዤ መሄድም እንዳለብኝ ግልፅ ነው...የውስጡን ትዕይንት ከምከታተልበት የመጋረጃ ሽንቁር አይኔን አንስቼ ወደ በሩ ስዞር አነስ ምትለዋ ሴትዮ................

Part 21....ይቀጥላል.........

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

11.9k 0 21 20 131

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

             ተከታታይ ትረካ

#ክፍል_19


...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደምንም ተረጋግቼ አንድ ስርቻ ጋር ተሸጎጥኩ አሁንም ፀጥታው እንደቀጠለ ነው ይመስለኛል ጆሯቸውን ቀስረው በድጋሜ የኔን ድምፅ እየጠበቁ ነው ማንም ከተቀመጠበት የተነሳ የለም...በዚህ ሰዓት ከተደበኩበት ቦታ ቀስ ብዬ በጥንቃቄ ተነሳሁ ልወጣ በሩ አካባቢ ስደርስ ሰውዬውም ሊወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሩ ተነሳ ወዲያውኑ ወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ ይባስ ብሎ ሰውዬው ሊወጣ ብሎ ወደሗላ መለስ አለ የጠረጠረው እንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝ "በቃ ከዚህ በሗላ ማምለጥና መትረፍ አይታሰብም" ብዬ ለራሴ ነግሬ ጭንቅላቴን ጉልበቴ መሀል አስገብቼ የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ እዛው በቃረቀርኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ከዛም እንደምንም ድፍረቴን ሰብስቤ ፍራቻዬን ተቋቁሜ ከአንገቴ ቀና ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ጋር አልነበረም በጣም ግራ ገባኝ ሲራመድ እንኳን ኮቴ አልተሰማኝም ነበር አሁን የባሰ ጭንቅ ሆነብኝ ሰውዬው ከየት እንደሚመጣ ለመገመትም ከበደኝ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተደበኩበት ተነስቼ ቅድም ውስጥ ያለውን ነገር እመለከትበት ወደነበረው የመጋረጃው ሽንቁር ተጠጋሁ ሁለቱ ሴቶች እንደነበሩት ናቸው በአርምሞ ሆነው የሮቤልን አካል ይመገባሉ ቀና ብለው እንኳን አይተያዩም ነበር ግን ከዛ አረመኔ ሰውዬ የተሻለ የተስተካከለ የፊት አቀማመጥ እና ጤናማነት ይታይባቸዋል በድንገት አይኔ ተወርውሮ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ሁለት የህፃናት ፎቶ ላይ አርፎ ቀረ "እነዚህ ብላቴናዎች ማን ሊሆን ይችላሉ" ብዬም አሰብኩ በድጋሜ በዛች ሽንቁር ዙሪያ ገባውን መቃኘት ጀመርኩ በድጋሜ አንድ ፎቶ ተመለከትኩ አንዲት መልከ መልካም እናት በጨርቅ የተጠቀለለ ልጅ አቅፋ ከሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ቆማ ያሳያል በእርግጥም ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ አሁን ያለንበት ቦታ ነው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር "ህፃን ታቅፋ ፎቶ ላይ ያለችው ሴት ማን ልትሆን ትችላለች" ብዬ ራሴን ጠየኩ ዳሩ መላሽ ባላገኝም በድጋሜ አይኔን ወርወር አድርጌ ሌላ ነገር ማየቴን ቀጠልኩ ፎቶዎቹ በአጠቃላይ ጥቁርና ነጭ ቀለመሸ ያላቸው ናቸው...አይኔን ግድግዳው ላይ ሳንከባልል አንድ መልከ ሸጋ ብላቴ ያለበትን ፎቶ ተመለከትኩ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቢከብድም ገዳዩ ሰውዬ ይሆን እንዴ ብዬም አሰብኩ ግን የማውቀውን የፊቱን ገፅታ እና አቀማመጡን ሳስበው ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችል ደመደምኩ ግን እነዚ የፎቶ ስብስቦች ያለ ምክንያት እንዳልተሰደሩም ተገንዝቤያለሁ በድንገት በዕድሜ ጠና ያለችው ሴትዮ ተነስታ ስመለከት ወደነበረው መልከ መልካሙ ብላቴና ፎቶ ጋር ጠጋ ብላ በእጆቿ እየዳበሰች በስስት አይን እየተመለከተች ድምፅ ሳታሰማ የእንባዋን ጎርፍ በጉንጯ ላይ ታወርደዋለች ከዛው ሌላኛዋ ሴት ተነስታ ከሗላ በኩል እቅፍ አርጋ የፊቷን የግራ ክፍል ጀርባዋ ላይ አስደግፋ ዝም ብላ አብራት ቆመች ከደቂቃዎች በሗላም ሴትየዋ ማልቀሷን አቆመች ወደነበሩበትም ተመለሱ ግን አሁንም ፊቷ አልተፈታም ነበር ሁለት እጆቿን በእልህ ጨብጣ ከንፈሯን ነክሳ በፍጥነት መተንፈስ ጀመረች ምን ሆነች ሳይባል በድንገት ተነስታ የክፍሉን ዕቃ አመሰችው በዚ ጊዜ ሰውዬው ድምፅ ሰምቶ ሊመጣ ይችላል ብዬወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ አሁን ንግግር ጀምረዋል "እባክሽ እባክሽ ተይ ተረጋጊ" ትላለች በዕድሜ አነስ የምትለዋ "ልጄን ልጄን ልጄን በሉብኝ አንድዬን የአይኔን ማረፊያ የፈጣሪዬን ስጦታ በሉብኝ" እያለች ድምፇን ከፍ አርጋ አምርራ ታለቅሳለች "ራስሽን አትጉጂ እባክሽን ተረጋጊ መድሃኒትሽን መውሰድ አለብሽ እንዲ መሆን የለብሽም የባሰ ታስጨንቂዋለሽ" አለቻት "ማነው ሚጨነቀው" ብዬ ወዲያውኑ ራሴን ጠየኩ "ሴትየዋ ልጄን በሉብኝ ብላ ነው ምታለቅሰው በሉብኝ ማለት ደግሞ ገደሉት ይመስለኛል እና ስለየትኛው ሰው እና ስለየትኛው ልጅ ነው እንደዚ ካየሽ ይጨነቃል" የምትለው ብዬ ከራሴ ንግግር ጀመርኩ የዚህ ቤተሰብ ውስብስብ ታሪክ ይበልጥ ዘልቄ እንዳውቃቸው አጓጓኝ ግን መሞትም እንዳለ አልዘነጋሁትም በድጋሜ ከተደበኩበት ተነስቼ ወደመጋረጃው ሽንቁር አመራሁ አሁን ፀጥታው ተመልሶ ነግሷል ሴትዬዋ መሬት ላይ ተኝታለች በዕድሜ አነስ የምትለው ደግሞ በተኛችበት ፀጉሯን እየደባበሰች ታፅናናታለች የሴትየዋ ጉዳት ከባድ እንደነበር መገመት ቀላል ነው ልጇን ምንም ያርጉት ምንም በብዙ ተጎድታለች ሰው ነችና አሳዘነችኝ አነስ የምትለዋ ሴት መድሃኒቱን እንድትውጥ አድርጋ አረጋጋቻት እዛው ቆሜ በመጋረጃው ሽንቁር እየተመለከትኩኝ ሳለ በድንገት በሩ ተከፈተ ስዞር..........

Part 20....ይቀጥላል.........

ቶሎ ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

 
   ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


'ካንቺ ጋራ ስሆን'😊 .....
ምሽቱ ይደምቃል ፣ ሀሳቤ ይሰምራል፣❤️
አስቀያሚው ያምራል 🤗፣
ጨለማው ያበራል ፡፡
ሰማሽኝ የኔ አለም ፡ ካንቺ ጋራ ስሆን ፣
ህይወቴ በሀሴት ፡ ፅዋ ትሞላለች🥰
ካንቺ ጋራ ስሆን አለም ለኔ እንዲህ ነች።




ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_18


...በድጋሜ "እርዱኝ አድኑኝ" ብሎ ድምፅ አወጣ በዚ ሰውዬው ቡታጋዙ ላይ ተጥዶ የነበረው የሚፍለቀለቅ ዘይት ከመቅፅበት አንስቶ ከፊቱ ጀምሮ እስከ እግሩ ድረስ ደፋበት ሮቤል አምርሮ ክፉኛ ጮኸ ግን ድጋሜ አልጮኸም ነበር ለዘላለሙ በዛው አሸለበ...ይሄን መቆጣጠር አልቻልኩም በዘይት የተጠበሰው የስጋው ሽታ ወደኔ ሲመጣ አጥወለወለኝ ሊያስመልሰኝም ዳዳሁ በብዙ ተፈታተነኝ...እንዳጋጣሚ ሰውዬው ለምን እንደሁ እንጃ ከክፍሉ ወጣ እኔም የሱን አለመኖር ጠብቄ ሚተናነቀኝን አስወጣሁት ከአንድ ደቂቃ በሗላ ሶስት ነጫጭ ሳህን አምጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠ ምን ሊያደርግ እንዳሰበ ምንም አልገባኝም የሩቤል አስክሬን ድርቅ ብሏል አንደበቱ ሊጮህ እንደተከፈተ በዛው ስላሸለበ አልተዘጋም ይሄ ሁሉ ነገር ሲደረግ አይኔን ገልጬ ማየቴ ራሴን እንደ ጨካኝ እንዳይ አድርጎኛል በሌላ በኩል ደግሞ ይሄን ሁላ ትዕይንት መቋቋሜ መልሶ ለራሴ ይደንቀኛል ሰውዬው አሁንም ከዘፈኑ እኩል እየተንቀሳቀሰ ሚከውነውን ይከውናል አንድ ተለቅ ብሎ ስፋት ያለው የሚያብለጨልጭ ስለታም ቢላ እና አነስተኛ ቢላ ይዞ ወደ ሮቤል በድን ተጠጋ ሊሆን ያለውን ማሰብ ለኔ ከባድ ነበር ይህ ከገመትኩት በላይ ክፉና አረመኔ ነው ሰው መባል ሁሉ የለበትም ሰይጣን ስጋ ለብሶ እንጂ...ሰውዬው መለስ ብሎ አነስ ያለ ወንበር ይዞ ወደ በድኑ ተመልሶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ ከዛም በትንሿ ቢላ አስክሬኑን መክፈት ጀመረ ለሚመለከተው የሚያክም እንጂ የሚበልት አይመስልም ዘየት በደንብ ያገኘውን የሰውነት ክፍል እየመረጠ መቁረጥ ጀመረ የቆረጠውንም የሰው ስጋ ባመጣቸው ሳህኖች ላይ እያስተካከለ መደርደር ጀመረ...ሲለው ደግሞ መሀል መሀል ላይ ከሚቆርጠው ስጋ እየቀመሰ ጭንቅላቱን በመነቅነቅ ይደነቃል ይሄን መመልከት ምነኛ አለመታደል ነው ግን ከቤት ወደዚ የመጣሁበትን ቀን አምርሬ ጠላሁት ሲበዛም ረገምኩት...ሰውዬው አሁንም እየቆራረጠ ነው ከትንሽ ደቂቃ በሗላ ሁለቱን ሳህኖች አንስቶ ከክፍሉ ወጣ ብዙም ሳይቆይ በድጋሜ ተመልሶ አንደኛውን ሳህን ይዞ ወጣ እኔም የሚሄድበትን ለመመልከት ብዙ ሳይረቅ ወደ በሩ ተጠጋሁ ሆስፒታሉ ውስጥ ከሚገኝ አንዱን በር ከፍቶ ሲገባ ተመለከትኩት የከፈተውንም በር ሳይዘጋ ወደ ውስጥ አመራ እርምጃዬን አጥፍቼ ያለውን ነገር ለመመልከት ወደ ውስጥ ገባሁ ግን ክፍሉ ባዶ ነበር በጣም ደነገጥኩኝ ወጥመድም መሰለኝ እዛው በቆምኩበት በድንጋጤ እያለከለኩ ተዟዟርኩኝ ግን ማንም አልነበረም የት እንደተሰወረ ግራ ሆነብኝ ነገር ግን የቆምኩበት ወለል እስካሁ ከረገጥኩት የወለል ድምፅ ይለያል ግድግዳ እና ጣሪያ ላይ ሲያማትር የነበረው አይኔን ቁልቁል ወደ ወለሉ ወረወርኩት እውነትም የቆምኩበት ወለል የተለየ ነበር ከላዩ ላይ ወረድኩና በጉልበቴ በርከክ ብዬ ጆሮዬን ላዩ ላይ ደቀንኩና ማዳመጥ ጀመርኩ በጣቶቼም ቆረቆርኩት ከሰማሁት ድምፅ በመናሳት ከታች የሆነ ክፍል እንዳለ ድምዳሜ ላይ ደረስኩ ውስጥ ያለውን ነገር ገብቶ ለመመልከት ወሰንኩኝ ከዛም ወለል መሳይ በሩን ለመክፈት መታገል ጀመርኩኝ ግን ብዙም አድካሚ አልነበረምና ተከፈተልኝ ቁልቁል ስመለከት ውስጡ ብዙም ብርሃን አልነበረውም ቢሆንም ግን የመመልከት ሀሳቤን አላስቀየረኝም ቀስ ብዬ እግሬን ከደረጃው ላይ አሳረፍኩ በአንድ እጄ በሩን ይዤ በጥንቃቄ ቁልቁል መውረድ ጀመርኩ አልፎ አልፎ ከሚታይ ወጋገን በቀር ክፍሉ ጨለማ ነው እቃ ነገር ጥዬ እራሴ ላይ ወጥመድ እንዳልሆን በጥንቃቄ መራመድ ጀመርኩ ወደፊት በተጠጋሁ ቁጥር ብርሃን እየበዛ መጣ ትንሽ እንደተራመድኩ የሚሳሳቁ የሰዎች ድምፅ ተሰማኝ "ያ ክፉ ሰው ብቻውን አልነበረም ሌሎች የሚያግዙት ሰዎች" አሉ አልኩኝ ለራሴ እርምጃዬን ጠብቄ ወደፊት መሄዴን ቀጠልኩኝ ጨዋታቸው ደርቷል ምን እንደሚባባሉ ግልፅ ባይሆንም ሳቃቸው ግን ይሰማል በነሱ ሁኔታ ከራሴ ጋር እያወራሁ ሳለ በድንገት ሳላስበው በእግሬ መሬት የነበረ ጣሳ ረገጥኩኝ የፈጠረው ድምፅ ለተንኮል ከፍ ያለ ነበር የደራው ጨዋታቸው እና የሞቀው ሳቃቸው በአንድ ጊዜ ፀጥ አለ በር ሲከፈት ያለው ድምፅ ተሰማኝ የሆነ ሰው ነገሩን ለማጣራት እየመጣ ይመስለኛል እንደዚ ባሰብኩ ጊዜ ከአካባቢው መራቅ ነበረብኝና የሆነ ጥግ ላይ ተደበኩ ግን ማንም አልመጣም ነበር በድጋሜ ቀስ ብዬ ወደፊ ተጠጋሁ ቅድም ሲከፈት የሰማሁት በር ይመስለኛል ከፊት ለፊት ክፍት ሆኖ ይታየኛል ጨዋታው በድጋሜ ደርቷል እየቀረብኩኝ ስሄድ ድምፃቸው ግልፅ እየሆነ መጣ ከእርምጃዎች በሗላ ወደ ክፍቱ በር ደረስኩ አንገቴን አስግጌ ውስጡን ስመለከት የተቀዳደና በደም የመነቸከ ነጭ መጋረጃ ተመለከትኩ ሰዎቹም ከመጋረጃው ጀርባ እንዳሉ ተረዳሁ ቀስ ብዬ ተጠጋሁና በቀዳዳው መመልከት ጀመርኩ ሰውዬው ጀርባው ለኔ ሰጥቶ ነው የተቀመጠው በሱ በስተቀኝ በኩል ተለቅ ያለች አሮጊት ትታየኛለች ከሷ ሴትዮ በመቀጠል ደግሞ ከሁለቱም በዕድሜ ምትበልጥ ሴት ከሱ ፊት ለፊት ተቀምጣለች በድንገት አይኔ የሚመገቡት ነገር አረፈ እሱን ባየው ጊዜ ሳላስበው ድምፅ አወጣሁ..............


part #19  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


🥀🖤
እሷ:"ድብብቆሽ (አኩኩሉ) እንጫወት ልደበቅና ካገኘሀኝ ታገባኛለህ"አለችው "
.
.
እሱ:""ፈልጌ ካላገኘሁሽስ? አላት
.
.
እሷ:""ከበሩ ኋላ ነው ምደበቀው አለችው____🥰😍


#ቸር ቀን ተመኘው🙏


፡  " ለምንድን ነው ግን ሁሌ እጄን እምትይዢኝ ?…" አይን አይንዋን እያየሁ ጠየኳት…ለእረጅም ደቂቃ አልመለሰችልኝም…


  " እጅህን ስይዘው ምንም ነገር አልፈራም…ስለቅህ ግን ይጨንቀኛል…ደግሜም እሚይዝህ አይመስለኝም…እጅህን ስይዘው ውስጤ ሰላም ይሰመኛል…መኖርን እመኛለው…ምነው አንተ ሲይዝህ ይደብርሀል እንዴ?…"

        አልመለስኩላትም…


 
       #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_17


...የሚሆነውን ሳስበው አንቀጠቀጠኝ ለማየትም ለመስማትም ሰቀጠጠኝ...በድን የመሰለኝ የሮቤል አካል መንቀሳቀስ ጀመረ እንደ ማሳልም ሲያረገው ከአፉ ደም ይረጫል ይሄን ባየ ጊዜ ያ ሰው ይበልጥ ደስ አለው ከሚሰማው ጫጫታ ይልቅ ይሄ ለሱ ደስታ ሰጥቶታል ጠጋ ብሎ አይን አይኑን እደተመለከተ ፈገግ ይላል በሌላ በኩል ሮቤል በለዘበ እና በቀሰስተኛ ድምፅ "እርዱኝ አድኑኝ ይላል" ይሄን መመልከት ለኔ እጅግ በጣም ከባድ ነው የማደውን ነገር ማመን አልቻልኩም እጄን አፌ ላይ አድርጌ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩኝ አቅም ቢኖረኝና ከዚ አረመኔ ሰው ባስጥለው ፍፁም ደስተኛ ነበርኩ ነገር ግን አልችልም...ሰውዬው አሁንም ዋይታ በሞላው የሰዎች ጫጫታ በደስታ እና እረፍት የተሰማው በሚመስል መልኩ ይንቀሳቀሳል የዘይቱን መፍላት እየተመላለሰ ይመለከታል ለምን እንደጣደው ባይገባኝም ብቻ አስፈርቶኛል...ሮቤል ሙሉ ለሙሉ ሰውነቱ በደም ተጨማልቋል ከቅንድቡ ትንሽ ከፍ ብሎ በስለት የተቆረጠ የሚመስል ቁስል አለ ይመስለኛል እኔ የተመለኩት ያ የተሰበረ መስታወት ሮቤል ለማምለጥ ሲል የሰበረው እንደሆነ ተረዳሁ ሳሩ ላይ የተመለከትኩት ደም ደሞ ከመስኮቱ ከወደቀ በሗላ ለማምለጥ በደረቱ የተሳበበት እንደሆነ ገባኝ ሁኔታዎቹን ከሮቤል መጥፋት ጋር ማመሳሰሌ ትክክል ነበርኩ ይሄን ሁኔታ ቅድስቴ አለመመልከቷ ለሌሎቻችን በህይወት መቆየት ምክንያት ነው...ብትመለከት ኖሮ ራሷን ማረጋጋት ስለማትችል ሁላችንም እንጠመድ ነበር...ሮቤል አሁንም ድምፁን እያሰማ ነው አረመኔው ሰውዬ ደግሞ እየደነሰ...እንቅስቃሴው ሁሉ ግራ ነው ጨፈረ ለማለት እንኳን አያስደፍርም...ከደቂቃዎች በሗላ የዘይቱን መፍላት አረጋገጠ ከዛም እየሳቀና እንደ ጭፈራ የሚያረገውን እንቅስቃሴ እያሳየ ወደ ሮቤል ተጠጋ ሁለት ተለቅ ያሉ ጥቋቁር ቀበቶ መሳይ ማሰሪያዎችን አንስቶ አንዱን ደረቱጋ አንዱን ደሙ ታፋው ጋር አድርጎ ከጠረጴዛው ጋር ሮቤልን የፊጥኝ አሰረው...የሮቤልን ስቃይ ለመረዳት ሮቤልን መሆን አልነበረብኝም ህመሙ አብዝቶ አመመኝ ስቃዩ አሰቃየኝ ወዲያውኑ ትሪ መሳይ በሆነው ነገር ካመጣቸው ስለቶች መሀል ሁለቱን አንስቶ ወደሰማይ እየተመለከተ ማፋጨት ጀመረ የዘይቱ መፍላት እኔ እስካለሁበት ቦታ ድረስ ሲፍለቀለቅ ይሰማል ብቻ እንደማስበው አይሁን ብዬ አምላኬን ተማፀንኩኝ..."እርዱኝ አድኑኝ እርዱኝ አድኑኝ" እያለ ሮቤል የማይደርስለትን አዳኝ ይጣራል አረመኔውም ሰውዬ አንድ ጣቱን አፉ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ለሮቤል በምልክት ያሳየዋል ነገር ግን ሮቤል የሚረዳውን ሰው ከማያገኝበት ስፍራ መጣራቱን ይቀጥላል በዚ ግዜ ሰውዬው አብዝቶ ይናደድና ሲያፋጭ የነበረውን ስለት ከፍ ሲያረገው አሁን ካሁን አንዳች ቦታ ላይ ወጋው ስል ከፍ ካደረገበት እጁን ሳይመልስ በንዴት የተለዋወጠው ፊቱ ወደ መጀመሪያ ገፅታው ተመልሶ በተረጋጋ ስሜት ሆኖ አሁንም አንድ ጣቱን ከንፈሩ ላይ አድርጎ ዝም እንዲል ይነግረዋል...ከዛ ከጋለ ስሜት ውስጥ መውጣቱ ለኔ በጣም ግራ ነው ሰውዬው በጣም አጠራጣሪና አወዛጋቢ በሆኑ ነገሮች ነው የተሞላው...ዶክተሮች የሚጠቀሙበትን የህክምና ጓንት ከአንዱ መሳቢያ አውጥቶ እጆቹ ላይ አጠለቀ በመሃል የከፈተው ዋይታ ፀጥ አለ እሱም እዛው የቆመበት ቦታ ለይ ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሎ ቆመ ሰከንዳት አልፈው ደቂቃዎች ተቆጠሩ እንደዛው ካለበት ሳይንቀሳቀስ ፀጥ ብሉ እንደቆመ...በዚ ሰዓት ሮቤል አንዳች ድምፅ ቢያወጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማሰላሰል ጀመርኩ ይሄን እያሰብኩኝ ሳለ የቅድሟ ድመት እየጮኸች ወደክፍሉ ስትገባ ከቆመበት ተስፈንጥሮ መጥረቢያውን አንስቶ ወገቧን ብሎ ለሁለት ከፈላት ከቅድሙ ይልቅ አሁን አፌን አጥብቄ ያዝኩ ሰውዬው እዛው ድመቷ የሞተችበት ቦታ ላይ በድጋሜ ፀጥ ብሎ ቆሟል አይኑ እንኳን አይርገበገብም ከደቂቃዎች በሗላ የዋይታው ድምፅ ጀመረ መጥረቢያውን ትከሻው ላይ አድርጎ እያፏጨ መንቀሳቀስ ጀመረ ትንሽ ተንፈስ አልኩኝ ምን ሲያቀብጠኝ ወደዚ ክፍል እንደመጣሁ አላውቅም እዛው ከጓደኞቼ ጋር ሆኜ የሚሆነውን ብጠብቅ ይሻለኝ ነበር...መጥረቢያውን የነበረበት ቦታ ላይ አስቀምጦ ድመቷን ከወደቀችበት አንስቶ የቆሻሻ መጣያ ውስጥ ከተታት ያደረገውንም ጓንት አውልቆ ከድመቷ በድን ጋር አብሮ ጣለው ከዛም አዲስ ጓንት ለማድረግ ወደ መሳቢያው ተጠጋ አውጥቶም በዋይታው እየተንቀሳቀሰ ማድረግ ጀመረ ከዛም ከተሰጡት የዶክተሮች ጋውን አንዱን አንስቶ ለበሰ ከዛም ፈገግ እያለ እየቆለፈ ራሱን በራሱ መመልከት ጀመረ በጣም ደስ ያለው ይመስላል እጁን ኪሱ ከቶ ወደዛ  ወደዚ መንጎራደድ ጀመረ ጓንት ወዳወጣበት መሳቢያ በድጋሜ ሄዶ መነፅር አውጥቶ አደረገ አሁን የባሰ ፈገግ አለ የሚያረገው ነገር ትንሽም ቢሆን ከፍራቻዬ አውጥቶ በአግራሞት ዝም ብዬ እንድመለከተው አደረገኝ ደረቱን ነፍቶ አሁንም መንጎራደዱን ቀጠለ ነገር ግን ሙዚቃው በድጋሜ ፀጥ አለ እሱም ባለበት ቦታ እጁን ኪሱ እንደከተተ ቆመ እኔም እቺ ደቂቃ እስክታልፍ አፌን አፍኜ ያዝኩኝ ነገር ግን ሮቤል......


part #18  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_16

...ልቤ ስንጥቅ እስኪል ድረስ ድንጋጤዬ ከባድ ነበር ነገር ግን ድንጋጤዬን ዋጥ አድርጌ ምንም ድምፅ ሳላሰማ ፀጥ አልኩኝ...የነካሁት አካል በደም የተጨማለቀ መሰለኝ ይቀዘቅዛል ቀስ ብዬ ወደ ነበርኩበት ቦታ ለመመለስ እጄን በጥንቃቄ ከነካሁት አካል ላይ አነሳሁ ከዛ ወደሗላ ማፈግፈግ ጀመርኩ ትንሽ እንደተጠጋሁ መብራቱ ቦግ ብሎ በራ ያየሁትን ማመን አቃተኝ ድንጋጤዬ ከመጠን ስላለፈ ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ በጭለማ ዳብሼ የነካሁት በደም የተጨማለቀው ገላ የሮቤል ነበር...ድምፄ ከተሰማ በሗላ ወዳለሁበት የሚራመድ ፈጠን ያለ እርምጃ ተሰማኝ ከገባሁበት ድንጋጤ ራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ምደበቅበትን አንዳች ስፍራ እንዳለ አይኔን እያማተርኩ ማሰስ ጀመርኩ ከፊት ለፊቴ የዶክተሮች ጋውን በብዛት የተሰቀለበትን ቦታ ተመለከትኩ እርምጃዬንም ፈጠን አድርጌ ከጋውኖቹ መሃል ተደበኩኝ ወደኔ ይመጣ የነበረው ያ እኔ የምፈራው ሰው ነበር በሩ ላይ ቆሞ ግራ ቀኙን ማማተር ጀመረ መጥረቢያውንም ከተቀመጠበት ስፍራ አንስቶ ያዘው ክፍሉ ውስ መዘዋወር ጀመረ ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ወደ ጋውኖቹ ትኩር ብሎ መመልከት ጀመረ እጅግ በጣም ጨነቀኝ አፌን በእጆቼ እፍን አድርጌ ደብዛዬን ለማጥፋት ፀጥ አልኩኝ ግን ከበስተሗላዬ ከሁለት የገመድ መስቀያ አለፍ ብሎ የነበረው መስቀያ ምን እንደነካው እንጃ ወደቀ ፀጥታውም በአንዴ ታወከ ከጋወኑ በታች የነበሩ ፕላስቲኮች እና ብረት ነክ ዕቃዎች ተንጫጩ ወደኔ በርቀት ሆኖ ሲመለከት የነበረው ሰው አሁን መጠጋት ጀመረ ምንም ማድረግ የማልችልበት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሁ ተረዳሁ ለማምለጥ ምንም አይነት አጋጣሚ ሊፈጥር እንደማይችል ደመደምኩ ሰውዬው አብዝቶ ወደኔ ተቃርቧል በመሃላችን ያለው ልዩነት የሶስት ገመድ መስቀያ ብቻ ነበር መጥረቢያውን እያንፏቀቀ አንዱን መስቀያ አለፈ ከጋውኖቹ መሀል ላይም ቆሞ ዙሪያ ገባውን ቃኘ በድጋሜ አንደኛውን መስቀያ አልፎ ወደኔ እጅግ ተቃረበ በመሃላችን የአንድ መስቀያ ልዩነት ብቻ ቀረ መላ አካላቴ መርገፍገፍ ጀመረ ተውረገረገ አይኖቼን ከድኜ ሞቴን መጠባበቅ ጀመረኩኝ እያወቁ መሞት ምንኛ ከባድ ነው ግን አስተውያቸው የማላውቃቸው እነዛ የሰላም ቀናት አብዝተው ናፈቁኝ ሰውነቴ በላብ እና በደም ተጨማልቋል አይኔን ጨፍኜ ሞቴን ብጠብቅም ገዳዬ ግን ዘገየ ምን እንደተፈጠረ ለመመልከት አይኔን ገለጥኩኝ ሰውዬው የተመለከተኝ ይመስል ወደኔ አቅጣጫ እያየ መጥረቢያውን ከፍ አድርጎ በሁለት እጆቹ ያዛው እርምጃው ትንሽ ወደኔ አስጠጋና ለሰከንዳት ያህል ፀጥ ብሎ ቆመ በድንገት አዲት ድመት ድምፇን ከፍ አርጋ ጮኻ ከወዳደቁት ጋውኖች መሀል ተስፈንጥራ ወጣች ወዲያውኑ እኔን ትቶኝ ወደሗላው ተመለሰ ነፍሴም ተረጋጋች ነገር ግን ሰውዬው ከክፍሉ ውስጥ አልወጣም ይብሱኑ ክፍሉ  ውስጥ ያለውን ተለቅ ያለ ጠረጴዛ አየጎተተ ወደ መሃል አመጣው ከዛም ስለት ያላቸውን መቆራረጫዎች ተለቅ ባለ ብራማ መልክ ባለው አራት ማዕዘን ትሪ መሳይ ነገር ላይ አድርጎ አመጣ...የሚያደርገው ነገር እጅግ ግራ ያጋባል ከዛም ወደበሩ ጋር ጠጋ ብሎ የሮቤልን በድን አካል ጠረጴዛው ላይ አደረገው ሊያረግ ያሰበውን ሳስበው ሆዴ ተላወሰ ሊያስመልሰኝም ቃጣው ፈጥኜ እጆቼን አፌ ላይ አደረኩኝ መስኮቱ አጠገብ ካለው መሳቢያ ውስጥ ቆየት ያለ ሞዴል ያለው ቴፕ አውጥቶ ውስጡ ያለውን ካሴት በመዳፉ መታ መታ አድርጎ አድርጎ ከተተው ከዛም ግራ የሚያጋባ ግጥም የሌለው በጩኸት የተሞላ ድምፅ ጀመረ ዋይታ ይበዛዋል ለሰሚው በጣም ይጨንቃል ግን እሱ በደስታ ይንቀሳቀስበት ነበር ፊቱ የጤነኛ ሰው መልክ የለውም ከአፍንጫው ጀምሮ እስከ ጆሮው ድረስ ተቀዶ የተሰፋ ቁስል ይታየኛል አንደኛው አይኑ የአይን ኳሱ የለውም የግራ ጆሮው በከፊል ተቆርጧል ፊቱ በእሳት የተለበለበ ነው ሚመስለው የእጅ ጣቶቹ ላይ ጥፍር የሚባል የለባቸውም የጭንቅላቱ ፀጉር መሃል መሃሉ ባዶ ነው በአደጋ እንደዚ የሆነ ይመስላል ይሄን ሁሉ ነገር የምመለከተው ለጆሮ በማይመቸው የሰቀቀን ድምፅ በሆነው ዋይታ ሲደንስ ነው ትንሽ ከተንቀሳቀሰ በሗላ ከክፍሉ ከአንዱ ጥግ ተለቅ ያለ ድስት አንስቶ ውሃ በዛ ያለ ዘይት ጨምሮበት ቡታጋዝ ለኩሶ ጣደው የሚያረገውን ሁሉ እየደነሰ ነበር ሚከውነው ግን ያልጠበኩት እና ያስደነገጠኝ አንዳች ክስተት ተፈጠረ...............

part #17  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_15


...በሆስፒታሉ የመግቢያ በር ላይ የቆመ ሰው ተመለከትን እጅግ በጣም ከመደንገጣችን የተነሳ የነበርንበትን ክፍል በር ሳንዘጋ እየተጯጯህን ወደ ውስጥ ገባን አንድ ላይ ተጠባብቀን የሚሆነውን መጠበቅ ጀመርን ለደቂቃዎች ቢሆንም መብራቱ አልጠፋም ግን ብዙም አልቆየም ነበር ወዲያውኑ ጠፋ አሁን ፍራቻችን የባሰ አየለ...ከእስትንፋሳችን በቀር የሚሰማ አንዳችም ድምፅ የለም ግን ትንሽ እንደቆየ ከድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ልዝብ ያለ የእርምጃ ድምፅ እና መሬት ላይ የሚጎተት የስለት ድምፅ ተሰማ አሁን ሆስፒታሉ ውስጥ ከኛ ሌላ ሰው እንዳለ እርግጠኛ ሆንኩኝ በመሃል መብራቱ መልሶ በራ ከመፍራታችን የተነሳ መብራቱ ሲበራ እንኳን ደንግጠናል...እርምጃው ቀጥ ብሎ ግን መብራቱ ብዙም ሳይቆይ ጠፋ የሆስፒታሉ በር መግቢያጋ ያለው ብቻ ነበር የሚበራው ለዛም ነው መሰለኝ ወለሉ ላይ የሰው ጥላ ይታየኛል...ጥላው መንቀሳቀስ ጀምሯል እነ ባርሳ ማልቀስ ጀምረዋል እኔ ግን ጥላው ምን እንደሆነ ለመመልከት ከክፍል መውጫ ወደሆነው በር ዝግ ባለ እና ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ መጠጋት ጀመርኩ "ሜርሲ የት ነው ምትሄጂው" አለኝ ባባ በሹክሸካ ድምፀት ከሱ ቀጠል አርጋ "ነይ ተመለሺ" አለችኝ ባርሳ...ሽሽሽሽ ተረጋጉ ያለውን ሁኔታ ለመመልከት ነው አልሄድም አልኳቸው ግልፅ የሆነ እይታ ባይኖረንም ውጪ ከሚበራው መብራት የሚገባው ወጋገን በጥቂቱ ብርሃን ሆኖናል...ጥላው እየቀረበ መጣ እኔም ወደ በሩ መጠጋት ጀመርኩ ያለሁበት የድንጋጤ ስሜት  ነው መሰለኝ የእግሬ ህመም ብዙም አልተሰማኝም...አሁን በሩ ጋር ደርሻለሁ አንገቴን ወደ ውጪ አስግጌ ስመለከት አንዳች ነገር የለም የሆስፒታሉ መብራት በድጋሜ ፏ ብሎ በራ በዚ ጊዜ በፍጥነት ወደ ውስጥ ተመለስኩኝ እነ ባርሳ እዛው ቦታ ላይ ቁጭ እንዳሉ ነው "ምንድነው እዚ ውስጥ ያለው ነገር" አለችኝ ቅድስቴ በተረጋጋ ድምፅ "እስካሁን ምንም ያየሁት ነገር የለም ግን ከኛ ውጪ የሆነ ሰው እዚ ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል ለማንኛው እናንተ ተረጋጉ እኔ ሁኔታው አጣራለሁ" አልኳቸው ሶስቱም በእሺታ አንገታቸውን ነቀነቁ እኔም መለስ ብዬ ያለውን ነገር ለመመልከት በድጋሜ ከክፍሉ ወጣሁ ሁሉም ክፍሎች ዝግ ናቸው ኮሪደሩም ቢሆን ባዶ ነው ግን ከክፍሎቹ ሁላ አንዱ ክፍል ገርበብ ብሏል ቀስ ብዬ እየተራመድኩኝ ገርበብ ወዳለው በር መጠጋት ጀመርኩኝ ጀርባዬን ግድግዳው ላይ አስደግፌ የጎን ነበር ስራመድ የነበረው ግራ ቀኜን ለመመልከት እንዲመቸኝ...ክፍሉ በር ላይ ደረስኩ እስከተከፈተበት ድረስ ስመለከት ምንም አልታየኝም ግራ ቀኜን አየሁና ወደ በሩ እጄን ሰደድኩ ግን ምንም አልነበረም አንገቴን ወደ ውስጥ አስገብቼም ተመለከትኩ አሁንም ባዶ ነው ግን አንዳች ነገር ቀልቤን ሳበው በደም የተጨማለቀ መጥረቢያ ተመለከትኩ እንደገመትኩትም ያ ሰው በዙሪያችን ነው ያለው ማንነቱን ለመለየት በድፍረት ወደ ውስጥ ገባሁ መጥረቢያው ወዳለበት ተጠግቼ ስመለከት በውስጥ በኩል ሌላ በር አለ መጥረቢያውን ትቼ ወደ ውስጠኛው በር አመራሁ ሆስፒታሉ አሰራሩ በጣም ውስብስብ ነው ወደ ውስጠኛው በር እንደተቃረብኩ ያልጠበኩትን ነገር ተመለከትኩ ወለሉ ላይ ወደ ውስጥ የሚያስገባ መንገድ ተመለከትኩ መስኮት የሚመስል መዝጊያ አለው ወለሉ ላይ በርከክ ብዬ ስመለከት ወደታችኛው ክፍል የሚወስድ በደም የተጨማለቀ ደረጃ ተመለከትኩ በጣም ደነገጥኩኝ ያ ሰው አዳኝ ሰውዬ መኖሪያው እዚ እንደሆነ ተሰማኝ በመሀል መብራቱ ድርግም ብሎ ጠፋ አሁን ካለሁበት ቦታ መሄድ ስላለብኝ ለደህንነቴም ስለሚያሰጋኝ የመጣሁበትን በምናቤ ስዬ ግድግዳውን እየተደገፈኩ ከክፍል ለመውጣት ሙከራ ጀመርኩ ግን ሳልጠብቀው እጄ የሰው አካል ላይ አረፈ.............


part #16  ___ ይቀጥላል

ቶሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

10k 0 34 16 84

 
ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው
ሬሳ"
            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_14


...
በጣም ደነገጥኩኝ አንዳች አደጋ ደርሶበት ወደዚ ሆስፒታል መጥቶ ነበር ግን ለምን ህክምናውን ሳይጨርስ ወጣ? ማንስ ሊያስወጣው ቻለ? ዶክተሮቹስ የት ሄደው ነው? የሚሉ መልስ አልባ ጥያቄዎች አይኔን ጫማው ላይ ተክዬ ሳለ ውስጤ ይመላለሱ ነበር ከጫማው ትንሽ ተስፈንጥሮ አንድ ግራ ሚያጋባ ነገር ተመለከትኩ ለማየትም እንዲያመቸኝ ወደፊት እየተጠጋሁ ሳለ ባርሳ "ሜርሲ" እያለች ስጠራኝ ተሰማኝ እኔ ያለሁበት ስፍራ ከመጡ የሚፈጠረውን ስሜት ስለማውቀው ቶሎ ወደ ሆስፒታሉ ተመለስኩ እግሬ ቢያስነክሰኝም እርምጃዬን ፈጠን አድርጌ ወደነሱ ሄድኩኝ ሳያቸው ሶስቱም ፊት ላይ አንዳች ልዩ ነገር ይታየኛል "የት ሔደሽ ነው?" አለች ሜርሲ በንዴት ስሜት ውስጥ ሆና የሷን ጥያቄ መመለስ ሳልጀምር ቅድስቴ ተከተለች "በቅጡ እንኳን የረባ ህክምና ሳታገኚ ምንድነው ሚያዞርሽ" አለችኝ በጣም ደነገጥኩት "ምን የተፈጠረ ነገር አለ" ብዬ ጥያቄዬን ቀጠል አደረኩኝ "የመኪናችንን ጎማ ማን እንደሆነ እንጃ በሆነ ነገር ወግቶታል" አለ ባባ ወዲያውኑ ያ ሰው ነበር ጭንቅላቴ ውስጥ ብልጭ ያለው "የመንደሩ ነዋሪ መሆን አለበት ማለትም ያ አንቺ ከምታስቢው ሰውዬ ሌላ" አለ ባባ እንዴት እንደዚ ማለት እንደቻለ ጥያቄ ፈጥሮብኛል ሆኖም ግን ምንም አላልኩትም ነበር...መልስ ሳልሰጣቸው ወደ መኪናው እያነከስኩኝ ሄድኩ እነሱም ከሗላዬ ተከተሉኝ የሗላው ጎማ ነበር የተወጋው...የቆምንበት ስፍራ ከአስፓልቱ ወረድ ብሎ ስለነበር አፈርማ ነው ግን መኪናው ዙሪያ ምንም አይነት የእግር ኮቴ የለም ከእኛ ውጪ...ከኛ መኪና ትንሽ ተስፈንጥሮ የሆነ ነገር ተመለከትኩ እያነከስኩኝ ተጠጋሁ "ምንድው ሜርሲ" አለችኝ ባርሳ የማየውን ነገር እስካረጋግጥ ድረስ ምንም አላልኳትም ነበር ግን ከእኛ ሌላ እዚ አካባቢ የቆመ መኪና እንዳለ ይሰማኛል እኛ ከቆምንበት በተቃራኒ አቋቋም የሆነ መኪና እንደነበር ያስታውቃል...ግን ሙሉ ለሙሉ ከአስፓልቱ ወርዶ አልቆመም ነበር በአንድ ጎን ያሉት ጎማዎች ናቸው አፈሩ ላይ ያረፉት አሁንም የጎማውን ቅርፅ ወዳየሁበት በጥንቃቄ መመልከት ጀመርኩኝ ይመስለኛል መኪናው ለኛ መኪና ጀርባውን ሰጥቶ ነው የቆመው አቅጣጫው ደሞ እና በቆምንበት ነበር...አተኩሬ ስመለከት የሰው የእግር ኮቴ አለ ኮቴውን እየተመለከትኩ ተጠጋሁ ብዙ ዱካ የለውም ከአምስት እርምጃ በላይ አልተራመዳም ታዲያ ወደመኪናችን እንዴት ሊደርስ ቻለ የሚለው ጥያቄ ውስጤ እያሰላሰልኩ ያለፍኳቸውን የእግር ዳና ድጋሜ እየተመለከትኩ ሳለ አስፓልቱ ላይ የእግር ዱካ ተመለከትኩ ይህ ሰው ካቆመው መኪና እስኪያልፍ ብቻ ነው የተራመደው ከዛ በአስፓልቱ ተራምዶ ወደ መኪናችን ይደርሳል አሁን ጥርጣሪዬ እውነት እየመሰለ ነው...እነ ሜርሲም የማየውን ነገር ሲያዩ የሆነ ነገር እንደተገለጠላቸው ያስታውቃሉ ወዲያው የመኪናው የፊት ጎማ ወዳረፈበት ተጠጋሁ ሲገባና ሲወጣ ይመስለኛል በዛ ያለ ዱካ ይታያል "ያ ሰው አሁንም እየተከታተለን ነው አልተወንም" አልኩኝ "ምነው እግራችንን በቆረጠው ባንመጣስ" አለች ባርሳ እጅግ ተበሳጭታ "አሁን ማማረሩን ትተን ከዚ አካባቢ የምንሄድበትን መንገድ እንፍጠር መዋከቡ ዋጋ ቢስ ነው" አለች ቅድስቴ የማልጠብቀውን የእርጋታ ስሜት እያሳየች "ልክ ብለሻል" በማለት ባባ በሀሳቧ ተስማማ "ትርፍ ጎማ አልያዝክም" ብዬ ባባን ጠየኩት በጭንቅላቱ ንቅናቄ አለመያዙን ነገሮኝ ቀጠል አርጎ "ጎሚስታ ቤት ነው ያለው ኔትወርክ እንኳን ቢኖር ብደውል ይልኩልኝ ነበር" አለ "እና ዛሬ እዚ ልናድር ነው" አለች ባርሳ በጭንቅላቴ ንቅናቄ አውንታዬን ገለፅኩላት ቢመራትም ትዋጠው ምንም ምርጫ የለንም እዚ ባናድር መልካም ነበር ግን አለማደር አንችልም...ሰዓቱ ተጉዞ ወደ አመሻሹ እየተቃረበ ነው ከመኪናው ውስጥ ምግብና አልባሳት ይዘን ወደ ሆስፒታሉ ውስጥ ተመለስን እኔ ከታከምኩበት ክፍል ፊት ለፊት ገባንና ማስተካከል ጀመርን እኔም ልብሴን ለመቀየር ወደ ሻንጣዬ ሄድኩኝ ለአይን ያዝ ያዝ ማረግ ጀምሯል ባባ መብራት ካለ ብሎ ሲሞክር ምንም የለም "መቆጣጠሪያው ጋ አይቼ ልምጣ" ብሎ ባባ ወጣ "ተጠንቀቅ አባቴ" አለች ባርሳ በስስት እያየችው ይሄን ጊዜ ቅድስቴ አይኗ እንባ አረገዘ የባሰ እንዳይከፋት ብዬ ምንም አላልኳትም እኔም ልብሴን ቀያይሬ ተቀመጥኩ ባባ ተሳካለት መሰለኝ መብራቱ በራ "የስ" አሉ ቅድስቴና ባርሳ እኔም ፈገግ አልኩኝ ወዲያውኑ ምግቡን አቀራረቡት ባባም መጣና ለመመገብ ተዘጋጀን በሩን ዘጋንና መመገባችንን ጀመርን አሁን ምሽቱ ጀምሯል ነፍሴ እየተጨነቀች ነው...እየተጨዋወትን መመገባችንን ቀጠልን ግን መብራቱ ጠፋ በጣም ደነገጥን ሁላችንም ፀጥ አልን የሆስፒታሉ አንዱ ክፍል በሃይል ጓ ተደርጎ ተዘጋ በጣም ደነገጥን ግን መብራቱ ወዲያውኑ መጣ ውጪ ያለውን ነገር ለመመልከት ሁላችንም ተነስተን በሩን ከፍተን ወጣን ግን አንዳች አልነበርም ወዲያውኑ ድጋሜ መብራቱ ጠፋ ግን ባሁኑ ብዙ አልቆየም ከመቅፅበት መጣ ደግሞም ጠፋ ድጋሜ ሲበራ ግን................


part #15  ___ ይቀጥላል

ቶሎ
እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

12.2k 0 41 112 140

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                 #ክፍል_፲፫
 
..
.ሁኔታዋ ግራ ስላጋባኝ "ይመስለኛል ይሄ ታካሚ ድንገተኛ አደጋ ደርሶበት ነው የመጣው" አለች "በምን ልታውቂ ቻልሽ ብዬ" ጥያቄዬን ቀጠል አድርጌ እየጠየቋት "የህክምና ካርዱ ላይ የታካሚው ስም የለበትም የመድሃኒት መዘዢያውም ላይ እንዲሁ" ብላ መለሰችልኝ "ቀንስ አልተፃፈበትም" አልኳት በውስጤ የማስበው አንዳች ነገር ስለነበር ክፍሉ ወውስጥ ወዳለው ወደ አንዱ ጠረጴዛ እያመራች የመድሀኒት ማዘዣ ወረቀቱን እየተመለከተች "ቀኑ ትላንት ነው ወደዚ ስፍራ የመጣው ሰዓቱ ግን የለም" ብላ መለሰችልኝ የራጅ ወረቀት ከጠረጴዛው ላይ አንስታ ከፍ አርጋ እየተመለከተች "ግን ታማሚው አብዛኛው የሰውነት ክፍሉ ያን ያህል አልተጎዳም ግን የሗላ የጭንቅላት ክፍሉ ላይ የአጥንት መሰንጠቅ ይታያል ከሆነ ነገር ጋር እንደተጋጨ ወይም በሆነ ነገር እንደተመታ ገምታለው" ብላ ስለ ራጅ ምሰስሉ አብራራችልኝ የጭንቅላት የሗላ ክፍሉ ስትል ጫካ ውስጥ የተመለከትኩት የቅድስት ጓደኛ የአወዳደቅ ሁኔታ ውስጤ ብልጭ አለብኝ እሱ ሊሆን እንደሚችልም አሰብኩ "ግን እዚ ማን ሊያመጣው ይችላል"  ብዬም እራሴን ጠየኩ ሳላስበው ድምፄን ከፍ አድርጌ ነበርና "ምን አለሽኝ" አለችኝ ቅድስቴ "አይ ምንም እንዲሁ ከራሴጋ እያወራሁ ነው ብዬ መለስኩላት ከደቂቃዎች በሗላ እነ ባርሳ መጡ "ምነው ቆያቹ" አለች ቅድስቴ ባባም ቀበል አርጎ "ቶሎ ማግኘት አልቻልንም ለዛ ነው አሁን ሜርሲ እንዴት ነሽ" አለኝ "ደህና ነኝ አሁን ምንም አልልም" በማለት እንዳይጨነቁ ደህና ነኝ አልኩኝ እንጂ ክፉኛ እያመመኝ ነው ቅድስቴ መድሃኒቶችን መዘጋጀት ጀምራለች ግን በመጠራጠር ስሜት ሆና ደግማ ቁስሌን ተመለከተችው "ራጅ ብትታዪ መልካም ነው ሜርሲዬ" አለችኝ "እንዴ ለምን" ብዬ በጥያቄ መለስኩላት "የአናትሽ በስጋ የሸፈነው ክፍል ክፉኛ በወጋሽ ነገር ተቀዷል በዚህ ሁኔታ አጥንትሽም ሊነካ ይችላል" ብላ መለሰችልኝ ባለችው ነገርም ተስማማሁ የተኛሁበትንም አልጋ እየገፉ ወደ ክፍሉ ማምራት ጀመርን በሩ ላይ የተፃፉትን እያነበብን ነበር ፍለጋችን ከተወሰኑ ክፍሎች በሗላ አገኘነው ወደ ውስጥም ዘልቀን ገባን ግን ምንም አልነበረም ባዶ ክፍል ነበር ባየነው ነገር ሁላችንም ግራ ተጋባን "ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ" አለ ባባ "አዲስ ሆስፒታል ነው እንዴ?" አለች ባርሳ ከባባ ቀበል አርጋ "በቅርብ ቀን የተሰራ የራጅ ውጤት እኮ አሁን ተመልክቻለሁ ግን እንዴት ላይኖር ቻለ" አለች ቅድስቴ ግራ በመጋባት ስሜት ሆና "ቁስሉ ንፋስ ስለሚገባበት በቃ መሰፋት አለበት" አለች ቀጠል አርጋ ከዛ ክፍል ወጥተን መጀመሪያ ወደነበርንበት ክፍል ማምራት ጀመርን ሆስፒታሉ ሲበዛ ነጭ ነው ፍሎረሰንት በሚባለው የአንፖል አይነት እጅግ ደምቋል እይታው ራሱ ትንሽ ህመምን ያቀላል ፈፅሞ ሰላም ይሰጣል ወደነበርንበት ክፍል ዘልቀን ገባን የህክምና ጓንቷን አድርጋ በደረቴ ከነ ባርሳ ጋ ሆነው አስተኙኝ ከዛም ህክምናውን ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ፈፀመችው ከዛም አገችው "አሁን ከኢንፌክሽን ነፃ ነሽ" አለችኝ "በቃ እሺ ከዚ አካባቢ በፍጥነት እንውጣ" አለ ባባ አዎ ብለው እነ ቅድስቴ በሀሳቡ ተስማምተው እኔን ደግፈው አነሱኝ እራሴን ችዬ መሄድ እንደምችል ነገርኳቸው እና የተኛሁበት አልጋ ላይ ቁጭ አልኩኝ እነሱ እዛው ባለሁበት ሆኜ ወደ መኪናው ሄዱ ከአልጋው ተነስቼ እየተራመድኩ ወደ መስኮቱ አመራሁ መጋረጃውን ገለጥኩት መስታወቱ ተሰብሮና በደም ተጨማልቆ ነበር ሲመስለኝ የሆነ ሰው ለማምለጥ በዚ በኩል ወድቋል በተሰበረው መስታወት ውስጥ አንገቴን ወደ ውጪ አውጥቼ ስመለከት ሳሩ በደም ተለውሷል የሆነ ሰው እየተንፏቀቀ እንደሄደበት አይነት ምልክት አለው አንገቴን ወደ ውስጥ መልሼ መስኮቱን በመክፈቻው ከፍቼ ቀስ ብዬ ወጣሁ የደሙንም ምልክት እየተመለከትኩ ወደፊት አመራሁ ማን እንደሆን እንጃ ብቻ ክፉኛ የተጎዳ ሰው ነው ከሆነ እርምጃ በሗላ ደሙ ላይ ተለቅ ያለ የጫማ ምልክት ተመለከትኩ እዛው ባለሁቡት ቆምኩኝና አይኔን አሻግሬ ወደፊት ሰደድኩት ከአንድ ስፍራ ላይ ሲንፏቀቅ ይፈስ ከነበረው ደም ይልቅ ብዙ ደም ፈሿል ሳሩም የተረጋገጠ ይመስላል ከዛ ከተጎዳው ሰው ሌላ ሌላም ሰው ነበር ... መሬት ራሱን እያንፏቀቀ ይሄድ የነበረው ሰው በድንገት ጠፋ እርምጃዬን ቀጠል አደረኩኝ አንዳች ምልክት አልነበረም ግን ከትንሽ እርምጃ በሗላ የተንጠባጠበ የደም ጠብታ ተመለከትኩ እሱን ተከትዬ መሄድ ጀመርኩ ዞር ብዬ ስመለከት ከሆስፒታሉ እየራኩኝ ነው ግን ለመመለስ አልፈለኩም እርምጃዬን ቀጠልኩ የደሙን ጠብታ ተከትዬ ስጓዝ ከአንድ ጫካ አጠገብ ደረስኩ አሁን እርምጃዬን ገታሁት ነገር ግን የደም ጠብታው እንደ ቀጠለ ነው ከጫካው መግቢያ ላይ አንድ ነጭ ነገር ተመለከትኩ ወደ ውስጥ ብዙም ያልገባ ስለነበር ለመመልከት ተጠጋሁ የቅድስቴ ጓደኛ ጫማ ነበር............

_part  #14  ___ ይቀጥላል


ሎ እንዲለቀቅ 👍 አሳዩኝ

ከተመቻቹ ÷
                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

11.8k 0 46 114 106
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.