☄የ
መጥፎ ፍፃሜ ምክንያቶች
① የዓቂዳ መበላሸት እንዲሁም ከሸሪዓ ድንጋጌ ውጪ አላህን መገዛት
🏷
የሱና ሰዎች በብዛት ለመልካም ኻቲማ የተወፈቁ ሲሆኑ የቢድዓ ሰዎች ግን በሚሞቱበት ጊዜ በጣም ጥርጣሬ የሚፈጠርባቸውና አላህ ያዘነላቸው ሲቀሩ በጥርጣሬያቸው ላይ ሆነው የሚሞቱ ናቸው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿
وَبَدَا لَهُمْ مِنَ اللَّهِ مَا لَمْ يَكُونُوا يَحْتَسِبُونَ}
📖
ለእነርሱም ከአላህ ዘንድ ያስቡት ያልነበሩት ሁሉ ይገለጽላቸዋል፡፡
﴿
قُلْ هَلْ نُنَبِّئُكُمْ بِالْأَخْسَرِينَ أَعْمَالًا * الَّذِينَ ضَلَّ سَعْيُهُمْ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَهُمْ يَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ يُحْسِنُونَ صُنْعًا}
📖
በስራዎች በጣም ከሳሪዎቹን እንንገራቹ በላቸው።
እነዚያ እነሱ ስራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ስራቸው የጠፋባቸው ናቸው።②የውስጥ ማንነት ከውጪ ካለን ማንነት ጋር የተለያየ መሆን
ነብዩ እንዲህ ይላሉ፦ አንድ ሰው ለሰዎች በሚታይ የጀነት ሰዎችን ስራ ይሰራል እሱ ግን የእሳት ነው አሉ። ቡኻሪ ዘግቦታል። 🟡እዚህ ላይ ሀዲሱ የሚያመላክተን ለሰዎች በሚታይ ሲል ውስጡና ውጪው የተለያየ ውስጡ ከውጪ ተቃራኒ መሆኑን ነው ።
👉ውስጡም ውጪውም መልካም የሆነ አካል ግን ኻቲማው አይበላሽም።
🔵አንድ ሰው ከላይ በሚታየው መልካም ሰሪ ሊመስል ይችላል ነገር ግን በውስጡ
ኩራትን፣
ንፍቅናን፣
ታይታን ወዘተ … ፈልጎ የሚሰራ ሊሆን ይችላል።
🔷አንድ ሰው ነበር ይህ አካል ከነብዩ ጋ ሆኖ ለእስልምና ይዋጋ ነበር ብዙ ታገለ ብዙ ጠላትን ገደለ ነገር ግን ነብዩ እሱ የእሳት ነው አሉ ሰሃቦችም ተገረሙ እንዴት ይሆናል እንዲህ እየተጋደለ አለ አላህ ግን የነብዩ ንግግር እውነት መሆኑን አሳያቸው ይህ ሰው የሆነ ጉዳት ደረሰበት ታዲይ ይህ አካል ህመሙን መቋቋም አልቻለምና ራሱን አጠፋ በዚህ ጊዜ ሰሃቦች የነብዩ ንግግር እውነት መሆኑን አረጋገጡ
③
ወንጀል ላይ ችክ ማለት
🔶ወንጀል እየሰራ ተውበት የማያደርግ አካል ሸይጣን በመጨረሻው የህወት እስትንፋስ ወቅት ራሱ አይተውም ይሾምበታል❗️ከዚያም በዙሪያው ያሉ ሰዎች ሸሃዳን በል ሲሉት ወንጀሉ በሀሳቡ ላይ ትመላለስና ሸሃዳን ከማለት ትከለክለዋለች።
🔶
ኢብን አልቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል፦ከወንጀል ቅጣቶች ውስጥ አንድ ሰው ሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ምላሱና ቀልቡ ሲከዱት ነው። ምን አልባትም ሸሃዳን መናገር ላይችል ይችላል።
👉ከፊል ሰዎች እንዳጋጠማቸው
ላ ኢላሃ ኢለላህ በል በሚባልበት ሰኣት አህ! አህ!
አልችልም ይላል። 🔺ሌላኛውም ደግሞ
لا إله إلا الله በል ሲባል
"ታቲና ቲንቲና" እያለ መዝፈን ይጀምራል ከዛም በዚያ ሁናቴ ላይ ሆኖ ይሞታል።
🔻
ሌላኛው ደግሞ ሸሃዳ በል ሲባል ሸሃዳ ማለት ምን ሊጠቅመኝ እኔኮ ምንም አይነት ወንጀል ሳልፈፅመው ያለፍኩት የለም። 🔺ሌላኛው ደግሞ መቼ ሰላቴን ሰግጄ አውቅና ይላል
🔻አንዳንዱ ደግሞ እኔ በምትለው ነገር የካድኩ ነኝ ይላል…
👉
አላህ ይጠብቀን ኻቲማችንንም ያሳምርልን 🤲👉
https://t.me/AbuEkrimahttps://t.me/Abu_Yehya_ilyas_Awel/6009