በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
👉 ከቁርኣን፣
👉ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
👉 ከታማኝ ዑለማዎችና
👉ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።
ማንኛውም አስተያዬት ሲኖራችሁ  @Abu_Sibewe ላይ አስፍሩት።
ስህተትም ባያችሁ ጊዜ አርሙኝ።
ጀዛኩሙል`ሏህ ኸይራ!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك dan repost
💦‏قال الشّيخ ‎صالح الفوزان حفظه اللّه:
◾️ሸኽ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ

【«فإن من أدرك شهر ‎رمضان ومكّنه اللّه من الإنتفاع به، فقد أنعم اللّه عليه نعمة عظيمة لا يعدلها شيء»】
አንድ ሰው አላህ ረመዷንን በሰላም አድርሶት እንዲጠቀምበት ካደረገው፦ አላህ ለዚህ ሰው የሚስተካከለው የሌለ የሆነን ትልቅ ፀጋ ውሎለታል።
📚 [ مجالس شهر رمضان ١١]

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


✨ረመዳንን እንዴት እንቀበል ?

1⃣ይህ የተከበረ ወር ረመዳን በመምጣቱ በመደሰት ።
ስንት እና ስንት ሰዎች አሉ ረመዳንን ሳያገኙ ሞት የቀደማቸው
አላህ ለዚህ ለተከበረ ወር ስላደረሰን ለውለታው ምስጋና የምናደርሰው ደግሞ በዚህ ወር ውስጥ በኢባዳ ላይ በመጠንከር እና በመታገል ነው።

2⃣ከሁሉም ወንጀሎች እና ስህተቶች እውነተኛ እና ጥርት ያለ መመለስን ወደ አላህ መመለስ ።
ለ እውነተኛ እና ጥርት ላለ ተውበት ደግሞ መስፈርቶች አሉት ፦

🔘ለሰሩት ወንጀል መጸጸት
🔘ዳግም ወደዛ ወንጀል ላለመመለስ መቁረጥ እና መወሰን
🔘ከወንጀሉ ሙሉ ለሙሉ መላቀቅ
🔘የሰዎች ሃቅ ደግሞ ወደ ባለቤቶቻቸው መመለስ

✨ቀደምቶች አላህ ረመዳንን እንዲያደርሳቸው ለ ስድስት ወራት ይለምኑት ነበር ከዚያም ለስድስት ወራት ደግሞ በረመዳን የሰሩትን ኢባዳ እንዲቀበላቸው ይለምኑት ነበር

لَطَائِفُ المَعَارِف


📃የረመዿንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዿን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዿን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዿንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዿንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዿን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዿን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዿንን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዿን
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


☑️ መጣላችሁ የተባረከዉ ወር!!
  
እንዴት ነው ዝግጅት  ለቂርዐት ለሰላት
ከወንጀል ርቆ   ኢባዳን ለማብዛት
ከሰፊው ራህመት  ሸምቶ ለመውጣት።
==
منقول


ለካስ እኔም ላጤ ነ*


🔺የተወረረ ከተማ አይመስልም⁉️

ላጤ ሲዝረከረክ
ሲተራመስ ሀገር

የመአት ነው ጉዱ
ይቅር አይነገር

ረመዳን ሲመጣ
ይብሳል ብሶቱ
የላጤ ሀዘኑ
ይታያል ከፊቱ

ሰው መግሪብ ሰግዶ
ሲሮጥ ወደ ቤት

ላጤ እግር አውጪኝ
ይላል ሻይ ቤት

መቀመጫ አጥቶ
እንቡ እንቡር ሲል

አንጀትን ይበላል
ላጤ ሲደናገር

ከዚህም የባሰ
የከፋው ልናገር ?

ወተትና ዳቦ
አለያ ቴምር

ትራስ ስር አድርጎ
አስቦ ለሱሁር

እንቅልፍ አሸልቦት
ሳይበላ ስሁር

አዛን ይላል ድንገት
ሶላት የፈጅር

ነገሩ ሳይከፋ
ሳትጠፋ ከሀገር

ተሎ ተዘውጀህ
ውጣ ከዚህ ችግር

ሴቶች እህቶቼ
ስሙኝ እባካችሁ

የትዳርን ወጪ
መህር ቀንሳችሁ

ላጤንው ሰው አድርጉት
ይግባ ከቤታችሁ
منقول

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


🗯️ለረመዳን ስንት ቀን ቀረው❓ አሏህ ያድርሰነና🤲 آمين
So‘rovnoma
  •   (ሀ) 5ቀን
  •   (ለ) 6ቀን
  •   (ሐ) 3ቀን
  •   (መ) 4ቀን
  •   (ሠ) 4 ወይም 5 ቀን
  •   (ረ) 3 ወይም 4 ቀን
37 ta ovoz


በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك dan repost
🔼 أهلاً يا رمضان شهر الإقبال على الله


ታላቁና ተወዳጁ ነቢያችን ﷺ ሶሐቦቻቸውን የረመዷንን መቃረብ አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ ብስራትን ሲገልጹ እንዲህ ይሏቸው ነበር፡-

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال، قال رسول الله ﷺ ( أتاكم رمضان شهر مبارك فرض الله عز وجل عليكم صيامه تفتح فيه أبواب السماء وتغلق فيه أبواب الجحيم وتغل فيه مردة الشياطين لله فيه ليلة خير من ألف شهر من حرم خيرها فقد حرم )

(صحيح رواه أحمد 9/225 ( الفتح الرباني ) والنسائي 4/129 وصححه الألباني في الترغيب 1/490).

«የተባረከ ወር የሆነው ረመዷን መጣላችሁ!፡፡ አላህ ጾሙን በናንተ ላይ ግዳጅ አድርጓል፡፡ በዚህ ወር የሰማይ ደጃፎች ይከፈታሉ፡፡ የጀሀነም ደጃፎች ይዘጋሉ፡፡ አመጠኛ ሸይጣናት ይታሰራሉ፡፡ አላህ ከአንድ ሺህ ወር (ስራ) የምትበልጥ የሆነች አንድ ለሊት አለችው፡፡ የዚህን ወር መልካም ነገር የተነፈገ ሰው በርግጥም ከብዙ መልካም ነገራት የተነፈገ ነው፡፡»

قال الإمام الحافظ ، الفقيه ابن رجب الحنبلي - رحمه الله وغفر له - :

قال بعض العلماء : هذا الحديث أصل في تهنئة الناس بعضهم بعضاً بشهر رمضان ، كيف لا يبشر المؤمن بفتح أبواب الجنان ، كيف لا يبشر المذنب بغلق أبواب النيران ، كيف لا يبشر العاقل بوقت تغل فيه الشياطين ، من أين يشبه هذا الزمان زمان ؟! . اهـ

📚 لطائف المعارف ص (1/158)

شهر الخير والبركات

قال تعالي { شهر رمضان الذي أنزل فيه القرآن هدي للناس وبينات من الهدي والفرقان } ( البقرة / 185 ) .
🛍📊
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ረመዳን ታላቁ ወር !!
كيف نستقبل شهر رمضان؟
የረመዳንን ወር እንዴት እንቀበለው ?

🎙 አቡ ቀታዳ አብደሏ ሐፊዘሁሏህ

⌚️ በ 1440 ሂጅሪ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


بسم    الله    الرحمن   الرحيم

አንድ   ሰው   ስራው    ተቀባይኘት    እዲያገኝ    ከፈለገ   2ለት    ነገራቶች    ሟሟላት    ይጠበቅበታላ   1   ኢህላስ     እና   2  ሙታባአ    ናቸው   1  ኢህላስ   ማለት   አንድ   ሰው   የሚሰረው    ስራ      ለالله   ብሎ   የሰራው   ሊሆን   ይገባል  1   الله  እንደ   ሚያየው   አድጎ   መስራት   2  አንተ   ጌታህ    እንደምታየው   አድገህ   መገዛት   ነው  ኢህላስ   የሌለውስ   ስራ  ማለት   ከቁጥር   በሀላ   ያለ   ዜሮ   ማለት   ነው   ስራህ   ለይልኝ   ስሙልኝ   ከሆነ   ምንም   ዋጋ   የለውም   እንደውም   ጀሀነም   መጀመሪያ   ከሚቀጣጥልባቸው   ሰዎች   ይሆናል   الله   ይጠብቀን   ስለዚህ   ስራህ   አጥራ   ለጌታህ   ብለህ   ስራ

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


➦ ዛሬ ደሞ ስለ ዓዒሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) ትንሽ እንይ እስኪ..👇

 ➦ አዒሻ በኒካህ ከነቢዩ ጋር የተሳሰረችው በስድስት ዓመቷ ነው። ➦ከመልክተኛው ጋር መኖር የጀመረችው ግን በዘጠኝ ዓመቷ ነበር።
➦መልዕክተኛው ባረፋበት ወቅትም ዕድሜዋ ገና 18 ነበር ።
➦የዕድሜዋ ማነስ ምንም ሳይገድባት ለብዙ ሀዲሶች ለኢስላማዊ ተግባራት ደንቦች ኃላፊነት ወስዳለች።
➦ይህንን በማስመልከት መስሩቅ ሲናገሩ፦👇

    ⭕️ኢስላማዊ ህግጋትን በተመለከተ ዕውቀት ፍለጋ ብዙ ታላላቅ ሶሃባዎች ወደ አዒሻ ሲሄዱ አይቻለሁ።ብለዋል።

➦ ዓታ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) ደግሞ
⭕️አዒሻ በጊዜዋ ከነበሩ ማናቸውም ወንዶች የበለጠ ምሁር ነበረች።ብሏል

➦ አቡ ሙሳ(ረዲየሏሁ ዐንሁ) በበኩላቸው  በሀይማኖታዊ ዕውቀት ይገጥሙን ለነበሩ እያንዳንዱ ችግሮች በአዒሻ ዕርዳታ መፍትሄ ይገኛል። ብለዋል።

  ከሐዲስ ውስጥ 2210 የሚደርሱ ሐዲሶች በአዒሻ የተዘገቡ ናቸው...

  Share join በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ።👇👇

  
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


➦ዛሬ  አንድ ትልቅ ሶሃባ ላስተዋዉቃችሁ። 👇

   ⭕️ ቢላል   አል-ሀበሽይ‼️

➦ ሙሉ ስሙ ቢላል ኢብን ረባህ ነው።
➦የተወለደው ሒጃዝ መካ ሲሆን ዘመኑም 580 ነው።
➦በዕድሜ ከነቢዩ (ዐለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በ10 ዓመት ያንሳል።
➦አባቱ ረባህ ጥቁር አረብ ባርያ ናቸው።
➦እናቱ ደግሞ ሐማም ትባላለች።
➦ ከዓባን ለማፍረስ የመጣው የአብረሃ ሰራዊት ሲሸነፍ የተማረከች ሐበሻዊት የጦር መሪ ልጅ/ልዕልት ናት።
➦ቢላል በመልኩ ጥቁር ሲሆን ከሁለት ጥቁር የተወለደ በመሆኑና ይበልጥ የሚታወቀው በእናቱ ስለሆነ ቢላል አል- ሐበሺ ይባላል።
➦ቁመቱ መካከለኛ፥ ሰውነቱ የተስተካከለ፥ ፊቱ በጣም ቆንጆ፥ ዓይኖቹ ቡናማ ሆነው ስበት ያላቸው፥ ፂሙ ሙልት ያለ፥ ድምፁ ተስረቅራቂና የተለየ ቅላፄ ያለው በነገሩ ሁሉ የተለየ ችሎታ የተቸረው ሰው ነበረ። ረዲየሏሁ ዐንሁ
➦ቢላል የመጀመሪያው የኢስላም አዛን አድራጊ (ሙአዚን) ነው።
➦በነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጂሓዶች ላይ ሁሉ ተሳትፏል።
➦በደረጃ የተላቁ ከሚባሉት ሰሃባዎች መካከል የሚመደብ ሲሆን ነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ●በጀነት ውስጥ ከእኔ ቀድሞ የእግርህን ኮቴ ሰማሁት!! ማለታቸው ተዘግቧል። (ቡኻሪ፥ 1149)
➦የመጀመሪያ ሚስቱ ሂንድ ስትባል ሌሎች ሁለት ሚስቶች እንደነበሩትም ይጠቀሳል። ነገርግን ልጆች እንዳሉት አልተገለፀም።
➦በነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘመን የግምጃ ቤት ኃላፊ የነበረ ሲሆን በኋላም ሲሞቱ ወደ ሻም ደማስቆ በመሄድ የኬላ ጠባቂ ሆኖ አገልግሏል።
➦ቢላል የሞተው በዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ኸሊፋነት ዘመን 643 ላይ እንደሆነና ዕድሜውም ከነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተመሳሳይ 63 እንደነበረ ይጠቀሳል.... ይህ በጥቂቱ ነዉ

  
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


📌ፈጅር ሰላት
የሰውነት ንቃት ብቻ ሳይሆን
የህይወት ሚስጥር የገባው ልብ እና
ወደ አላህ የሚያመላክተውን መንገድ
ያወቀች ሩህ ንቃት ነው ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን አሶላቱ ወሰላሙ ዐላ ነብይና ሙሀመድን ወዐላ አሊሂ ወሶህቢሂ አጅመዒን
  በመቀጠል፦ስለ ፆም አጠር አጠር ያሉ ፅሁፎችንበዚህ  ቻናል እለቃለሁ ኢንሻአላህ ተከታተሉኝ ባረከሏሁ ፊኩም!
       ፅሁፍ (2)
    💥የፆም አይነቶች💥
  👉የፆም አይነቶች ሁለት ናቸው።እነሱም ግደታ ፆም እና በበጎ ፈቃደኝነት እሚፆም ፆም።
  👉የግደታ ፆም ለሶስት(3)ይከፈላል።
        1)ለወቅቱ ግደታ እሚሆን፡ ይህ የረመዷንን ወር መፆም ነው።
        2)ለምክንያት ግደታ እሚሆን፡ይህ የከፋራ (ማበሻ)ፆሞች ናቸው።
       3)አንድ ሰው በራሱ ላይ ግደታ እሚያደርገው ፆም እሱም የነዝር(ስለት)ፆሞች ናቸው።
         💥የረመዷን ፆም💥
             〰〰〰〰〰
  👉የረመዷን ፆም ብይኑ አቅመ አዳም የደረሰ፣አዕምሮው ሙሉ፣ጤነኛ፣ሀገሩ ውስጥ ተቀማጭ  በሆነ ሙስሊም ሁሉ  ላይ ግደታ ነው።
  የረመዷን ወርን መፆም ከእስልምና ማዕዘናቶች አንድኛው ነው።ለግደታ ነቱ ማስረጃው ከቁርኣን፦
قوله تعالى: {يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ (183)
((እናንተ ያመናችሁ ሆይ!በእናንተ ላይ ፆም ግደታ ተደርጎ ባችኋል በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ ግደታ እንደተደረገ አምሳያ፡ልትጠነቀቁ ይከጀላል እና))(ሱረቱ በቀራ 183)
    ከሀድስ፦
1_ حديث طلحة بن عبد الله رضي الله عنه أن أعرابيًّا جاء إلى رسول الله صلى الله عليه وسلم ثائر الرأس -وفيه- فقال: أخبرني مما فرض الله عليَّ من الصيام، فقال: «شهر رمضان إلا أن تطوع شيئًا» .
1)ጦልሀ ብን ዐብዲላህ እንዳለው  አንድ ፀጉሩ የጎፈጨረ የሆነ የገጠር ሰው ወዴ አላህ መልእክተኛ ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም መጣ አለ።ከዚያ ከሀድሱ ውስጥ እንድህ አለ "አላህ ከፆም ግደታ ያደረገብኝን ንገረኝ"አለ። ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም "የረመዷን ወር ነው በበጎ ፈቃደኝነት የሰራኸው ሲቀር"አሉ።

         2 - حديث ابن عمر رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: «بُني الإسلام على خمس: شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمدًا رسول الله، وإقام الصلاة، وإيتاء الزكاة، والحج، وصوم رمضان» .
2)ዐብደላህ ብን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁ)እንድህ ብሏል የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "እስልምና በአምስት ነገሮች ላይ ተገንብቷል፡ከአላህ ውጭ በሀቅ እሚመለክ አምላክ የለም ሙሀመድም የአላህ መልእክተኛ ነብሎ መመስከር፣ሶላትን አስተካክሎ መስጀድ፣ዘካን(ግደታ ምፅዋትን)መስጠት፣ ሀጅ ማድረግ እና ረመዷንን መፆም።"አሉ።
   ረመዷን ወርን መፆም ከእስልምና ማዕዘናቶች አንዱ በመሆኑ ሙስሊሞች ተስማምተዋል።የረመዷን ወርን መፆም ግደታ አይደለም ያለ ሰው ይከፍራል።ይህን ወር መፆም እሚታዎቁ በሆኑ ትክክለኛ ምክንያቶች እንጅ አይሰቅጥም።

      ቀ
            ጥ
                  ላ
                       ል!
      https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik




የሰው ልጅ ረጅም እድሜው ለዱንያ ሲል እየተዋጋ ይቆይና ሲሞት ግን ዱንያ ከአንድና ሁለት ሜትር ቁራጭ የሚቀበርበት መሬት ውጪ ምንም አትሰጠውም።


🌙 ታላቁ ወር መጣ 📢

አጭር ግጥም

በአቡ አብዲልመናን ኻሊድ ጠይብ
حفظه الله
https://t.me/Fetwawoch_bicha


◉በችግሮች ውስጥ ብሩህ
ተስፋዎች አሉ።
◌ቁም ነገሩ ችግሮቹን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ብሩህ የሆነውን ተስፋ ለማየት የሚያስችለንን ጥበብ መካኑ ላይ ነው።


◉ከስኒው ላይ የተደፋውን ቡና የሚያሳየውን ፎቶ በአመልካችና በአውራጣታችሁ ከግራና ቀኝ በመለጠጥ ሰፋ አድርጋችሁ (Zoom In) ተመልከቱ።


◎ምን አያችሁ ???

◉ እንዲህ ነው ከችግሮች ውስጥ ብሩህ ተስፋዎች የሚፈልቁት።


https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


ወደ ሰዎች አትመልከት አላህ ለሰዎች በሰጣቸዉ ፀጋ መገምዠት በራሱ ድህነት ነዉ



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.