በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


فوائد : أبي سيبويه نور بن صاديق
@Abu_babelheyr_bin_Sadik
https://t.me/+Se4xqUVr3TtG4W9L

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


☑ የእሁድ ሙሀደራ ከቋንጤ ....  ቁ -1

👌!!ከፊል በአብፌት የሚሰሩ ሙኻለፍዎች!!

በሚል ርዕስ   በጉራግኛ  የተዘጋጀ ወቅታዊ ሁሉም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ መካሪ የሆነ ሙሐደራ....

🎙በወንድማችን አቡ ሀምዛ አብዱል ወዱድ  አላህ ይጠብቀው።

በደምብ ወደ ህብረተሰቡ እንዲዳረስ ሼር ሼር ይደረግ

🕌 መስጂድ አሱናህ  (ቋንጤ )

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
 


-ወንዶች የሚያስታውሷቸውና
የሚረሷቸው አምስት ነገሮች

የሚያስታውሷቸው ነገሮች:

① والتِي تكاد أعينهم تنطِق بذَلك: مثنى وثلاث ورباع.

②: إنّ كيدهنّ عظِيم.

③: النّساء ناقصات عقلٍ ودِين.

④: الرّجال قوّامون على النّساء.

⑤: للذكَر مثل حظّ الأنثَيين.

-
የሚረሷቸው ነገሮች:

①: وَعاشِروهنّ بالمعروف.

②: استوْصوا بالنّساء خيرًا.

③: رفقًا بالقَوارير.

④: خيرُكم خيرُكم لأهلِه وأنا خيركم لأهلِي.

⑤: ما أكرَمهنّ إلّا كرِيم ومَا أهانهنّ إلّا لئِيم.

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
📖 {…وَمَا نُرْسِلُ بِالْآيَاتِ إِلَّا تَخْوِيفًا}
{…ተዓምራቶችንም ለማስፈራራት እንጂ አንልክም።}

    [አል_ኢስራእ: ⁵⁹]

ግን ደግሞ…………👇

📖 {…وَنُخَوِّفُهُمْ فَمَا يَزِيدُهُمْ إِلَّا طُغْيَانًا كَبِيرًا}
{…እናስፈራራቸዋለን: ትልቅ የሆነ ጥመት እንጂ አይጨምርላቸውም።}

      [አል_ኢስራእ: ⁶⁰]

   የሰሞኑ አስፈሪ እና አስደንጋጭ የሆነው የዐዛብ ሚስኮል ከደረሰን በኋላ: እንዲው ሰው አጠገብ ከንፈር ከመምጠጥ በዘለለ ፈርተን ተደናግጠን ተውበት አድርገን ወደ አላህ ተመልሰናል ወይ??

منقول


"አስቀያሚ ህይወት ማለት አካል ህያው
ሆኖ ዲን ሲሞት ነው ".

أحمدُ بنُ حنبل رحمه الله.👉ምንጭ


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ቪድዮ በሌሊቱ መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ቤቶች ላይ ያሳየው የንዝረቱ ልክ በእንቅስቃሴ ሲታይ!!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036



©: ቡኻሪና ሙስሊም
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


መዝሪያችን አሁን ነው!


☞ከአስገራሚው የኢማሙ ሻፊዒይ ዲዋን መካከል

🍂إذا المرء لا يرعاك إلا تكلفا
      ❀❀فدعه ولا تكثر عليه التأسفا

ከአንገት በላይ በግድ የሚቀርብህ ከሆን
እርግፍ አድርገህ ተወው አታብዛ ፀፀትን

ففي الناس أبدال وفي الترك راحة
      ❀❀وفي القلب صبر للحبيب وإن جفا

ከሰውም ልዋጭ አለው በመተውም እረፍት
በልብ ውስጥም አለ ለወዳጅ የሚሆን ፅናት

🍂فما كل من تهواه يهواك قلبه
      ❀❀ولا كل من صافيته لك قد صفا

የምትወደው ሁሉ ልቡ አይወድህም
ንፁህ የሆንክለት ኩሉ ንፁህ አይሆንልህም

إذا لم يكن صفو الوداد طبيعة
      ❀❀فلا خير في ود يجيء تكلفا

ከልብ መውደድና ንፁህነት ባህሪ ካልሆነ
በግድ የሚመጣ ውዴታ መልካምም አልሆነ

🍂ولا خير في خل يخون خليله
      ❀❀ويلقاه من بعد المودة بالجفا

ወዳጅን የሚክድ ወዳጅ መቼም ኸይር የለውም
ከውዴታ ቡኋላ የሚገፋው ከሆን ፍፁም አይበጀውም

وينكر عيشا قد تقادم عهده
      ❀❀ويظهر سرا كان بالأمس قد خفا

አብረው የኖሩትን ዘመንን ከድቶ ክፋቱን ያወጣል
ትላንት ያፈነውን የእምነት ሚስጥርን  ይዘረግፋል

🍂سلام على الدنيا إذا لم يكن بها
      ❀❀صديق صدوق صادق الوعد منصفا

በዱንያ ላይ ሰላም! እንሰናበታት በሷ ላይ ከጠፋ
እውነተኛ ወዳጅ  ቃሉን የሚያከብር ፍትሓዊ ሙንሲፋ

    •┈┈┈••✿👑✿••┈┈┈•

✍አል-ኢማሙ ሻፊዒይ

【روائع من ديوان الامام الشافعي رحمه
الله】

        https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


~በረጀብ ወር ዑምራ ማድረግ ይበረታታል። ኢብኑ አቢ ሸይባ በትክክለኛ ሰነድ እንደዘገበው ዑመር፣ ዑስማን፣ ዐኢሻ፣ ኢብኑ ዑመርና ሌሎችም ሶሃባዎች በረጀብ ዑምራ አድርገዋል። ኢብኑ ረጀብ እንደገለፁት ዑመር ቢን ኸጧብ በረጀብ ዑምራ ማድረግን ይወድ ነበር። ኢብኑ ሲሪንም ሰለፎች በረጀብ ወር ዑምራ ያደርጉ ነበር ብሎ አስተላልፏል።
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


☁️🌟🌟🌟☁️

ፈገግ ይበሉ


👉ያው እንደሚታወቀው በሻፊኢይ መዝሀብ ሁሉም ኢባዳዎች ላይ ንያን በንግግር ማስገኘት ሱና ነው

💥ከአዝናኝ(አስቂኝ) የፉቀሀዎች ንግግር


አቡል ፈድል አል መህዛኒይ የሚባሉ የሻፊኢይ መዝሀብ ተከታይ ናቸው እና አባቱ በጣም ፈቂህ ነበሩ ልጅ አቡል ፈድል እንዲህ ይላል

አባቴ እኔን መምታት ሲፈልግ በምቱ ላይ ድንበር እንዳያል በፍራት እንዲህ ይል ነበር

"ልክ አላህ እንዳዘዘው አደብ እንዲይዝ ብዬ ልጄን ለመምታት ነየትኩኝ "
يقول: نويتُ أن أضربَ ولدي تأديباً كما أمر الله


እና አባቴ ንያውን ጨርሶ እስኪያሟላ ድረስ ሸሽቼ አመልጥ ነበር ይላል።

🌱البداية والنهاية (١٢/ ١٨٨)🌱👉ምንጭ

☁️🌟🌟🌟☁️


☞ አንዱ ለሷሊሕ ብን ዐብዱልቁዱስ እንዲህ ብሎ ፃፈላቸው፦


المَوْتُ بَابٌ وكلُّ الناس داخلُهُ
فليتَ شعري بعدَ البابِ ما الدارُ ؟

ሞት እኮ መግቢያ ነው - ሁሉም ሚዘልቅበቱ
እስኪ አሳውቁኝ - ምን ይሆን ቤቱ የተገባበቱ

እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱለት፦

فأجابه:

الدَّارُ جَنَّاتُ عَدْنٍ إنْ عمِلْتَ بما
يُرضي الإلهَ ، وإن خالفتَ فالنارُ

هُمَا مَحَلَّانِ ما لِلناسِ غيرُهما
فانظُرْ لِنفسِك ماذا أنت تختار


ቤቱማ ይሆናል - ዘውታሪ መኖሪያ በዛ በጀነት
መልካምን ከሰራህ - ጌታን ሚያስደስት
ደግሞ ከተቃረንክ - መርጊያህ ነው እሳት
ከሁለቱ በቀር - ለሰዎች ማረፊያ ሌላም የላቸው
ለነፍስህ ተመልከት - ምርጫው ያንተ ነው

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


የምንችለውን እናስተምር

ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።

[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]


ለረመዷን 60 ቀን ቀረው❗️ያረብ🤲


~የ‌ተ‌ከ‌በ‌ሩ‌ ወ‌ራ‌ት‌ (አ‌ሽ‌ሁ‌ሩ‌ል‌‐ሑ‌ሩ‌ም‌)

አላህ እንዲህ ብሏል፦
"إِنَّ عِدَّةَ الشُّهُورِ عِندَ اللَّهِ اثْنَا عَشَرَ شَهْرًا فِي كِتَابِ اللَّهِ يَوْمَ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ مِنْهَا أَرْبَعَةٌ حُرُمٌ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ ۚ فَلَا تَظْلِمُوا فِيهِنَّ أَنفُسَكُمْ"
«የወሮች ቁጥር አላህ ዘንድ በአላህ መጽሐፍ ውስጥ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ቀን ዐሥራ ሁለት ወር ነው፡፡ ከእነሱ አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ይህ ቀጥተኛው ሃይማኖት ነው፡፡ በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»

የተከበሩ ወራት አራት ናቸው:
• ዙል‐ቀዕዳ (ቂዕዳ አትበሉ)
• ዙል‐ሒጃ
• ሙሐር‐ረም
• ረጀብ
ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው። አንዱ ብቸኛ ነው። እርሱም ረጀብ ነው። በሂጅራ አቆጣጠር ሰባተኛው ወር ነው።

ኢማም አል‐ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: ‐
«በእነርሱ ውስጥም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ፡፡»
(ከላይ የጠቀስነው አያ ውስጥ)ኃጢኣት በመፈፀም ነፍሶቻችሁን አትበድሉ ማለት ነው። ምክንያቱም የመልካም ሥራዎች ምንዳ እንደሚነባበረው ሁሉ በዚህ ጊዜ የሚፈፀም ኃጢኣትም ቅጣቱ ይነባበራል። 
ቀታዳ እንዲህ ብለዋል: ‐ «በተከበሩት ወራት የሚፈፀም በደል በሌላ ጊዜ ከሚፈፀመው እጅግ የከፋ ወንጀል ነው።»

ለነፍሳችን መዳን የምንመርጠው ጊዜ ላይ አለንና እናስብበት!

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik


"ምድር ላይ ዝቅ ያልክ ሁነህ እንጂ እንዳትራመድ
ካንተ በላይ ክብር ያላቸው ስንቶች ከምድር በታች ናቸው"


እነዚህን 4 ዱዐዎች ሁሌም ልንረሳቸው አይገባም:
‏- اللهُم إني أسألك حُسنٌ الخَاتمة
‏- اللهُم ارزقنيِ توبة نصوحة قبل الموت
‏- اللهُم يا مُقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
‏- اللَّهم إنَّك عفوٌ كريمٌ تحبُّ العفوَ فاعفُ عنّا


ማንኛዉም ጉዳይ ሲከብድህ
ዱንያ ከመስፋቷ ጋር ስትጠብህ
ልብህን ጥደህ አላህን በ الفتاح ስሙ ችክ ብለህ ተማጸነው


በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك dan repost
◉ውዷ ―እህቴ ―ጊዜው― የኒቃብነው!


¤" ብዙዎቹ ኒቃብ ለምን? ይላሉ።
ግን ዙሪያችንን ብናስተነትን
.
①" ምድር ሽፋን ያላት መሆኑ
.
②ለሰይፍ ሽፋን አፎት መኖሩ
.
③"እስክሪብቶ ያለ ሽፋን
ቀለሙ ቶሎ መድረቁ
.
④አፕል ሽፋኑ ባይኖር ኖሮ ወዲያውኑ መበላሸቱ
.
⑤"ሙዝ ሽፋኑ ቢነሳ ወዲያውኑ መጥቆሩ
.
⑥"ተማሪዎቻችን ደብተሮቻቸውን የሚሸፍኑት እንዳይበላሽባቸው መሆኑን በአስተውሎት
ብንመለከት ሽፋን ያለውን ጥቅም እንረዳ ነበር።
.
🎖ሴቶች ደግሞ ከሁሉም በላይ ውብ ናቸውና የሚሸፈኑበት ሂጃብ ( ኒቃብ ) ያስፈልጋቸዋል!!!
.

🎖ሌላው ቀርቶ ለስልኮቻችን እራሱ ሽፋን ከየትም አፈላልገን ገዝተን እናደርጋለን ፡፡
.
🎖ታድያ ውዷ እህቴ አንቺ ከሙዝ በምን ታንሺያለሽ ፣ ከሞባይል በምን ታንሽያለሽ ?
        አንቺ ፦
.
🎖እኮ አላህ እሱ በፈለገውና ባማረ ቅርፅ ፈጥሮሽ ሲያበቃ የወንዶች ቀልብ ማረፊያ አደረገሽ ፡፡

·
🎖የሚገርመው አንድ ሠው ምኑንም ያክል ሀብታም ቢሆን ምኑንም ያክል የተከበረ
ባለስልጣን ቢሆን የደስታው ጥግ ያለው ሴት ጋር ነው ፡፡
.
🎖ለዚህም ነው የአላህ መልዐክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል
ዱንያ ውስጥ ካሉት ከሚያስደስቷቸው ነገሮች መካከል【 ሴቶችን】
የጠቀሱት ፡፡
.
🎖 ከምንም በላይ ደግሞ አህቴ "አላህን ልትፈሪ ይገባል " አንድ ጥያቄ እራስሽን
ጠይቂ?
.

🎖 አሁን ያለሽበትን ይህን ያማረ ገፅታ ማን ነው የፈጠረው " ..?
.
መልስሽ አላህ ከሆነ ፦
.
አላህ በሰጠሽ ፀጋ እሱ ታምጭዋለሽ ?
.

🎖አላህ ለእናንተ ሂጃብ የምትለብሱበትን ለኛ ( (ለወንዶች )) ዐይናችንን የምንሰብርበትን
ኢማን ይስጠን !!!
      
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik
https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik




በሚጠቅምህ ነገር ላይ ብቻ መሽሁል ሁን!!إحرص على ما ينفعك dan repost
◉ሂጃብሽን አደራ!!!


ከቤት ስትወጪ ስትዉይ ከገበያ
ወይንም ሌላም ቦታ ከህዝብ መዋያ
ሂጃብሽን አትርሽ ሀራም መከልከያ

የትም የትም ቢሆን የዲንሽ ዉበቱ
ልፋትሽ ጥረትሽ የሚያምረዉ ዉጤቱ

የምትኮሪበት በሙስሊምነትሽ
ለሀራም ለዚና ሁሉ እንዳይመኝሽ

የሰፈር ቦዘኔ እንዳይቀልድብሽ
እንቶኔ ሰካራም እንዳይዳፈርሽ
ሂጃብሽን አደራ እሱ ነዉ መከታሽ።

ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
ያልተሸፋፈነ በዝንብ ይወረራል!!!

ስለዚህ ለመኖር በሸሪአ ጎራ
አይን ሳይበዛብሽ ሆነሽ ከሴት ተራ
ሂጃብሽን አትርሽ ሀራም መከልከያ።

https://t.me/Abu_babelheyr_bin_Sadik

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.