ሕብረተሰቡ ሪሊፍ የተባለ ሕገ ወጥ መድሃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ ማሳሰቢያ ተሰጠ!
ሪሊፍ (RELIEF) የተባለና በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው የሚገመት ሕገወጥ መድኃኒት፤ በኢትዮጵያ ገበያ በስፋት እየተዘዋወረ መሆኑ እንደተደረሰበት የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ገልጿል።ይህ መድኃኒት በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገበ በመሆኑ፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ እንደማይታወቅ አስታውቋል።
በተጨማሪም፣ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት፣ ተቅማጥ፣ የሆድ ህመም፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ድካም፣ የእይታ መዛባት፣ መፍዘዝ፣ ራስ ምታት፣ የቆዳ ሽፍታ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን እንደሚያመጣ አመላክቷል።
ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ እንደሚችልም ጥናቶች ማመላከታቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
በመሆኑም ሕብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እና መድኃኒቱን ጥቅም ላይ ሲውል ከተገኘ፤ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 በመደወል ለባለስልጣኑ ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።
@Addis_Reporter