ዓርብ ኅዳር 13፣ 2017 ዓ፣ም ዕለታዊ ዜና
1፤ የሲቪል ማኅበረስብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣ “የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል”፣ “ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች ኢትዮጵያ” እና "የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች" የተባሉ ሲቪክ ድርጅቶችን ማገዱን ዋዜማ ሰምታለች። ባለሥልጣኑ ባለፈው ሳምንት መጨረሻና በዚህ ሳምንት ለድርጅቶቹ በተናጠል በላከው ደብዳቤ፣ ድርጅቶቹ ከማናቸውም እንቅስቃሴ መታገዳቸውን አስታውቋቸዋል። ዋዜማ የተመለከተችው ደብዳቤ ለእገዳው የሰጠው ምክንያት፣ ድርጅቶቹ ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆነው መሥራት ሲገባቸው ከዓላማቸው ውጭ በመንቀሳቀስ የአገርና የሕዝብ ጥቅምን በሚጎዱ ተግባራት ላይ ተሠማርተዋል የሚል ነው። የድርጅቶቹ የባንክ ሒሳብም ታግዷል ተብሏል። እገዳው መንግሥት በሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ ሲያደረግ የቆየው ጫና የመጨረሻ ከፍታ ነው ሲሉ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዋዜማ ተናግረዋል። ለባለሥልጣኑ ቅርብ የሆኑ ምንጮችም፣ እገዳው የተላለፈበት ሂደት ግልጽ እንዳልኾነላቸው ተናግረዋል።
2፤ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የደራ ወረዳ ነዋሪዎች ሰሞኑን በንጹሃን ላይ የተፈጸመውን ጥቃት የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ ኅዳር 13 ማካሄዳቸውን የዞኑ ኮምኒኬሽን ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል። የፋኖ ታጣቂዎችና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው አማጺ ቡድን በወረዳው ለዓመታት ከሰብዓዊነት ያፈነገጠ የሽብር ድርጊት በንጹሃን ላይ ሲፈጽሙ እንደነበር በመግለጽ ነዋሪዎቹ ድርጊቱን አውግዘዋል ተብሏል። በሰልፉ ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ክፈለው አደሬ፣ ድርጊቱ ለዘመናት አብሮ የኖረውን የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ ለማጋጨት ጽንፈኞች ሆነ ብለው ያደረጉት ነው ያሉ ሲኾን፣ ታጣቂዎች የሚያሴሩት ሴራ የትኛውንም ብሔር አይወክልም ማለታቸው ተገልጧል። በክልሉ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጊንጪ ከተማም በተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። በሌላ በኩል ትላንት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ቀጥሎ፣ ዛሬም በቦረና፣ ደምቢዶሎ፣ አርባ ምንጭና ወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች የተቃውሞ ሰልፎች መደረጋቸው ታውቋል።
3፤ በአማራ ክልል በተለያዩ መጠለያዎች የተጠለሉ ኤርትራዊያንና ሱዳናዊያን ስደተኞች ደኅንነታቸው አደጋ ላይ መውደቁን መናገራቸውን ኒው ሂውማኒተሪያን ድረገጽ ዘግቧል። ስደተኞቹ ታጣቂዎች ጥቃት እንደሚፈጽሙባቸውና የግዳጅ ጉልበት እንደሚያሠሯቸው መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል። በደቡብ ጎንደር ዞን ደምቢያ ወረዳ በሚገኘው አለምዋች መጠያ የተጠለሉ ኤርትራዊያን ስደተኞች፣ የታጠቁ ኃይሎች አካላዊ ጥቃትና ዘረፋ እንደሚፈጽሙባቸው፣ አፍነው እንደሚወስዷቸውና ባንድ ዓመት ውስጥ ዘጠኝ ስደተኞች በጥይት ተመትተው እንደሞቱ ዘገባው ጠቅሷል። በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ ሰባት ሕጻናትን ጨምሮ 12 ስደተኞች ታግተው፣ ለማስለቀቂያ ግማሽ ሚሊዮን ብር እንደተጠየቀባቸው የመጠለያው አመራሮች ተናግረዋል ተብሏል።
4፤ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኩባንያ መንግሥት በቴሌኮምንኬሽን ዘርፍ ሁሉንም በእኩል የሚያስተናግድ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቧል። ኩባንያው፣ መንግሥት በኤምፔሳ እና በሌሎች የገንዘብ መገበያያ ዘዴዎች መካከል እርስ በርሱ ተነባቢ የኾነ አሠራር እንዲኖር መፍቀድን ጨምሮ አንዳንድ ማሻሻያዎችን እንዲያደርግ መጠየቁን ኢትዮጵያ ቢዝነስ ሪቪው ድረገጽ ዘግቧል። ዋናው የቴሌኮምንኬሽን ዘርፉ ትኩረት፣ በአገልግሎት የዋጋ ቅናሽ እና በአገልግሎት ጥራት ላይ መሆን እንዳለበት ኩባንያው ጠቁሟል ተብሏል። ኩባንያው ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ጥያቄ ያቀረበው፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ወደ ኩባንያው ጽሕፈት ቤት አቅንቶ በኩባንያው እንቅስቃሴ ዙሪያ ከኩባንያው ሃላፊዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።
5፤ መንግሥት ከሁለት አስርት ዓመታት በኋላ የአካባቢ ጥበቃ አዋጁን ያሻሻለ ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል። የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽዕኖ አዋጅ የተሰኘው ረቂቅ፣ መንግሥት በፕሮጀክቶች ትግበራ ወቅት ጉዳት ሊደርስባቸው የሚችሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች በፕሮጀክቱ ዙሪያ በቅድሚያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በትግበራው ዙሪያ አስተያየቶችን እንዲሰጡ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት እንደተደነገገ ዛሬ በረቂቁ ላይ በተደረገ ሕዝባዊ ውይይት ላይ ተገልጧል። ረቂቅ አዋጁ፣ ፕሮጀክታቸው ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ይሁንታ ሳያገኙ ኘሮጀክቶችን ወደመተግበር የሚገቡ አካላት ከ500 ሺሕ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል የሚል አንቀጽም አካቷል። ፍቃድ ያላቸው የፕሮጀክት ባለቤቶች በየሦስት ዓመቱ የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽዕኖ አጠባበቅ ዕቅዶችን ለአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን እንዲያቀርቡ ረቂቅ አዋጁ ግዴታ ይጥላል።
6፤ በ500 ያህል ወረዳዎች የነዳጅ ማደያ ባለመኖሩ ሕገወጥ የነዳጅ ግብይት እንደተባባሰ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ ባወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ በተደረገ የአስረጂዎች መድረክ ላይ ተገልጧል። በየደረጃው ያሉ የንግድ መዋቅሮች በበርሜልና በጀሪካን ነዳጅ እንዲገዙ ፍቃድ ማግኘታቸው፣ ሕገወጥ ንግድ እንዲስፋፋ አድርጓል ሲል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ቅሬታ አቅርቧል። አንዳንድ ክልሎችም የሚላክላቸውን ወርሃዊ የነዳጅ ፍጆታ በበርሜልና በጀሪካን በመሸጥ፣ ባጃጆች እና የከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ነዳጅ እንዲያጡ ምክንያት ኾነዋል ተብሏል። የነዳጅ ውጤቶችን የነዳጅ ማደያ በሌለባቸው አካባቢዎች ሲሸጥ የተገኘ ሰው፣ በስድስት ወራት እስራትና ከ20 እስከ 50 ሺሕ ብር እንዲቀጣ መንግሥት መመሪያ ቢያወጣም፣ ቅጣቱ ግን ከፍ ማለት እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳስቧል።
Via : ዋዜማ
@Addis_Reporter