ኃይማኖት በመስበክ ስም በመሰጂዶች አካባቢ "ትንኮሳ" እየተደረገብኝ ነው - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች
የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ በጎዳናዎች ላይ ኃይማኖት በመስበክ ስም ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን በመፈጸም በኃይማኖቶች መካከል "ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ" አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
ምክር ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወንዶቹን ጀለቢያና ሴቶችን ሂጃብ በማስለበስ በቡድን እምነትን የመስበክና በመሰጂዶች አካባቢ "ትንኮሳ" የመፈጸም ድርጊቶች እየተደጋገሙ እንደሆነ ገልጿል።
ምክር ቤቱ አንድ የከፍተኛ አመራሮች ቡድኑ ከአዲሰ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አመራሮች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ መወያየቱንና የኹሉም ኃይማኖቶች አመራሮች በተገኙበት ውይይት እንዲደረግ ስምምነት ላይ እንደተደረሰ ጠቅሷል።
ጉዳዩ የኃይማኖት ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊነት፣ የሕሊናና የሕግ ጭምር ነው ያለው ምክር ቤቱ፣ በእምነት ስም የኃይማኖት ጥላቻ የሚያንጸባርቁ አካላትን በሕግ ለመጠየቅ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
@Addis_Reporter