የአማዞን መስራቹ ጄፍ ቤዞስ ንብረት የሆነው የጠፈር ኩባንያ የመጀመሪያውን ሮኬቱን ወደ ምህዋር አምጥቋል።
ይህ የቤዞስ እርምጃ በዘርፉ ላይ የበላይነት ተጎናፅፎ የቆየውን የኤሎን መስክ ስፔስ ኤክስ ኩባንያን የሚፎካከር ነው።
ወደ ህዋ በሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የዓለማችን ሁለቱ ባለጸጎች ፉክክር ውስጥ ገብተዋል።
ቱጃሮቹ ትላልቅ እና ኃይለኛ ሮኬቶችን በማምጠቅ ሰማዩን በሳተላይቶች ማጨናነቅ፣ የግል የጠፈር ጣቢያዎችን መመስረት እና ወደ ጨረቃ በሚደረጉ መደበኛ ጉዞዎች ላይ መስራት ይፈልጋሉ።
ከዛሬ ብዙ እንማራለን የሚሉት የቤዞስ የጠፈር ኩባንያ የሆነው የብሉ ኦሪጅን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴቭ ሊምፕ፤ በመጭው የፀደይ ወቅት ላይ በድጋሜ ሙከራ እንደሚደረግም አመላክተዋል።
ከ60 ዓመታት በፊት በምህዋር ሆኖ ምድርን በመዞር የመጀመሪያ በሆነው አሜሪካዊ ጠፈርተኛ ስም ጆን ግሌን የተሰየመው እና በቤዞስ የጠፈር ኩባንያ የመጠቀው ሮኬት 98 ሜትር ከፍታ ያለው ነው።
“ኒው ግሌን” የተባለው ይህ ሮኬት በስፔስ ኤክስ በብዛት ጥቅም ላይ ከዋለው ፋልኮን 9 ሮኬት የበለጠ አቅም ያለው ሲሆን ብዙ ሳተላይቶችን መሸከም የሚችል መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።
ይህ ጅምር በዘርፉ ላይ ትልቅ እርምጃ ተደርጎ የሚወሰድ ቢሆንም ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት ብቻ 134 ጊዜ ሮኬቶችን ያመጠቀው ስፔስ ኤክስ ከፍተኛ ብልጫ አለው።
ኤሎን መስክ በኤክስ ገፁ ላይ "በመጀመሪያው ሙከራ ምህዋር ላይ ስለደረስክ እንኳን ደስ አለህ" በማለት ለአዲሱ ተፎካካሪው መልዕክት አስተላልፏል።
ይህንን ተከትሎ የቱጃሮቹ አዲሱ የፉክክር ሜዳ ህዋ ሊሆን እንደሚችል እየተገመተ ይገኛል፡፡
@Addis_Reporter