ኢትዮጵያን "በሽብር፣ በአክራሪነት እና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ” በሚል የተድበሰበሰ ክስ ከሚያስሩ አገራት ተርታ ተመደበች።
ዓለማቀፉ የጋዜጠኞች ተከላካይ ቡድን (ሲፒጄ) ትናንት ባወጣው ልዩ ሪፖርት፤ ኢትዮጵያን "የተድበሰበሰ ክስ" ከሚመሠርቱ ወይም "በሽብር" ወይም "በአክራሪነት" ውንጀላ ቅጣት ከሚጥሉና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ከሚያስሩ አገራት ተርታ መድቧታል።
በዙህም ኢትዮጵያ ከግብጽ፣ ሩሲያ፣ ማይነማርና ቤላሩስ ተርታ ተመድባለች።
ኢትዮጵያ ካሠረቻቸው ስድስት ጋዜጠኞች አምስቱ በአማራ ክልል የሚካሄደውን ግጭት ከዘገቡ በኋላ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው ሪፖርቱ ጠቅሷል።
ስድስተኛው ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ በመስከረም 2017 ዓ.ም መታሠሩንና ባለሥልጣናቱ ጋዜጠኛው የታሠረበትን ምክንያት እስካሁን እንዳልገለፁ ወይም ክስ እንዳልመሠረቱበት ሪፖርቱ ገልጧል።
ኤርትራ ከሰሃራ በታች ካሉ አገራት 16 ጋዜጠኞችን በማሠር ቀዳሚዋ ሆና የቀጠለች ሲሆን፤ በዓለም ላይ ደሞ ከኢራንና ቬትናም ጋር ሰባተኛዋ ቀዳሚ ጋዜጠኛ አሳሪ ተብላለች።
@Addis_Reporter