ጓደኞቼ "እንዴት ታድለሻል" እያሉ ይቀኑብኝ ነበር።እውነትም እናትና አባቴ ብዙ ገንዘብ ነበራቸው።በልጅነት ዘመኔ፣ሊያስደስቱኝ ፈልገው በገንዘባቸው ብዙ ነገር ያደርጉልኝ ነበር።አባቴም "ልጄ አንቺን ስለምወድሽ ይሄን ይሄን አደርግልሻለው" እያለ ገንዘቡን ብዙ ነገር ላይ ያወጣ ነበር።በዚያ በልጅነቴ ዘመን ከሚገዛልኝና ከሚያደርግልኝ ብዙ ነገሮች ሁሉ በላይ የሚያስደስተኝና በናፍቆት እጠብቀው የነበረው፤በስንት ጊዜ አንዴ አብሮኝ የሚያሳልፋቸው ጥቂት ጊዜያት ነበሩ።እነዚያ ጥቂት ጊዜያት ለኔ ምን ያህል ዋጋ እንደነበራቸው ቢያውቅ ኖሮ፤ከመሞቱ በፊት ቢረዳ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ።
📚ርዕስ፦የኔ ታሪክ
✍️ደራሲ፦ሲፈን ኦስቲን
✈️ @Bemnet_Library
📚ርዕስ፦የኔ ታሪክ
✍️ደራሲ፦ሲፈን ኦስቲን
✈️ @Bemnet_Library