የንስር አሞራ አስገራሚ ባህሪ እና አንተ አንቺ እና እኔ
🎯ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው መጨረሻህን ድል ድል ታሸተዋለህና በፍቅር ተከተለኝ።
ልጀምርልህ
🎯ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ጸሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው የአለማችን ፍጥረት ነው ። አንድ ንስር በመብረር ላይ እያለ ቁራወች ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሁነው ከበው ሲጮሁበት ወደጸሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ጸሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋቸዋል!!
🎯ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል ፣
🎯 ንስር ከ5-7 ኪሜ ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣
🎯 ንስር ለአደን እስከ 120 km አካሎ ይበራል፣
🎯 ንስር መመጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሁኖ ሃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣
🎯ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣
🎯ንስር ሲታመም ጸሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣
🎯 ንስር 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣
🎯ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...
👉የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...
👉ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...
👉ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።
👉እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።
👉1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
👉2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?
🖐የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።
👉፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።
👉፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።
👉፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡
👉፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።
👉፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።
👉ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡
ወዳጄ ሆይ:-
ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ...
፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ...
፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ...
አስተውል
👉ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ...
👉፩ኛ. ራስህን ከመጥፎ ነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ...ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል።
👉፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ።
👉፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ።
👉፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ።
👉፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በኋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል።
📷ሲጠቃለል ...
🎯አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በኋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል።
ለዚህ ነው ንስር የጥንካሬ የአይበገሬነት እና የከፍታ የመታደስ የአትኩሮት የሐያልነት ምልክት የሆነ ልዩ ፍጡር በመሆኑ በርካታ ሐገሮች ንስርን ምልክታቸው በማድረግ የሚጠቀሙት!!
ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/eec1227