የሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያ ኃይሎች ጌዶ ግዛት ውስጥ ዶሎ በተባለች የድንበር ከተማ በሦስት የሱማሊያ ጸጥታ ኃይሎች ጣቢያዎች ላይ ትናንት ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። ጥቃቱ "የታቀደ" እና "ኾን ተብሎ" የተፈጸመ ነበር ያለው ሚንስቴሩ፣ በጥቃቱ ሲቪል የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ ቁጥራቸውን ያልገለጣቸው ሰዎች እንደተገደሉ ጠቅሷል። ጥቃቱ ኹለቱ አገሮች አንካራ ላይ የተፈራረሙትን የባሕር በር ስምምነት የሚጥስ እንደኾነ ሚንስቴሩ የጠቀሰ ሲኾን፣ ሱማሊያ ጥቃቱን በዝምታ እንደማትመለከተውም ገልጧል። ሱማሊያ ይህን ክስ ያሠማችው፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደኤታዋ ዓሊ ኦማር ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር በኹለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመነጋገር አዲስ አበባ ከገቡ ከሰዓታት በኋላ ነው።
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA