ከሞት በኋላ ኩላሊት እንዲለገስ የሚፈቅድ የሕግ ማዕቀፍ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡ ተገለጸ‼️
👉 በኢትዮጵያ ከ400 ሺሕ በላይ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች አሉ ተብሏል
ሰዎች ከሞቱ በኋላ ኩላሊት እንዲለግሱ የሚፈቅደው የሕግ ማዕቀፍ ሀሳቡ ከዓመታት በፊት በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀ ሲሆን፤ በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ መቅረቡን የኩላሊት ሕመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል።
ሰው በሕይወት እያለ ወዶና ፈቅዶ በመስማማት ሕይወቱ ካለፈ በኋላ ኩላሊቱ እንዲወሰድ የሚፈቅደው የሕግ ማዕቀፍ ለብዙ ጊዜ ይፀድቃል፤ በሚል ሲጠበቅ እንደነበረ የገለጹት የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ሰሎሞን አሰፋ፤ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ለአሐዱ ተናግረዋል።
ዋና ሥራ አስኪያጁ አክለውም ኢትዮጵያ ውስጥ የታማሚዎች ትልቁ ችግር ኩላሊት ማጣት እንደሆነ የገለጹ ሲሆን፤ "አንዳንዱ ጭራሹንም የሚሰጠው ሰው የለም፡፡ ሌላኛው ደግሞ ኩላሊት የሚሰጠው አግኝቶ ግን በምርመራ አይመሳሰልም፣ በተጨማሪም ሕመምተኛ ሁኖ ከቤተሰቡ መውሰድ የማይፈልግ ስላለ የኩላሊት ንቅለ ተከላን ለማድረግ አዳጋች ነው" ብለዋል።
"ለዚህ ሁሉ መፍትሄ ይሆናል ብለን የምናስበውን ሕይወቱ ካለፈ ሰው የሚደረገው የኩላሊት ንቅለ ተከላ ላይ ጠንከር ያለ ሥራን ለመስራት እያሰብን ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም በሀገሪቱ ከሚገኙ የኩላሊት ህመምተኞች መካከል ከ400 ሺህ በላይ የሚሆኑት የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው እንደሆኑ ዋና ሥራ አስኪያጁ ዶ/ር ሰሎሞን አሰፋ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ከነዚህ ውስጥ በሳምንት ከ30 እስከ 45 ሺሕ ብር በመክፈል የኩላሊት እጥበት በማድረግ ሕይወታቸውን ለማቆየት ሲታገሉ አንዳንዶቹ ደግሞ፤ በገንዘብ እጥረት ምክንያት በሳምንት ሦስት ጊዜ ማድረግ ያለባቸውን እጥበት አንድ ጊዜ ብቻ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ሲሉም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ለኩላሊት ሕመምተኞች ፈታኙ ነገር የገንዘብ እጥረት እንደሆነ የገለጹም ሲሆን፤ ግብአቶች ከውጩ የሚመጡ በመሆናቸው በተለይም ከማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያው በኋላ ሕመምተኛው በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ አክለዋል።
በአዲስ አበባ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ዳግማዊ ምኒሊክና ዘውዲቱ ሆስፒታል ብቻ የሚሰጠውን ነፃ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት በመዲናዋና ላይ የማስፋፋት ሌሎች ከተሞች ላይ ደግሞ የማስጀመር ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝም ዋና ሥራ አስኪያጁ ለአሐዱ አሳውቀዋል።
እድሜው ከ40 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ ከ40 ዓመት በታች የሆነ ደግሞ፤ በዓመት ሁለት ጊዜ የኩላሊት ምርመራ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ ለኩላሊት መድከም 60 በመቶ የሚሆነው የስኳርና ደም ግፊት ሕመም በመሆኑ በዚህ ሕመም የተጠቁ ሰዎች በሙሉ ቢያንስ በየዓመቱ እንዲመረመሩና መድኃኒታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እንዲሁም፤ በሀኪማቸው የሚሰጣቸውን ምክር ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
#አሀዱ
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA