በመዲናዋ በአምስት ወራት ውስጥ ከ300 በላይ ሕጻናት በተለያዩ ቦታዎች ተትተው መገኘታቸው ተገለጸ‼️
👉ሕጻናትን ወልደው በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚተው ወላጆች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ተላልፏል
ታሕሳስ 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ እድሜያቸው ከ8 ዓመት በታች የሆኑ ከ300 በላይ ሕጻናት በወላጆቻቸው የተለያየ ቦታዎች ላይ ተትተው መገኘታቸውን የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ሕጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገልጿል፡፡
ቢሮው የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሕጻናትን ወልደው የሚተው ወላጆች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ አስተላልፏል፡፡
በወላጆቻቸው ተትተው የተገኙት ሕጻናትም፤ በክበበ ፀሀይ የሕጻናት መንከባከቢያ ማዕከል ውስጥ እንዲገቡ መደረጉንም አስታውቋል፡፡
በቢሮው የሕጻናት ደህነት መብት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አንዷለም ታፈሰ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ ሕጻትን በተለያየ ቦታ በመተው እና ወላጅ አጥ ሆነው እንዲያደጉ ማድረግ በሀገር ላይ ሁለንተናዊ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሰል ችግሮች በመዲናዋ እየተስፋፉ መምጣታቸውን አንስተው፤ ከ3 መቶው ሕጻናት በተጨማሪ በቅርቡ አንድ መቶ አምሳ ሕጻናት ከተለያዩ አካባቢዎች ተገኝተው ወደ ማዕከሉ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
ወላጆች ሕጻናትን በተለያዩ ቦታዎች ለመተዋቸው ዋንኛው ምክንያት ድህነት መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ መሰል ድርጊቶችን መፈጸም ከሀይማኖት እና ባህል ጋር የሚጣረስ እንዲሁም ፍጹም ከኢትዮጵያዊነት ያፈነገጠ በመሆኑ ወላጆች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስበዋል፡፡
በዚህ ማዕከል ውስጥ ሕጻናትን በመንከባከብ፣ በመጠበቅ እና በማስተማር ደረጃ በመንግሥት በኩል በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ስለመሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ኃላፊው አያይዘውም የችግሩን መስፋፋት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በ3 ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ አንድ ሺሕ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት እንደሚገነቡ ተናግረዋል።
#አሀዱ
======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA