ሽሽት‼️
በ #አዋሽ_ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አጎራባች ስፍራዎች እየሸሹ መሆኑ ተገለጸ‼️
በ #አፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ ከሰሞኑን በተደጋጋሚ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በርካታ ሰዎች አከባቢያቸውን ለቀው አጎራባች ወደሆኑ ስፍራዎች እየሸሹ ነው።
የአካባቢው ነዋሪ በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት አስፋልት ሲሰነጠቅ ማየታቸውን ገልጸው አሁን ላይ ስንጣቂው እየሰፋ መምጣቱን እና ከሰዎች መኖሪያ ቤት ውስጥ ሳይቀር ውሃ ሲፈልቅ ማየታቸውን ጠቁመዋል። በተለይም በአርብሃራ እና ቦሊቃ መካከል የተሰነጠቀው አስፋልት ጥልቀቱ በጣም ትልቅ መሆኑ ገለጿል።
የአዋሻ ፈንታሌ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አደን በለአ በበኩላቸው የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቱ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ሳቡሬ ቀበሌ የሚገኘው የኡንጋይቱ መጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ላይ ጉዳት መድረሱንና ትምህርት መቋረጡን አረጋግጠዋል። በተጨማሪም በዱሃ ቀበሌ የሚገኝ መስጂድ ላይ መሰነጣጠቅ አጋጥሟል ብለዋል።
#አዲስስታንዳርድ
=======================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA