የህወሓት ምላሽ‼️
ምርጫ ቦርድ ቢሰርዝም/ባይሰርዝም ፋይዳ የለውም:-ህወሃት‼️
በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ህወሓት በፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ ከአሸባሪነት ተሰርዞ ወደ ህጋዊ ማንነቱ እንዲመለስ እንጂ እንደ አዲስ ፓርቲ ለመመዝገብ ጠይቆ አያውቅም። ስለዚህ ህወሓት የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ያልጠየቀውን፣ያልተቀበለውን እና በህግ ላይ ያልተመሰረተ ዕውቅና ቢሰርዝም ባይሰርዝም ህጋዊ ፋይዳ የለውም። በፍትህ ሚኒስቴር ተፃፈ የተባለው ደብዳቤም ያልተጠየቀ እና ህወሓት የማያውቀው ነው ብሏል። እንዲሁም በይዘቱ በፍጹም አንስማማም ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት በሚመለከተው ህግ መሰረት የወያኔን ህጋዊ አቋም ማስመለሱ ከባድ አልነበረም። የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶሪያን መንፈስ እና ፅሁፍ በትክክል በመተግበር የትግራይን ህዝብ ችግር ለማቃለል ግዳጁን መወጣት አልቻለም ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት በህወሀት ህጋዊ ሰውነት መመለስ ዙሪያ ያለውን አላስፈላጊ ጥፋት ለኢትዮጵያ መንግስት ለማስረዳትና በውይይት ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ መንግስትም ጉዳዩን በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት ገልጿል። መፍትሄዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ቀጣይ ውይይቶች እየተደረጉ ነው። ይህ አበረታች ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በቅርቡ ይጠናቀቃል ብለን እናምናለን።
ፕሪቶሪያ ፖለቲካ ነው ማንም ሰው በቴክኒክ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ እንዲበላሽ ካደረገ ተጠያቂው እራሱ ነው እንጂ ወያኔ አይደለም ብሏል።
በተጨማሪም የፕሪቶሪያ ስምምነት በአስቸኳይ እንዲተገበር እንጠይቃለን"ሲል በመግለጫው አስታውቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @Akiyas21bot
@ET_SEBER_ZENA