ልጅ አያቱ በእርሳስ ደብዳቤ ስትፅፍ ይመለከታል "አያቴ የምትፅፊው ስለ እኔና አንቺ ነው ወይስ ስለ እኔ ብቻ ነው?
"
አያቱም መፃፏን አቁማ "በእርግጥ የምፅፈው ስለ አንተ ነው ከምፅፋቸው ቃላቶች ይልቅ ትልቁ ነገር የምፅፍበት እርሳስ ነው።ስታድግ ይህን እርሳስ እንደምትወደው እርግጠኛ ነኝ።"
ልጁም እርሳሱን በንቀት እየተመለከተ "ይህ እርሳስ እኮ ተራ ነው እስካሁን ካየኋቸው እርሳሶች በምን ይለያል?"
"እሱ የሚወሰነው ነገሮችን በምታይበት መንገድ ነው።ይህ እርሳስ 5 ጥበቦች አሉት
አንደኛው ጥበብ :ብዙ መልካም ነገሮችን መከወን ትችላለህ ነግር ግን እኔ ይህን እርሳስ እርምጃውን እየመራሁ እንደምፅፍበት ሁሉ አንተንም በእያንዳንዷ እርምጃህ የሚመራህ አምላክ እንዳለ ሁሌም አስታውስ።
ሁለተኛው ጥበብ: መፃፌን ለአፍታ አቁሜ መቀረጫ አውጥቼ እርሳሱን እቀርፀዋለሁ፤እርሳሱ በመጠኑም ቢሆን ሊጎዳ ይችላል ነገር ግን ከበፊቱ ይበልጥ የሰላ ይሆናል።አንተም ሀዘንና መከራ ሲግጥሙህ ይበልጥ ህይወትህን እንደሚቀርፁትና የተሻለ ሰው እንደሚያደርጉህ አስብ።
ሶስተኛው ጥበብ፣እርሳስ ስህተቶችን እንድናስተካክል ማጥፊያ እንድንጠቀም ይፈቅድልናል።ይህ ማለት ችግርን ማረም ስህተት አይደለም፣በፍትህ መንገድ እንድንሄድ ያደርገናልና።
አራተኛው ጥበብ:የእርሳስ ትልቁ ነገር ከውጭ የሚታየው እንጨት ሳይሆን ከውስጥ ያለው ግራፋይት ነው።አንተም ከውጫዊው ማንነትህ ይልቅ ውስጥህ ስለሚሆነው ነገር ልትጨነቅ ይገባሀል።
አምስተኛውና የመጨረሻው ጥበብ እርሳስ ምልክትን ትቶ ያልፋል።እንተም በእያንዳንዷ ቀን የምታደርገው ነገር ሁሉ ምልክትን ትቶ ማለፉ አይቀርምና የምታደርጋቸውን ነግሮች ሁሉ አመዛዝነህ አድርግ"
story of apencil by paulo coehlo
✅️@Enmare1988
✅️✅️@Enmare1988