ቤተመንግስት ተገኘ የተባለው ወርቅ ከተሸጠ የመንግስት አካላት ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው እናት ፓርቲ ገለፀ‼️
ፓርቲው ባወጣው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት “ባደረግነው የብሔራዊ ቤተ መንግሥት እድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪ.ግ. ወርቅ ኮሚቴ አቋቁመን ወደ ብሔራዊ ባንክ አስገብተናል” በሚል ያቀረቡት ገለፃ ላይ ለህዝብ ማብራርያ እንዲሰጡ ጠይቋል።
"የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ግልጽ አይደለም" ያለው ፓርቲው "ከእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አስቀድሞ ለ44 ዓመታት ደርግ እና ኢህአዴግ ሲመሩ ይህ የተጠቀሰው ወርቅ ከእይታ ተሰውሮ ተደብቆ የተገኘ አዲስ ግኝት ወይንስ የአገር ቅርስ በመሆኑ ለጥፋት እንዳይጋለጥ ተጠብቆ የቆየ ነው?" የሚለው ምላሽ እንደሚፈልግ ገልጿል።
እናት ፓርቲ በመግለጫው በጠ/ሚኒስትሩ የተጠቀሰው ወርቅ በቤተ መንግሥት አገልግሎት ላይ ይውሉ የነበሩ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ወይንም ለነገሥታቱ ከውጭ አገራት መንግሥታት የተበረከቱ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከሆኑ እነዚህ ወርቅ ተብለው በወርቅ ዋጋ የሚገመቱና ተመዝግበው በብሔራዊ ባንክ የሚቀመጡ ባንኩም አግባብነት አለው ባለው ጊዜ የሚሸጠው ንብረት ሊሆኑ ከቶውንም አይችሉም ብሏል።
ይህን መሰል የአገር ቅርስ ወደ ተራ ወርቅነት ተለውጦ መልኩን እንዲቀይርና በወርቅም ሆነ በሌላ መልኩ ተሸጦ ወደ ገንዘብ የሚለወጥ ከሆነ የኢትዮጵያ መንግሥት በአጠቃላይና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን በተለይ የጋራ ተጠያቂነት እንደሚጠብቃቸው በመረዳት ከዚህ መሰል የጥፋት ሥራ እንዲታቀቡ እናት ፓርቲ በጽኑ ያሳስባል በማለት መግለጫውን አጠቃሏል።
@Esat_tv1