ዩክሬን የሩሲያ ግዛት ውስጥ ዘልቃ በአሜሪካ ሚሳኤሎች እንድትመታ ባይደን ፈቃድ ሰጡ‼️
ዩክሬን አሜሪካ የሰጠቻትን የረዥም ርቀት ሚሳዔሎች ተጠቅማ ወደ ሩሲያ ግዛት ዘልቃ መምታት እንደምትችል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፈቃድ ሰጡ።እርምጃው አሜሪካ በፖሊሲዋ ላይ ያደረገችው ትልቅ ለውጥ መሆኑን አንድ የአገሪቱ ባለስልጣን ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ አረጋግጠዋል።የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ አገራቸው ከድንበራቸው አልፈው ለመምታት እንዲችሉ ኤቲኤሲኤምኤስ በመባል የሚታወቁት ሚሳኤሎች ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ለወራት ሲወተውቱ ቆይተዋል።
ዕሁድ በሰጡት አስተያየት "እንዲህ ያሉ ነገሮች አይነገሩም፤ ሚሳዔሎች በራሳቸው ይናገራሉ" ብለዋል።የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል የምዕራባውያን አገራት ከእንዲህ ዓይነት እርምጃ እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። ካልሆነ ግን ኔቶ በዩክሬን ጦርነት ውስጥ "በቀጥታ መሳተፉን" እንደሚያሳይ ተናግረዋል።ፕሬዝዳንቱ እስካሁን በውሳኔው ላይ አስተያየት ባይሰጡም ከፍተኛ የክሬምሊን ፖለቲከኞች ግን ውሳኔውን ጦርነቱን እንደማባባስ ነው ሲሉ ገልጸውታል።
የዋሽንግተን በኤቲኤሲኤምኤስ ዙሪያ ያሳለፈችው ውሳኔ ኪዬቭ በነሐሴ ወር ድንገተኛ ወረራ ባደረገችበት በሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ያሉ የዩክሬን ሃይሎች ጥበቃ ብቻ እንዲውል ተወስኗል።በዚህም ዩክሬን የያዘችውን አነስተኛ የሩሲያ መሬት በመያዝ ወደፊት ለሚደረገው ማንኛውም ድርድር እንደትልቅ መደራደሪያ ልትጠቀመው እንደምትችል የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን አስታውቋል።
በኪዬቭ የሚገኘው የዩክሬን የጸጥታ እና የትብብር ማዕከል ሊቀመንበር ሰርሂ ኩዛን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጆ ባይደን ውሳኔ ለአገሪቱ “በጣም ጠቃሚ” ነው።“ጦርነቱን የሚቀይር ውሳኔ ባይሆንም ግን ኃይላችንን የበለጠ እኩል የሚያደርግ ይመስለኛል” ብለዋል።
ኤቲኤሲኤምኤስ እስከ 300 ኪሜ መምዘግዘግ ይችላል። ስማቸው ያልተጠቀሰው የአሜሪካ ባለስልጣናት ለኒውዮርክ ታይምስ እና ለዋሽንግተን ፖስት እንደተናገሩት የክሬንን ኤቲኤሲኤምኤስ እንድትጠቀም በባይደን የተፈቀደው የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ከሩሲያ ጎን ሆነው በዩክሬን እንዲዋጉ ለፈቀደችበት ውሳኔ ምላሽ እንዲሆን ነው።ኩዛን በበኩላቸው የእሑዱ ውሳኔ የዩክሬን ሃይሎችን ከሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ለማስወጣት ታስቦ በሩስያ እና በኮሪያ ወታደሮች ሊከፈት ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው ጥቃት አስቀድሞ የመጣ ነው ብለዋል። ጥቃቱ በቀጣይ ቀናት እንደሚፈጸም ይጠበቃል።
እንደዩክሬን ከሆነ በኩርስክ 11 ሺህ የሚጠጉ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች እንዳሉ ግምቷን አስቀምጣለች።የፕሬዚዳንት ባይደን ውሳኔ ብሪታንያ እና ፈረንሣይ ስቶርም ሻዶው የተባሉ የረዥም ርቀት ሚሳዔሎችን ዩክሬን እንድትጠቀም ፈቃድ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።ዩናይትድ ኪንግደምም ሆነች ፈረንሳይ ከባይደን ውሳኔ ጋር በተያያዘ እስካሁን አስተያየት አልሰጡም።
@Esat_tv1