የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው‼️
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶጋን፣ በኢትዮጵያና ሱማሊያ ይፋዊ ጉብኝት ሊያደርጉ ማቀዳቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን በኹለቱ አገራት ጉብኝት ለማድረግ ያቀዱት፣ ከቀጣዩ ጥር እስከ የካቲት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ እንደኾነ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ የገለጡት፣ ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ጥር ወር ከሶማሌላንድ ራስ ገዝ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ በኹለቱ አገራት መካከል በባሕር በር ዙሪያ የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቁርሾ አንካራ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይንና ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድን በማሸማገል በፈቱ ማግስት ነው።
@Esat_tv1