ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከአየር ጥቃት ተረፉ‼️
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በየመን በአየር ማረፊያ ሳሉ በደረሰ የአየር ጥቃት መትረፋቸውን ገለጹ፡፡
እስራኤል በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኙት የሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተሰምቷል፡፡
በዚህም በሰንዓ አየር ማረፊያ የነበሩት ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን ገልጸዋል፡፡
የሰነዓ አየር ማረፊያ ተጠግኖ አገልገሎት መስጠት እስከሚጀምርም ዋና ዳይሬክተሩ እና ቡድናቸው በሰነዓ እንደሚቆዩ ጠቁመዋል፡፡
ዶክተር ቴድሮስ በአደጋው ህይዎታቸው ላለፉትና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡ዋና ዳይሬክተሩ ወደ የመን ያቀኑት በሀገሪቱ የታሰሩትን የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች እንዲለቀቁ ለመደራደርና በየመን ያለውን የጤና እና ሰብዓዊ ሁኔታን ለመገምገም እንደነበር ገልጸዋል።
@Esat_tv1