በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ለመጓዝ ፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ ሊሆን ነው‼️
የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ከየካቲት 2017 አ.ም ጀምሮ በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ለመጓዝ ተጓዦች ፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ እንዳለባቸው አስታውቋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከየካቲት 2017 ጀምሮ በኦንላይን ቦታ በማስያዝ የህዝብ መንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ነው የገለጹት።
በዚህም ጥራት ያለዉና እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት ለመስጠት፣ ትክክለኛ የመንገደኛ መረጃን ለማረጋገጥ እና ከችግር የጸዳ ጉዞን ለማመቻቸት እንዲሁም የሀገር ውስጥ ተሳፋሪዎች ቦታ ለመያዝም ሆነ ለመጓዝ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ በመስፈርትነት መቀመጡን ነው ያስታወቁት።
በኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት ባለፉት 6 ወራት 165 ሺህ 639 መንገደኞችንና 934 ሺህ ቶን ጭነት ማጓጓዝ መቻሉን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር መረጃ ያሳያል።
@Esat_tv1