ሓበን የማነ የተባለች ወጣትን በጭካኔ በመግደል ክስ የተመሰረተበት ዳዊት ዘርኡ የተባለ ወንጀለኛ ትናንት ጥር 28/2017 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈርዶበታል‼️
ፍርዱን ያሳለፈው የመቐለ ማእከላዊ ፍርድ ቤት ሲሆን አሰቃቂ ግድያው በትግራይ ፣ መቐለ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ዓዲሓ ተብሎ በሚጠራው ልዩ ሰፈር በሚገኝ የአንድ ሆቴል ክፍል ነበር የተፈፀመው።
ሓበን የማነ የ19 ዓመት ወጣት ስትሆን በሆቴል ክፍል በቢላዋ ተገድላ መገኘቷንና ጥቅምት 20 /2017 ዓ.ም ከሰአት በኋላ የቀብር ስነ-ሰርዓት መከናወኑ በወቅቱ መረጃ አድርሰናችሁ ነበር።
ፓሊስ አሰቃቂ የግድያ ተግባሩ አስመልክቶ በወቅቱ በሰጠው መረጃ ፤ የነፍስሄር ወጣት ሓበን የማነ አስከሬን ከ2 ቀን በኋላ ነው በተገደለችበት የሆቴል ክፍል የተገኘው።
ገዳይ ወንጀለኛው አሰቃቂ ተግባሩ በመቐለ ከተማ ከፈፀመ በኋላ በአማራ ክልል በኩል በድብቅ ለውጣት ሲያሴር ደሴ ከተማ በአማራ ክልል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ለትግራይ ክልል ፓሊስ ተላልፎ ተሰጥቷል።
በወቅቱም ለደሴ ህዝብና ለአማራ ክልል ፖሊስ ምስጋና ቀርቦ ነበር።
ፓሊስ ጉዳዩ አጣርቶ አቃቤ ህግ ክሰ መስርቶ ሲከራከር ከቆየ በኋላ ትናንት እሮብ ጥር 28/2017 ዓ.ም የመቐለ ማእከላይ ፍርድ ቤት ባዋለው ችሎት ወንጀለኛው በዕድሜ ልክ ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
@Esat_tv1