🗣️| ማርቲን Ødegaard ስለ ቶተንሃም ጨዋታ፡
🎙“ቶተንሃም በዚህ የውድድር ዘመን ውጤታቸው አንጻር ትንሽ ወጥነት የጎደለው ጉዞ ነበር ነገርግን ምንም እንኳን ወጥ አቋም ማሳየት ባይችሉም እነሱ በጣም ከፍተኛ ደረጃ እና በጣም ከፍተኛ ጨዋታ እንደሆነ እናውቃለን።"
🎙"ጥሩ ቡድን አላቸው ማንንም ማሸነፍ ይችላሉ፣ እናም በዚህ ሰሞን ያንን ሲያደርጉ አይተናል። እግር ኳስ ላይ መሠረት ያረገ ጨዋታን እና ጥሩ እግር ኳስ መጫወት የሚወድ ጥሩ ቡድን ነው ነገርግን እኛ ከዛሬ ጨዋታ የምንፈልገው ዋናው ነገር ማሸነፍ እና ውጤት ማግኘት ነው ለዚህ ደሞ ጥንካሬያችንን መጠቀም የእኛ ትልቁ ሃላፊነት ነው።"
🎙“በዚህ ሲዝን ብዙ ጨዋታውችን እያደረግን ነው ብዙ ውድድሮች ላይ ነበርን ። በሳምንቱ መጨረሻ በአንድ የዋንጫ ዕድላችንን አጥተናል ነገርግን ከፊታችን ብዙ ፈተናዎች አሉን ስለዚህ በቀሩት ውድድሮች ሥኬታማ ለመሆን ሁሉም ሰው አብረን መቆም እና፣ ጠንክረን መስራት፣ መረዳዳትን እና መደጋገፍን መቀጠል አለብን።"
[አርሰናል]
SHARE
@ETHIO_ARSENAL