በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ድርቅ እና የምግብ እጥረት ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ጨምሮ 10 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ወረዳው አስታወቀ።
በክልሉ ባለው ግጭት እና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖ ምክንያት ወረዳው ለድርቅ እና የምግብ እጥረት መጋለጡን የቡግና ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ገ/መስቀል ዓለሙ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል የተነሳው ግጭት አንድ ዓመት ከመንፈቅ ያለፈው ሲሆን ከግጭቱ ባለፈ ወረዳው "ዝናብ አጠር እና በተፈጥሮ የተጎዳ ነው" ያሉት ኃላፊው በተደራራቢ ችግሮች ምክንያት የምግብ እጥረት መከሰቱን አስታውቀዋል።
"ማኅበረሰቡ ምርት ባለማግኘቱ እናቶች ልጆቻቸውን በአግባቡ መግበው የተሻለ የጤና እድገት እንዳይኖራቸው [አድርጓል]" ሲሉ ተፈጥሯዊውን ተጽዕኖ የገለጹት አቶ ገ/መስቀል፤ "ረድኤት ድርጅቶችም ለማኅበረሰቡ አልደረሱለትም" ብለዋል።
በወረዳው ብርኮ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ የካባ የአንድ ዓመት ከሦስት ወር መንታ ወንድና ሴት ልጆቻቸው በምግብ እጥረት "ስቃይ" ውስጥ እንደሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
"ምን አግኝተን እንርዳቸው? እስካሁን ድረስ በተቻለን ይዘናቸው ነበር። ከአዲስ ዓመት ወዲህ ግን ምንም ነገር የለም። ተያይዞ ቁልጭልጭ ሆነ እኮ?" ሲሉ ስላሉበት ሁኔታ አስረድተዋል።
"ጡጦ የምልበት ጎን [አቅም] የለኝም። ጡቴን ብቻ ነው ሳጠባቸው የከረምኩት። የጡት ወተት አሁን አነሳቸው፤ እንዴት ይድረሳቸው?. . . የተገኘው ምግብም አልሆናቸው አለ፤ አልስማማቸው አለ።"
ጠላ በመሸጥ ይተዳደሩ ነበሩት ወ/ሮ የካባ ልጆቻቸው ሲታመሙ ስራ እንዳቆሙ ይናገራሉ። ከቤተሰቦቻቸው ያገኙት የነበረውን የምግብ ድጋፍ በማጣታቸው መቸገራቸውንም ያስረዳሉ።[BBC Amharic]
@Ethionews433 @Ethionews433