ወላድ እናት አሳፍሮ ወደ አዲስ አባባ ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ወላዷን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ።
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውጫሌ ወረዳ ዱበር ድልድይ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
የውጫሌ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት እንዳስታወቀው ሰኞ ታህሳስ 14 ማለዳ 2:30 ላይ ለከፍተኛ ህክምና ወላድ አሳፍሮ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ አምቡላንስ ተሽከርካሪ ከኋላ የነበረ አሽከርካሪ ገጭቶት ከመንገድ በማስወጣት 15 ሜትር ድልድይ ውስጥ በመክተቱ የአምቡላንስ አሽከርካሪውን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የውጫሌ ከተማ ሆስፒታል ተሽከርካሪ ለከፍተኛ ህክምና ሪፈር የተባለች ወላድ እናት እና ሁለት አስታማሚዎችን ጭኖ ሲጓዝ በውጫሌ ወረዳ ዱበር ድልድይ ሲደርስ ከጎጃም ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ ኤፍ ኤስ አር የጭነት ተሽከርካሪ ከኋላ ገጭቶት ወላዷን ጨምሮ ነው የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈው፡፡
ከአደጋው የተፈው አንድ ግለሰብ በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን አደጋውን ያደረሰው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲደረግበት ፍሬን እንቢ ብሎኝ ነው በማለት ቃሉን መስጠቱንም ነው የውጫሌ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የጠቆመው፡፡
@Ethionews433 @Ethionews433