ምክር ቤቱ በነገ ውሎው የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ሥርዓትን ለመደንገግ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን ጨምሮ የተለያዩ ሕጎችን መርምሮ ያፀድቃል
*****
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባው የ17ኛ መደበኛ ስብሰባው ቃለ ጉባኤን መርምሮ እንደሚያፀድቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም፥ የፌዴራል የፍትህና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የሚቀርብ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ በመርመር አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።
በተመሳሳይ ምክር ቤቱ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ እንዲሁም የአካባቢና ማህበራዊ ተፅዕኖ ግምገማ ሥርዓትን ለመደንገግ የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችን አስመልክቶ የሚቀረብለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጆቹን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
@Ethionews433 @Ethionews433