የሰራተኞች_የኑሮ_ውድነት_ጫና_መደጎሚያ_የደመወዝ_ማሻሻያ.pdf
#New የደመወዝ ጭማሪው ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለውሳኔ ቀረበ
በቅርቡ ትግበራው የተጀመረውን የአገራችን የተሟላ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች በተለይም ዝቅተኛ የደመወዝ ተከፋይ ሰራተኞች በኑሮ ውድነት እንዳይጎዱ እና ሊደርስ የሚችለውን የኑሮ ጫና በመጠኑም ቢሆን ለመቋቋም እንዲችሉ ከመንግስት በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት የሰራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት ተካሂዷል፡፡
ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ጥናት በገንዘብ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ ተካሄዶ ለማክሮ ኦኮኖሚ ኮሚቴ ቀርቦ ታይቷል።
ለደመወዝ ጭማሪው የሚያስፈልገው ተጨማሪ የወጪ በጀት ከነመጠባበቂያው ብር 91,439,368,014 /ዘጠና አንድ ቢሊዮን አራት መቶ ሰላሣ ዘጠኝ ሚሊዮን ሦስት መቶ ስድሳ ስምንት ሺህ ከአሥራ አራት ብር/ ሲሆን የደመወዝ ማሻሻያ የተደረገላቸው አካላት ዝርዝር ተለይቶ ቀርቧል።
የደመወዝ ጭማሪው ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለውሳኔ የቀረበ ሲሆን ዝርዝር ትግበራውን የገንዘብ ሚኒስቴር እና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጋራ የሚያስፈጽሙት ይሆናል፡፡
ስለዚህ በሁለቱ መ/ቤቶች ተጠንቶና ተደግፎ የቀረበው እና በማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ የታየው የደመወዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲጸድቅ ቀርቧል፡፡
@Ethiopian_Digital_Library