መፅሐፍ ከማሳተማችሁ በፊት - ለማሳተም ሐሳብ ላላችሁ
ብዙ ወዳጆቸ መፅሐፍ ለማሳተም እንደምትፈልጉና ከህትመት ጋር በተያያዘ አስተያየት እንድሰጣችሁ በየጊዜው ትጠይቁኛላችሁ። ምክንያቱ ባይገባኝም በተለይ ሰሞኑን ደግሞ ጥያቄው በዛ ብሏል። አንዳንዶቻችሁ መልስ አለመስጠቴ ትንሽ እንዳሳዘናችሁ ፅፋችሁልኛል። ኩራት አልያም ንቄት ነው ያላችሁኝም አላችሁ። እውነታው በዚህ ጉዳይ ምክርም አስተያየትም መስጠት አስቸጋሪ ሆኖብኝ ነው። የግድ አስተያየቴን መስጠት ካለብኝ ግን ቀጣዮቹን 10 ነጥቦች ላካፍል። የተለየ ሐሳብ ካለም በደስታ እቀበላለሁ።
👉1ኛ. እንኳን ፃፋችሁ፣ መፃፋችሁን ቀጥሉ! ከእናንተ የሚጠበቀው ከባዱ ሀላፊነት ይሄው ነው። የፀሐፊ ስራው ሳይታክት መፃፍ፣መፃፍ አሁንም መፃፍ ነው። ይህ ፅሁፍ ግን ስለመፃፍ ብቻ ሳይሆን ((ስለማሳተም)) ነው።
👉2.መፅሐፍ ስታሳትሙ ለህትመት ያወጣችሁትን ገንዘብ እንደጠፋ፣ እንደተሰረቀ ወይም ፈፅሞ ከዚህ በኋላ እንደማታገኙት ሐብት ቁጠሩት። ከተመለሰ እሰየው! ካልተመለሰም በሞራልም በገንዘብም ህይወታችሁን እንዳያመሳቅል ብዙ ተስፋ አታድርጉ።
👉3.🚫በጣም እንዳትሞክሩት የምመክረው ...ንብረት በመሸጥ፣ በማስያዝ፣ ወይም በብዙ ድካም ለሌላ ጉዳይ ያጠራቀማችሁትን ገንዘብ በማውጣት መፅሐፍ አታሳትሙ። እባካችሁ አታሳትሙ። ስፖንሰር ከተገኘ፣ ለማሳተም ብዙም የገንዘብ ችግር ከሌለባችሁና ለስሜታችሁ ስትሉ ማሳተም ከቻላችሁ ችግር የለውም።
👉4. የግጥም መፅሐፍ ማሳተም አሁን ባለው የመፅሐፍ ገበያ የሚመከር አይደለም።
👉5. ጥሩ ፅፋችሁ በአመታት ድካምና መስዋዕትነት ያሳተማችሁት መፅሐፍ በቀናት ውስጥ በዮ ቲዮብ፣ በሬዲዮ ጣቢያዎች ፣ በቲክቶክና በቴሌግራም አየር ላይ ተበትኖ የሽያጩ ነገር ከአፈር ሲደባለቅ ማየት የዚህ ዘመን የደራሲያን የልብ ስብራት ነው።
👉6. እነእንትና እንኳ ፅፈው ተነቦላቸው የለ የሚል ሞኝ ንፅፅር ውስጥ ራሳችሁን አታስገቡ። ሰወች ምንጊዜም እንደባህር አለት ጫፋቸው ብቻ የሚታይ ፍጥረቶች ናቸው ውሀው ውስጥ ያላቸውን መሠረት አናውቅም።
👉7. ሁልጊዜም ሽፋን ላይ የምታዮት ዋጋ ለደራሲው በቀጥታ የሚደርስ አይደለም። እውነታው ግማሹ እንኳን አይደርሰውም። ስለዚህ ማሳተም ስታስቡ ይሄን ያህል ኮፒ በዚህ ዋጋ ቢሸጥ ከሚል የዋህ "ቀቢፀ ሒሳብ" ውጡ።
👉8. እንዲህም ሆኖ ብዙ መፅሐፍት ይታተማሉ የሚል ግርታ ውስጥ ከሆናችሁ ከብዙወቹ እንደአንዱ ከመሆናችሁ በፊት በእነዚህ ነጥቦች ላይ የራሳችሁን ጥናት ደግሞ አድርጉ። በማይገባኝ ምክንያት ደራሲያን ትክክለኛውን መረጃ እርስ በእርስ አይለዋወጡም።
👉9. መሠረታዊ ችግሩ በሁሉም ዘርፍ ያለው የዋጋ መናር ካለን ደካማ የንባብ ባህል ጋር መዳመሩ ሲሆን በተጨማሪም አንባቢው በተደጋጋሚ በሚታተሙ መፅሐፍት ያሰበውን ያህል እርካታ ማግኘት አለመቻሉ ያሳደረው ተፅዕኖም ቀላል የሚባል አይደለም።
👉10. መፅሐፋችሁ መሸጡ ወይም አለመሸጡ የእናተን ደካማ ደራሲነት ወይም ጥሩ ፀሐፊነት ማረጋገጫ ላይሆን ይችላል። ሊሆን የሚችልበትም አጋጣሚም ይኖራል። የመፅሐፍ ገበያ እብድ ነው። ታዋቂ ሁናችሁ ያጨበጨበው ሁሉ ድራሹ ሊጠፋ በተቃራኒው ድንገት ብቅ ብላችሁ ህዝብ ሊሻማ ጥሩ ሊሸጥና ሊነበብም ይችላል። ግን ከመቶ ሁለትና ሶስት እንኳን ይሄ እድል አይገጥመውም። በበኩሌ ህይወትን ለዕድል መተው ለማንም የምመክረው ነገር አይደለም። ዕድልን በህይወት ውስጥ መጠቀምን እመርጣለሁ። ምክንያቱ ብዙና ውስብስብ ነው። የሆነ ሆኖ የተሻለ ተስፋ ብሰጣችሁ ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን እውነታው ቢታደጋችሁ ይሻላል። አውቃችሁ ተጋፈጡት!!
አሌክስ አብርሃም
@Ethiopian_Digital_Library