ኢትዮ ፖስት 450 ሰራተኞቹን ማሰናበቱ ታወቀ
መንግስታዊው ኢትዮ ፖስት፣ በቀድሞ አጠራሩ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ከ450 በላይ ሰራተኞቹን መቀነሱ ታወቀ።
በኢትዮ ፖስት የተለያዩ ዲስትሪክቶች ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ እና ለጡረታ የደረሱ ሰዎችን ጨምሮ እነዚህ ሰራተኞች አሁን ላይ ተቋሙ ላይ እየተደረገ ካለው 'ሪፎርም' ጋር ተያይዞ መሰናበታቸውን ለመሠረት ሚድያ ጠቁመዋል።
"ያለው ተግባር በጣም የሚያሳዝን ነው። ከማናጀርነት ፖዝሽን ጀምሮ ከፍ እያለ ሲሄድ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የሚተዋወቁ ሰዎች መሠባሰቢያ እየሆነ ነው" የሚሉት ሰራተኞቹ ከታች ያለው ሱፐርቫይዘርና ከፍተኛ ባለሙያ በተቀመጠለት ህግ መሠረት ማደግ ሲገባው በተቋሙ እየተተገበረ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
"ይህ ደግም የሚደረገው ሆነ ተብሎ ለፎርማሊቲ ለውስጥ እድገት እና ለውጭ ተወዳዳሪ በቀናት ልዩነት ማስታወቂያ ይወጣል። ነገር ግን ስለተቋሙ በቂ ልምድ እና እውቀት ያለውን ወደጎን በመተው ከውጭ ለመጣ ተወዳዳሪ ቦታው ይሰጣል" የሚሉት ሰራተኞቹ የመጣው አዲስ ማናጀር ወይም ከዚያ በላይ የተሻለ ስለሆነ ሳይሆን ከውስጥ ካለው ሀላፊ ጋር ትስስር እና ዝምድና ስላለው ነው ብለዋል።
ከሰሞኑ እንደ አንበሳ አውቶቡስ እና ለሚ ኩራ ያሉ ክፍለ ከተሞች በርካታ ሰራተኞቻቸውን ማሰናበታቸው ይታወሳል።
ከሰሞኑ የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ "ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው" ቢባልም ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሊቀነሱ እንደሚችሉ የመንግስት ምንጮቻችንን ጠቅሰን በቅርቡ መረጃ አጋርተን ነበር።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ በአዋጁ አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው በነበሩበት ወቅት ስለ ሰራተኛ ቅነሳው ያነሱት ነገር ባይኖርም በመንግስት አቅጣጫ ከተያዘባቸው ጉዳዮች አንዱ "ከሚያስፈልገው በላይ የመንግስት ሰራተኛ አለ" የሚለው ዋናው መሆኑን ጠቅሰን ነበር።
መሠረት ሚድያ
@Ethiopian_Digital_Library