መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል ይሁንላችሁ!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጉዞና በአደባባይ ከምታከብራቸው ታላላቅ በዓላት አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አከባበር ሃይማኖታዊና ታሪካዊ መሠረት አለው፡፡ ‹‹ጥምቀት›› ማለት በውኃ ውስጥ መጠመቅ፣ መጥለቅ፣ መንጻት ማለት ነው፡፡
የጥምቀት በዓል የሚከበረው በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር ጥር 11 ሲሆን አከባበሩ የሚጀምረው ከተራ በመባል ከሚታወቀው የዋዜማ ዕለት (ጥር 10) ጀምሮ ነው፡፡ ‹‹ከተራ›› መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች ዘንድ በድምቀት የሚከበሩት የከተራና የጥምቀት በዓላት በርካታ ሕዝብ ይታደምባቸዋል።
ምዕመናን ከሕፃን እስከ አዋቂ ያማረ ልብሳቸውን ለብሰው ታቦተ ሕጉን በማጀብ ለማክበር ይሰበሰባሉ፡፡
ታቦተ ሕጉ ከመንበረ ክብሩ ሲነሳ ‹‹ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት›› የሚለው ሰላም በሊቃውንቱና በወጣቱ እየተዘመረ ጉዞ ይቀጥላል፡፡
የወርቅ ካባ ላንቃ የለበሱ ቀሳውስትና መነኮሳት ጥላ የያዙት ከታቦቱ ጎን መስቀልና ጸናጽል የያዙት ከታቦቱ ፊት ይሄዳሉ፡፡
ልብስ ተክህኖ የለበሱ ዲያቆናት ጥላ፣ መስቀልና ቃጭል ይዘው እያቃጨሉ ከቀሳውስቱ ፊት በመሆን ይጓዛሉ፡፡
ከእነዚህም ሌላ ካባ፣ ላንቃ፣ ጥንግ ድርብ፣ መጠምጠሚያ የለበሱ ሊቃውንት የብር፣ የነሐስ መቋሚያና ጽናጽል ከበሮ ይዘው ‹‹ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት›› የሚለውን ዜማ እያሸበሸቡ ከዲያቆናቱ በፊት ይጓዛሉ፡፡
@Ethiopian_Digital_Library