በሸገር ራዲዮ 102.1 ላይ የሰማሁት አንድ ታሪክ ደስ ስላለኝ ላካፍላችሁ
ገርጂ አካባቢ የሚኖሩ አባትና ልጅ የወደቀ ገንዘብ ያገኛሉ(911 ዶላር እና 11 ብር)።ከገንዘቡ ጋር የፓስፖርት ኮፒም አብሮ ነበር።ለሰውየው ለመመለስ አስበው በፓስፖርቱ ላይ በተጠቀሰው ስም ያፈላልጉት ገቡ።አጡት። ከፎቶው እንደተረዱት ባለገንዘቡ 'ፈረንጅ ' ነው።
ሁለት አመት ሙሉ ነጭ ሲያዩ እያስቆሙ ስሙን እየጠየቁ ከፎቶው እያመሳከሩ አፈላለጉት። የሰፈር ሰው ሁሉ 'ስለምን ትሞኛላችሁ?! ገንዘቡን ተጠቀሙበት!' አላቸው።የሰው ሃቅ አንነካም አሉ።እንደውም በመሃል ልጅየው ታሞ ሆስፒታል ገባ።ኦፕራሲዮን ይደረግ ተባለ። ገንዘብ ከየት ይምጣ?!
'አባዬ በዛ በፈረንጁ ገንዘብ ልታከም?' አላቸው።
አባት 'አላህ በሰው ሃቅ እንድታተከም አይፈቅድም!ፈቃዱ ከሆነ በጥበቡ ያድንሃል! ' አሉት።ያ ችግርም ታለፈ ።
ከሰሞኑ ገንዘቡን የጣለውን ሰው አገኙት። ህንዳዊ ነው።ያችኑ 911 ዶላርና አብራ የነበረችውን 11 ብር ሰጡት።
ምን ሊል እንደሚችል ገምቱ።
ጋዜጠኛው ሰዎቹንም እሱንም አፈላልጎ ኢንተርቪው አደረጋቸው።
ጠዋት ወደ ስራ እየሄድኩ ህንዳዊው ለኢትዮጵያውያን ያለውን አድናቆት ሲገልጽ እየሰማሁት ልቤ ሲሞቅ ይሰማኝ ነበር!!
አንዳንዴ እንደዚህ አይነት ታሪኮችን ስሰማ ያ የድሮው የኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዳልጠፋ አስብና ደስ ይለኛል።
ከዘገባው የገረመኝ 'ታሪኩን የሰሙ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለአባትና ለልጅ ገንዘብ አሰባስበው 200 ዶላር ላኩላቸው! ' የሚለው ነው።ሰዎቹ በዚህ ደስ ቢላቸውም እኔ ግን ብዙም ደስ አላለኝም። ማድነቅም በትላልቅ ሚዲያዎች ላይ ማቅረብም ያለብን የእነኚህን አይነቶቹን ሰዎች ነበርኮ!
ብዙ ሰዎች የወደቀ ገንዘብ አግኝተው መልሰዋል። የነኚህ ግን ይለያል።ሁለት አመት ሙሉ ያውም ድህነትና ችግር እየፈተነህ?!ሃቁን ለባለሃቁ መመለስ!!
አቅራቢው ጋዜጠኛ ወንድሙ ሃይሉ ነው።
Andualem Buketo
@Ethiopian_Digital_Library