#ExitExam
#Advise
#ክፍል_ሁለት (@ExitExamPrep)
👉ፈተና ላይ በጋራ መስራትን ተማምናችሁ አለመግባት። ፈተናው በኮምፒውተር የታገዘ ስለሆነም በጣም ብዙ ኮድ ነው ያለው። ይሄ የማይቻል ነው እራሳችሁ መስራት የምትችሉትንም ጊዚያችሁን የሚያባክንባችሁ ነው።
👉በምትፈተኑበት ጊዜ የኮምፒውተር ክፍሎችን አለመነካካት እና በስህተት ኮምፒውተራችሁን እንዳትዘጉት መጠንቀቅ። ምክንያቱም እስኪ ከፍት ድረስ ጊዚያችሁን ያባክንባችኋል።
👉የኮምፒውተር እውቀት የለኝም ብላችሁ አትጨነቁ። ፈታኝ መምህራን ያግዟችኋል።
👉በቂ የሆነ እንቅልፍ መተኛት እና እረፍት ማድረግ አለባችሁ። እስከ መጨረሻው ሰአት/ ወደ ፈተና መግቢያ ሰአት ድረስ አታንብቡ
👉ቀድመው የተፈተኑ ተማሪዎች በሚያወሩት ወሬ አለመረበሽ። የሌላው ትምህርት ክፍል ፈተና መክበድ ወይም መቅለል የእናንተን ትምህርት ክፍል ፈተና መክበድ ወይም መቅለል ጋር አይገናኝም። የተለያዩ ትምህርት ክፍል ፈተናን የሚያወጡት የተለያዩ ሰዎች ናቸው። ምንም አይነት ግንኙነት የለውም።
👉ፈተና ወቷል በሚል ወሬ አለመረበሽ። ፈተናው በኮምፒውተር የታገዘ እና በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚያውቁት በመሆኑ የመሰረቅ እድሉ በጣም ጠባብ ነው። ችግሩ ቢከሰት እንኳን ከእናንተ የሚጠበቀው ፈተናችሁን ሳትዘናጉ መስራት ነው። የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይሰጥበታል።
👉ፈተናውን የሚያወጣው ዩኒቨርስቲ ሊያሳስባችሁ አይገባም። ፈተናው የሚወጣው በተማራችሁት መሠረት ስለሆነ ትኩረታችሁ ፈተናው ላይ ብቻ ይሁን።
👉ፈተና ላይ እንዳትቸገሩ ስትመገቡ ምቾት በማይሰጣችሁ ልክ ጠግባችሁ አትብሉ። ውሃም አብዝታችሁ አትጠጡ።
👉በመጨረሻም ለድጋሚ ተፈታኞች እራሳችሁን ጭንቀት ውስጥ መክተትና የበፊቱ ውጤታችሁ አሁን ላይ ተጽእኖ ሊያደርግባችሁ አይገባም። ምክንያቱም ከዚህ በፊት መፈተናችሁ የፈተናውን ይዘት የተረዳችሁበት፣ ከስህተታችሁ የተማራችሁበትና አሁን የተሻለ ውጤት የምታስመዘግቡበት ስለሆነ መጨነቅ የለባችሁም።
ይሄንን መረጃው Exit ለሚፈተኑ ጓደኞቻችሁ (Department Telegram Group ላይ) Forward አድርጉላቸው!
መልካም ፈተና!!!
መልካም ውጤት!!!
©️Agegnehu W. (Asst. Prof.)
ለወቅታዊ መረጃ ይቀላቀሉን
👉ቴሌግራም ቻናላችን: @ExitExamPrep
👉ቴሌግራም ግሩፓችን: @ExitExamSquad