የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማዘመን የጀመራቸው ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ፡፡
ጥር 28 ፣2017 ዓ.ም.
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ ለማዘመን የጀመራቸው ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዬች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል።
ቋሚ ኮሚቴው በጥቁር አንበሳ እና በጐተራ የሚገኘውን የአገልግሎቱን ቢሮ የጐበኘ ሲሆን በተለይ በጐተራ የሚሰጠው አገልግሎት እጅግ ዘመናዊ የሆነ፣ በአንድ መስኮት በርካታ አገልግሎቶችን ማግኘት የሚቻልበት እድልን የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ተቋሙ ከዚህ በፊት በርካታ ችግሮች ያሉበት እንደነበረ ገልፆ የለውጡ አመራር ችግሮቹን ለመፍታት የሄደበት ርቀት እና አገልግሎቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጅ በማዘመን ለህ/ሠቡ ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ያለው ስራ የሚያስደንቅ ነው ብለዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው እየሰራን ያለውን ስራ፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን እና እየፈታን ያለንበትን መንገድ ማየታችሁ ለምናደርገው የኮሙኒኬሽን ስራ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
አክለውም ተቋሙ በርካታ ውስብስብ ችግሮች የነበሩበት ተቋም የነበረ መሆኑን ገልፀው አሁን ላይ የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረጽና እጃችን ላይ ያሉትን ችግሮች ደግሞ በፍጥነት በመፍታት ከሰው ሀይል፣ ከበጀት፣ ከቴክኖሎጅ አኳያ እያሻሻልን መጠናል ብለዋል፡፡
አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግም በተለያዩ ቦታዎች ላይ ቅ/ጽ/ቤት ለመክፈት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የተጠናቀቁ መሆኑንና 1000 የሚሆኑ ሰራተኞችን ለመቅጠር በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ምዝገባ በማድረግ ለቅጥር ሂደት ላይ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ዶ/ር ፈትሂ ማህዲ በበኩላቸው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለዜጐች በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ተቋም እንደመሆኑ ባለፉት አመታት በርካታ ቅሬታዎች የሚነሳበት ተቋም የነበረ መሆኑንና አሁን ላይ ግን ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር ፣ አገልግሎቱን የተቀላጠፈ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጅን ለመጠቀም የሄደበት ርቀት የሚያበረታታ መሆኑን ገልፀው አዲሱን ኢ ፖስፖርት ለመስጠት ከሀገሪቱና ከዜጐች ፍላጐት አንፃር በፍጥነት ወደ ትግበራ እንዲገባ አሳስበዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
--
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia