የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ለገቡ ሰራተኞች በ3 ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
በቅርቡ ወደ ተቋሙ ለገቡ አዲስ ሰራተኞች በmigration ጽንሰ-ሀሳቦች፣ አዝማሚያዎች፣ በተቀናጀ የድንበር አስተዳደር፣ በሥርዓተ-ፆታ እና ፍልሰት፣ በጤና እና ፍልሰት፣ በስደተኞች ጥበቃ እና ድጋፍ ፣ በደንበኞች አያያዝና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናውን ያዘጋጁት አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ነው።
በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአገልግሎቱ የአየር ድንበር አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ወንድሙ ስልጠና በተለያዩ ዙሮችና ተቋማት መሠጠቱ ተቋሙ የተሠጠውን ተልእኮ ለመወጣት አዳዲስ ባለሙያዎች ወደስራው ከመቀላቀላቸው በፊት በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲይዙ ለማድረግና የነቃና የበቃ የሠው ሀይል ወደስራ በማሠማራት የላቀ የስራ አፈፃፀም እንዲመዘገብ ለማስቻል ነው ብለዋል።
አክለውም በተለያዩ ተቋማት ለሁለት ወር ያክል የተሰጠውን ስልጠና ወደ ተግባር በመለወጥ የአገልጋይነት መንፈስን ተላብሶ አብሮ በመስራት እና በታማኝነት ሀገርን በማገልገል ተቋሙ የጀመረው ሁሉን አቀፍ ሪፎርም እንዲሳካ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አደራ ብለዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና IOM ሙሉ ወጪውን ሸፍነው ለሠጡት ስልጠና ምስጋና በማቅረብ በቀጣይም ከተቋማቱ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ በመግለፅ የስልጠና መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/