የቀዳሚው ሙፍቲ'ል ፊትነህ ነገር…
—————
#ክፍል_①
—————
የርእሱ ማብራሪያ:-
ቀዳሚው ሙፍቲ'ል ፊትነህ ማለት:- የተፈለገበት ሰዎች ቅድሚያ ሳይሰጡት በዒልም የሸበቱ የሱንና መሻይኾች እያሉ ቀደም ቀደም ብሎ ምንም እዚህ ግባ የሚባል እውቀት ሳይኖረው በሰለፊይ ጀመዓ መካከል ፊትና ቀስቃሽ ብይን ለመስጠት የሚሽቀዳደምና ብሎም የመሻይኾች መሪ ሆኖ "እኔ አውቅላችኋለሁ" ለማለት ያላሰለሰ ጥረትና ጥድፊያ የሚያደርግ ማለት ነው።
ብዙዎቻችሁ እንደምታውቁት በሀገራችን የሰለፊያ ጀመዓ በተለያዩ ጊዜያት የተለያየ አላማ ባላቸው ግን ደግሞ ከመሰረታዊ የሸሪዓ እውቀት እዚህ ግባ የሚባል ድርሻ በሌላቸውና ምናልባትም ከፊሎች ደግሞ ባለቻቸው ጥቂት እውቀት በሚያምታቱ፣ አላዋቂዎች ዘንድ በሚዲያና በተለያዩ መንገዶች በገነኑ ሰዎች የተለያዩ አደጋዎች ሲያንዣብቡበት ቆይቷል።
ይሁን እንጂ የዓለማቱ ጌታ አምላካችን አላህ ከነቢዩ ﷺ ህልፈት ጀምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ዲኑን እንደጠበቀው ሁሉ፣ በእየ ጊዜው ለዲኑ የሚከላከሉ ሰራዊቶችን ብቅ ያደርጋል። ብዙ ጊዜ በሰለፊያ ጀመዓ ውስጥ የተለያየ የግል አላማቸውን ለማሳካት የተለያየ ጥረት በማድረግ ለመበታተንና የተለያየ ችግር ለመፍጠር ጥረት የሚያደርጉ ሰዎችን በተለያየ መንገድ ያጋልጣቸዋል።
በሌሎች ቀደምቶቹ እንዳየነው ይህ ቀዳሚው ሙፍቲ'ል ፊትነህ በሰለፊያ ጀመዓ መካከል ፊትና ሲቀሰቅስ የእራሱ የሆነ ዋንኛ አላማዎች አሉት። በሰለፊያው ጀመዓ ውስጥ ፊትና የሚፈጥሩ ሰዎች የስልጣን ጥማትም ይሁን ምቀኝነት፣ አለያም የነፍሲያ ስሜት ግልቢያም… ብቻ ግን ሐቁን እያወቁት የራሳቸውን አላማ አንግበው ነው ፊትናውን የሚቀሰቅሱት። የጥመትና የዝንባሌ ባለ ቤቶችን እርቃናቸውን በማስቀረት ረገድ ልዩ ተሰጥዖ ያለው ታላቁ ዓሊም ሸይኹ'ል ኢስላም ኢብኑ ተይሚየህ (ቀደሰላሁ ሩሀህ) እንዲ አሉ:-
قال ابن تيمية رحمه الله :-
" فإن الإنسان قد يعرف أن الحق مع غيره ومع هذا يجحد ذلك لحسده إياه، أو لطلب علوه عليه، أو لهوى النفس، ويحمله ذلك الهوى على أن يعتدي عليه ويرد ما يقول بكل طريق وهو في قلبه يعلم أن الحق معه " [مجموع الفتاوى(١٩١)]
“…አንድ ሰው ሀቁ ከእርሱ ተቃራኒ ካለው አካል ጋር መሆኑን ያውቃል። ከመሆኑም ጋር ግን ያንን አካል ስለ ሚመቃኘው፣ አለያም በእርሱ የበላይ መሆን ስለ ሚፈልግ፣ አለያም ደግሞ ለነፍሲያው ስሜት ሲል ሀቁን ይገፈትረዋል (ይታገለዋል)። ስሜቱን መከተሉም ሀቁን እንዳይቀበለውና ሐቅ መሆኑንም ልቡ እያወቀ በሁሉም መንገድ ውድቅ እንዲያደርገው ያነሳሰዋል።” [መጅሙዕ አል-ፈታዋ 191]
አዎ ይህ የምናየው ተጨባጭ ነው!።
ስለ አላማዎቹ ስናወራ ምናልባትም "ልቤን ሰንጥቃችሁ አያችሁ እንዴ? ወይስ የሩቅ አውቃለሁ ማለት ጀመራችሁ…?" የምትል "ካፈርኩ አይመልሰኝ" አይነት የብልጣ ብልጥ ማጭበርበሪያውን ሊያነሳ ይችላል። አዎ ልብህን ከፍተን አላየንም። አቅሙም የለንም!። ነገር ግን እኛ የምንለው ልክ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳለው ነው:-
عن عبد الله بن عتبة بن مسعود قال: سمعت عمر بن الخطاب رضي الله عنه يقول: "إن ناساً كانوا يُؤخذون بالوحي في عهد رسول الله ﷺ، وإن الوحي قد انقطع وإنما نأخذكم الآن بما ظهر لنا من أعمالكم" أخرجه البخاري، كتاب الشهادات، باب الشهداء العدول، برقم: (2641).
“በመልክተኛው ﷺ ዘመን የነበሩ ሰዎች በወህይ ነበር የሚይዙት፣ አሁን ግን ወህይ ተቋርጧልና እኛ የምንይዛችሁ ከስራችሁ ግልፅ በሆነልን ነገር ነው…።” [ቡኻሪይ 2641 ላይ ዘግበውታል]
አዎ ይህ ታላቁ ሶቢይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳለው እኛ የምንፈርደው በተግባርህና በምትሄደው መርዘኛ አካሄድህ ተመርኩዘን ነው እንጂ የልብህን ተቆጣጣሪ አይደለንም። እንለዋለን።
:
የዚህ ሰው አላማዎቹ አንፃራዊ ልዩነት ቢኖራቸውም አንዱ ሌላኛውን በመመገብ ተደጋግፈው ወደ አንድ አላማ መዳረሻ ናቸው እንጂ ተለያይተው የሚለያዩ አይደሉም።
እነርሱም የሚከተሉት ናቸው:-
1ኛ, ድንበር የለሽ የስልጣንና የበላይነት ጥማት!!
እንደሚታወቀው አላማው ስልጣን የሆነ አካል ኀፍረት የሚባልን ነገር አሽቀንጥሮ ይጥላል። ይህ ደግሞ ከባድ አደጋ ነው። ኀፍረተ-ቢስ የሆነ ሰው በእያንዳንዱ በሚያደርገው እንቅስቃሴ "አላህ ይታዘበኛል" ብሎ አላህን አያፍረውም፣ አይፈራውም። ሰዎችንም አያፍርም። ነቢዩ ﷺ ኀፍረተ-ቢስ የሆነ ሰው ያሻውን እንደሚሰራ ጠቋሚ በሆነው ንግግራቸው እንዲህ ብለዋል:-
عَنْ ابْنِ مَسْعُودٍ عُقْبَةَ بْنِ عَمْرٍو الْأَنْصَارِيِّ الْبَدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم "إنَّ مِمَّا أَدْرَكَ النَّاسُ مِنْ كَلَامِ النُّبُوَّةِ الْأُولَى: إذَا لَمْ تَسْتَحِ فَاصْنَعْ مَا شِئْت" . رَوَاهُ الْبُخَارِيُّ.
ከኢብኑ መስዑድ ዑቅበት ኢብን ዐምሪን አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:-
“ሰዎች ከቀደምት ነቢያቶች ካገኙት ነገር:- የማታፍር ከሆነ ያሻህን ስራ። ማለትን ነው።” [ቡኻሪ 6120 ላይ ዘግበውታል]
ይህ ማለት:- ሀፍረተ-ቢስ ከሆንክ ግድ የለም እንዳሻህ ሁን ተፈቅዶልሃል ማለት ሳይሆን!! ኀፍረተ-ቢስ የሆነ ሰው እንዳሻው ይሆናል፣ አላህንም ሆነ ሰዎችንም የማያፍር እንዳሻው የሚሆን ስርኣት አልበኛ ጀሀነምና ጀነት መኖራቸውንም የሚዘነጋ መናጤ ሰው ነው የሚል ጠንካራ ወቀሳ ነው። ምክንያቱም የዚህ ተቃራኒ ሀፍረተኛ የሆነን ሰው የሚያበረታታ ብዙ ሙስሊሞች የሚያውቁት "ሀያእ ከኢማን ቅርንጫፍ" እንደሆነ የሚገልፅ ሌላ ሀዲስ አለ።
:
አዎን በተጨባጭ የምናውቀውም ነው ኀፍረተ-ቢስ የሆነ ሰው:- በጥፋቱ ላይ አላህን አያፍርም!፣ የአላህን ክቡር ፍጡሮችን አያፍርም!፣ በሚሰራው ጥፋት መላኢካዎችን አያፍር፣ ታላላቅ ሰዎችን አያፍርም!። ገጣሚው እንዲህ ይላል:-
إذا لم تخش عاقبة الليالي
ولم تستح فاصنع ما تشاء
"የሌሊቶችን መጨረሻ የማትፈራና የማታፍር ከሆንክ ያሻህን ስራ"
የስልጣን ጥመኛ ሲሆን ግዴታ ይህን ነገር አሽቀንጥሮ መጣል ይጠበቅበታል። ትላንት ወዳጅ ያደረገውን አካል ዛሬ ከአላማውና አካሄዱ ጋር ካልገጠመ ያለ አንዳች ሀፍረት አሽቀንጥሮ መጣል ይጠበቅበታል። ትላንት እውነተኛ ነው ያለውን አካል ዛሬ ከአላማው ጋር የማይሄድ ከሆነ የለየለት ውሸታም ነው ማለት ይጠበቅበታል። ምክንያቱም ይህ አካል የራሱ የሆነ አላማ አለው፣ "አላማህ ትክክል አይደለም! ከያዝከው የጥፋት አላማህ ተመለስ…" ያለው ሁሉ ጥላቱ ነውና ባለ በሌለ ሁሉ ተባዝቶ፣ ተዋሽቶ፣ ተቀጥፎበትም ይሁን መወገድ አለበት የሚል አቋም ይዛል። ምን ይህ ብቻ ልክ በአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን እንደምናውቀው ማስገደል ካለበትና የሚችል ከሆነም ሊያስገድል ይችላል።
በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል…
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa