📌በቀዷና በቀደር ማመን
(ከሸህ ሷሊህ ፈውዛን - ሀፊዞሁሏህ - ደርስ በአማርኛ ተተርጉሞ የቀረበ)
(ክፍል አምስት)
ክፍል 1 ⤵️ (ያለፉ ክፍሎች)
https://t.me/alateriqilhaq/5054
ክፍል 2 ⤵️
https://t.me/alateriqilhaq/5057
ክፍል 3 ⤵️
https://t.me/alateriqilhaq/5060
ክፍል 4 ⤵️
https://t.me/alateriqilhaq/5062
በቀዷ በቀደር የማመን ፍሬዎቹ
በቀዷ በቀደር ከማመን ፍሬዎች ትልቁ ፣ የግለሰቡ እምነት ጤናማ ሆኖ ማእዘኖቹ መሟላታቸው ነው፡፡ ምክንያቱም ቁርዓን እና ሱና እንደሚጠቁመው ፣ በዚህ ማመን በእርሱ እንጅ እምነት የማይረጋገጥበት ከሆኑት ከስድስቱ ኢማን መሰረቶች አንዱ በመሆኑ ነው፡፡
በቀዷ በቀደር በማመን ከሚገኙ ፍሬዎች መካከል የልብ መረጋጋት እና እረፍት ይገኛል፡፡ በዚህ አለም በሰው ልጅ ሂዎት ላይ ችግሮች ሲጋረጡ መጨናነቅ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ የአላህ መልክተኛ እንደተናገሩት የሚደርስበት ነገር ሁሉ በአላሀ ውሳኔ መሆኑን ካወቀ ፣ ““እወቅ የሚደርስብህ ነገር የሚስትህ አይደለም ፤ የሚስትህ ደግ የሚደርስብህ አይደለም” የሚለውን የአላህ መልክተኛ ንግግር ከተገነዘበ እንዲሁም የሚደርስበት ነገር የማይቀር ፣ ምንም አይነት መላሽ የሌለው መሆኑን ከተገነዘበ ነፍሱ ትረጋጋለች ፣ ልቡ የተደላደለ ይሆናል፡፡
በዚህ ተቀራኒ በቀዷ በቀደር የማያምን ፣ ሀሳብ እና ሐዘን ትይዘዋለች፡፡ ጭንቀት ይረብሸዋል፡፡ በሂዎት ተጨናንቆ ከእርሷ ለመገላገል ራሱን እስከማጥፋት ይደርሳል፡፡ ከደረሰባቸው ችግር ለመሸሽ እና የወደፊት ተስፋቸው በመጨለሙ ከዚህ ነገር ይገላግለናል ብለው ራሳቸውን የሚያጠፉ ሰዎች ቁጥር መብዛቱ የሚስተዋል ነው - ምክንያቱም እነርሱ በቀዷ በቀደር አያምኑምና፡፡ ይህ እንቅስቃሴያቸው የአቂዳቸው መጥፎነት ውጤት ነው፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል
“በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ፣ ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትሆን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፤ (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ ፣ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም፡፡”
(ሀዲድ ፡22-23)
አላህ በምድርም ይሁን በነፍሶች ውስጥ የሚከሰቱ መከራዎች የተወሰኑ መሆናቸውን ተናገረ፡፡ የፈለግነውን መከላከል ብንሞክር እርሱ ተወስኗል ፣ ተጽፏል ፣ ከመከሰት የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ከዚያም ይህን ያደረገበት ጥበቡ የመከራ ጊዜ እንድንረጋጋ ፣ እንዳንበሳጭ ፣ እንዳንቆጭ ፤ ጸጋ ስናገኝ ደግሞ ቅጣትን የሚያስረሳ ደስታ እንዳንደሰት መሆኑን አላህ ግልጽ አደረገ፡፡ ይልቁንም የመከራ ጊዜ ትግስት ማድረግ ፣ ከአላህ ረህመት ተስፋ አለመቁረጥ በእኛ ላይ ግዴታ ነው፡፡ የምቾት ጊዜ ማመስገን ፣ አላህ አዘናግቶ እኛን አይዘንም ብለን አለመተማመን፡፡ አላህ በሁለቱም ባህሪዎች ከእርሱ ጋር ቁርኝት እንዲኖረን ይፈለጋል፡፡
ኢክሪማ የሚከተለውን ተናገረ ፡ “አንድም አካል አይኖርም ፣ የሚደሰት ወይም የሚያዝን ቢሆን እንጅ፡፡ ነገር ግን ደስታን አድርጉት ምስጋና ፣ ሀዘንን አድርጉት ትግስት፡፡”
ይህ ማለት ግለሰቡን ከመጥፎ የሚጠብቁ ፣ መልካም የሚያመጡ ሰበብ ነገሮችን አይጠቀም ማለት አይደለም፡፡ አንዳንድ ጃሂሎች እንደሚገምቱት በቀዷ በቀደር ይመካ ማለት አይደለም፡፡ ይህ ትልቅ የሆነ ስህተት እና ማህይምነት ነው፡፡ አላህ ሰበብ ነገሮችን እንድንጠቀም አዞናል ፣ ከስንፍና እና ከቸልተኝነት ከልክሎናል፡፡ ነገር ግን ሰበብ ነገሮችን ተጠቅመን በምንፈልገው ተቃራኒ ከተከሰተ መናደድ የለብንም - ምክንያቱም ይህ ቀዷ ቀደር ነውና፡፡ ሌላ ቢወሰን ኖሮ ፣ ይሆን ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ነብዩ የሚከተለውን ተናግረዋል ፡
“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎት ይኑርህ፡፡ በአላህ ታገዝ፡፡ አትቆጭ፡፡ አንድ ነገር ቢገጥምህ ፣ ይህን ብሰራው ኖሮ ፣ እንዲህ እንዲህ ይሆን ነበር አትበል፡፡ ነገር ግን አላህ ወሰነው የፈለገውን ሰራ በል፡፡ “ለው” ያለችው ቃል የሰይጣንን ተግባር ትከፍታለች፡፡” ሙስሊም ዘግቦታል፡፡
ይህ ከመሆኑ ጋር ግለሰቡ ነፍሱን ሂሳብ ያድርግ፡፡ ስህተቶቹን ያርም፡፡ አንድም ነገር አይደርስበትም ፣ በወንጀሎቹ ሰበብ እንጅ፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል ፡
“ከመከራም ማንኛውም ያገኛችሁ ነገር እጆቻችሁ በሰሩት (ሐጢአት) ምክንያት ነው፡፡” (ሹራ ፡ 30)
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة