የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ dan repost
ዕውቀት እና የዕውቀት ባለቤቶች ደረጃ
ክፍል ሁለት
ለሸሪዓ እውቀት ባለቤቶች አላህ ልቅና እና ክብር ሰጧቸዋል፤ በተውሂዱና በኢኽላሱ ላይ እነርሱን አስመስክሯቸዋል ፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናገሯል፡-
"شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ"
"አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡"
(አል-ዒምራን -18)
እርሱ ብቸኛ ተመላኪ ለመሆኑ ከመላኢካዎች ጋር የእውቀት ባለቤቶችን አስመሰከረ ፤ የሸሪኣ እውቀት ባለቤቶች ኢኽላስ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆኑን ፣ የአለማት ጌታ እርሱ መሆኑን፣ እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ መሆኑን ከአላህ ውጭ ያለ አምልኮት ውሸት መሆኑን መስካሪዎች ናቸው፡፡ ለእነርሱ ደረጃ በአላህ ብቸኛ ተመላኪነት ላይ መመስከራቸው ብቻ ይብቃ!
የእውቀት ባለቤቶች ከሌላው ጋር እኩል እንዳልሆኑ አላህ እንደሚከተለው ተናግሯል፡-
قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ
«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡"
(ዙመር -9)
۞ أَفَمَن يَعْلَمُ أَنَّمَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ الْحَقُّ كَمَنْ هُوَ أَعْمَىٰ ۚ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ
"ከጌታህ ወዳንተ የተወረደው እውነት መኾኑን የሚያውቅ ሰው እንደዚያ እርሱ ዕውር እንደኾነው ሰው ነውን የሚገሠጹት የአእምሮ ባለቤቶች ብቻ ናቸው፡፡"
(ረዕድ-19)
አላህ ያወረደው እውነት እና ቅን መመሪያ የስኬት መንገድ መሆኑን የሚያውቁ እና ከዚህ መንገድ ፣ ከዚህ እውቀት ከታወሩት ጋር እኩል ይሆናሉ? በፍጹም እኩል ሊሆኑ አይችሉም።
በእነዚያ እና በእነዚህ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፤
ሀቅን ባወቀ ፣ በብርሃኑ ችቦን በለኮሰ ፣ ጌታውን እስከሚገናኝ ድረስ በቅኑ ጎዳና ላይ የተጓዘ ፣ የስከትን ጎዳና የተጎናጸፈ እና ስሜቱን በመከተል ከዚህ መንገድ የታወረ ፣ በሰይጣን እና በልብ ወለድ መንገድ በተጓዘ መካከል ከፍተኛ ልዩነት አልለ፡፡
እነዚህ እነዚያ በፍጹም እኩል አይሆኑም ፤ የእውቀት ባለቤቶችን ደረጃ ከፍ እንደሚያደርግ አላህ ግልጽ አድርጓል፤ ይህ የሆነው ለሌላ ሳይሆን በሰዎች ላይ ያላቸው መልካም ተጽእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የእውቀት ባለቤቶች የሚከተለውን ይናገራሉ፡-
"فما أحسن أثرهم على الناس ، وأقبح أثر الناس عليهم"
“በሰዎች ላይ ያላቸው መልካም ተጽእኖ ምን አማረ! በእነርሱ ላይ የሰዎችን መጥፎ ተጽእኖ ምን አከፋው!”
ሰዎችን ወደ መልካምና ወደሐቅ አቅጣጫ በመምራታቸው የሰዎች ተጽእኖ በእነርሱ ላይ ከፋ!
ይሁን እጅ ይህ አላህ ያመሰገነው ፣ ሙእሚኖች ያመሰገኑት ፣ በዋነኝነት ዳኢዎችም ይሁኑ ስለአላህ ፣ ስለሸሪዓው አዋቂ የሆኑ ሩሉሎች ያመሰገኙት ታላቅ የሆነ መልካም ተጽእኖ ነው። ከሩሱሎች ቀጥሎ የእነርሱ ተከታዮች ፤ እነርሱ የመጡበትን በጣም አዋቂ ፤ ወደርሱ በተሟላ ሁኔታ ዳዕዋ በማድረግ ፤ በእርሱም ላይ ትግስት በማድረግ ፤ ወደርሱም አቅጣጫ በመስጠት ያመሰገኑት መልካም ተጽዕኖ ነው፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
"አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡"
(ሙጃደላ-11)
وَتِلْكَ حُجَّتُنَا آتَيْنَاهَا إِبْرَاهِيمَ عَلَىٰ قَوْمِهِ ۚ نَرْفَعُ دَرَجَاتٍ مَّن نَّشَاءُ ۗ إِنَّ رَبَّكَ حَكِيمٌ عَلِيمٌ
"ይህችም ማስረጃችን ናት፡፡ ለኢብራሂም በሕዝቦቹ ላይ (አስረጅ እንድትኾን) ሰጠናት፡፡ የምንሻውን ሰው በደረጃዎች ከፍ እናደርጋለን፡፡ ጌታህ ጥበበኛ ዐዋቂ ነውና፡፡"
(አንአም-83)
በአጠቃላይ አላህን መፍራት ከሙእሚኖች ላይ ቢኖርም በተሟላ እና በእውነት አላህን የሚፈሩት ግን የእውቀት ባለቤቶች መሆናቸውን አላህ ግልጽ አደረገ፡፡ ነገር ግን የተሟላው እና ትክክለኛው ፍርሐት ለኡለሞች ነው ፤ በዋነኝነት ሩሱሎች ናቸው፤
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ ۗ إِنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ غَفُورٌ
"አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ብቻ ናቸው፡፡ አላህ አሸናፊ መሓሪ ነው፡፡"
(ፋጢር-28)
አላህን ከባሮቹ ውስጥ የሚፈሩት ዐዋቂዎቹ ናቸው ሲባል የተሟላ ፍርሓት የሚፈሩት ለማለት ነው፡፡
ስለአላህ ፣ ስለስሞቹ ፣ ስለመገለጫው፣ ሩሱሎችን ስለላከበት ሸሪዓ በጣም አዋቂዎቹ ኡለሞች ናቸው፡፡
በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ረሱልን ﷺ የሚከተለውን ጥያቄ ጠየቃቸው፡
“የአላህ መልክተኛ ሆይ! እኛ እንዳንተ አይደለንም ፣ አንተ ከዚህ በፊት ያለንም ይሁን የወደፊቱን ወንጀል አላህ ምሮሃል” አላቸው፡፡ እርሳቸውም “ወሏሂ እኔ ለአላህ በጣም ፈሪያችሁ በጣም ጥንቁቁ ነኝ” አሉት፡፡
ከሩሱሎች በኋላ ከሰዎች በጣም ፈሪው ፤ በእውቀታቸው እና በደረጃቸው መጠን ፣ ሀቅን በመድፈር ከሰዎች ሁሉ ጠንካሮች ፣ ስለአላህ ፣ ስለዲኑ ፣ ስለስሞቹ ፣ ስለመገለጫዎቹ አዋቂ የሆኑት የሸሪዓ ኡለሞች ናቸው፡፡
ከሁሉም በላይ በተሟላና በከፍተኛ ሁኔታ አላህን የሚፈሩት ሩሱሎች ናቸው፤ እነርሱ ለአላህ በጣም ጥንቁቁ ናቸው፤ ከእነርሱ መካከል ደግሞ በእውቀት ፣ አላህን በመፍራት ፣ በጥንቁቅነት ተወዳዳሪ የሌላቸው የእኛ ነብይ ሙሀመድ ﷺ ናቸው፡፡
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة