ቁርኣንን ለማስተንተን የሚረዱ አስር ነጥቦች
—————
① በእራስ ላይ የተረጋጋና የመተናነስን ተፅእኖ እያሳደሩ ማንበብ። እንዲሁም የአንባቢው ግብ ሱራውን መጨረስ ብቻ መሆን የለበትም።
② አንባቢው የተናጋሪውን የአላህን (ጥራት ይገባ ውና) ልቅና በሚያነብበት ጊዜ በልቡ ሊያስገኝ ነው። ለአላህ ቃል ነቃ ሊል! ልቡም ሊረጥብና ሊፈራ! እንዲሁም የአላህን ረህመት ሊከጅል በዚህም ሊደሰት ይገበዋል።
③ ከሸይጧን በአላህ ይጠበቅ! ከሸይጧንም የመጠበቁን እገዛ በልቡ አላህን ሊያስቀምጥ ነው። ምክንያቱም ሸይጧን አንባቢውን የአላህን ቃል አንብቦ እንዳይጠቀምበት ለማድረግ ይሸቀዳደማል።
④ ቁርኣን የሚቀራው ሰው ድምፁን ዝቅ አድርጎ አሳምሮ ልክ ትርጉሙን እንደሚፈልግና እንደሚያጠና መፍጠንንም እንደሚፈራ ሆኖ የአንቀፁን ሀሳብ ባልቋጨበት ቦታ ከማቆምና አለያም ሀሳቡ ምን እንደሆነ ሳያጤናው ማለፍ የለበትም!።
⑤ ቁርኣንን ለማስተንተን ከሚረዳው ነገር ትልቁና አንዱ ከሰማይ ወደ ምድር እንዴት እንደወረደና ነቢዩ ﷺ እንዴት እንደያዙት፣ ከዚያም ሶሃቦች ከነቢዩ ﷺ የመጀመሪያ በሰሙት ጊዜ በነፍሳቸው ላይ ምን አይነት ተፅእኖ እንዳሳደረባቸውና እንዴት ተቀብለው እንደተገበሩት ማወቅ ነው!!።
⑥ ሌላው ወሳኝ ነጥብ በየትኛውም ሁኔታ ስንኖር ለሕይወታችን ቁርኣንን መድኃኒት ማድረግ ነው!!። እናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ስለ ነቢዩ ﷺ ስነ-ምግባር ስትጠየቅ "ስነ-ምግባራቸው ቁርኣን ነበር" ብላ ነው የመለሰችው።
⑦ አንባቢው በነቢያቶችና በደጋጎች ላይ የአላህን ውዳሴ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል። ነቢያቶችንና ደጋጎችን መከተሉ ተፈላጊ መሆኑንም ያውቃል። አላህ ወንጀለኞችንና በደለኞችን የሚወቅስበትን ቦታ ካነበበ አላህ እያናገረው መሆኑን ያውቃል፣ የሚፈለገውም ከነሱ ባህሪ መጠንቀቁና መራቁ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል።
⑧ አንቀፆችን በተደጋጋሚ እንደ አዲስ ማስተንተንና አንዴ ብቻ በማስተንተን አለመገደብ፣ አንዲትን አንቀፅ አንዴ ካስተነተናት በኋላ በዛው ከልቡ ልትቋረጥ አይገባውም!። ሊደጋግማትና ወደርሷም መለስ እያለ ሊያየስተውላት ይገባል!! ትርጉሟም በልቡ እስኪታተም ከአንቀጿ ሊቋረጥ አይገባውም!!።
⑨ ወደራሱ ሊመለከትና ራሱንም ሊፈትሽ ይገበዋል። እውነት ከልቤ አስተንትኜዋለሁ?! ወይስ አላስተነተንኩትም? ብሎ እራሱን ሊጠይቅ ይገበዋል። በውስጣዊና በውጪያዊ ስራው ቁርኣን በሕይወቱ በ(ኢባዳው) በአምልኮው ተፅእኖ መፍጠር አለመፍጠሩን እራሱን ሊፈትሽ ይገበዋል።
10, ከቤተሰባችን ከልጆቻችን በምንቀማመጥበት ጊዜና በምንመካከርበት፣ ሙሃደራ በምናደርግበት፣ እንዲሁም መድረክ ላይ ቆመን ንግግር በምናደርግበት ጊዜ ንግግራችን ሁሉ ሊሆን የሚገባው ቁርኣንን ስለ ማስተንተንና በቁርኣን ስለመተግበር ሊሆን ይገባል!!
እርግጥ ነው! አላህ ግንዛቤውንና ማስታወሱን አግርቶልናል። ከፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ በላይ ከፍ ያለው፣ የላቀው! አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
﴿وَلَقَد يَسَّرنَا القُرآنَ لِلذِّكرِ فَهَل مِن مُدَّكِرٍ﴾ القمر ١٧
“ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፣ ተገንዛቢ አለን?። " አል-ቀመር 17
አላህ በአግባቡ በትክክለኛው መንገድ ለመገንዘብና ለማስተንተን በህጎቹም በትክክል ለመተግበር፣ ስነ-ምግባራችን ቁርኣን እስኪሆንና በአኼራም "ዱኒያ ላይ ታነበው እንደነበረው አንብብ" እስክንባል ይወፍቀን!! አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነውና!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://telegram.me/IbnShifa