ተመድና የአውሮፓ ኅብረት የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ድንበር ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ
የአውሮፓ ኅብረት በጉባዔው ላይ ባቀረበው መግለጫ፣ ሳይወጡ የቀሩ የኤርትራ ወታደሮች ከድንበሩ ለቀው እንዲወጡ፣ ተፈጽመዋል በተባሉ የመብት ጥሰቶች ላይ ተዓማኒና ገለልተኛ አካል ሙሉ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የአውሮፓ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በሰብዓዊ መብትና በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ አገልግሎቶች ላይ ተፈጽመዋል ባላቸው ጥሰቶች ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ጥገኝነት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የሸሹ ኤርትራውያን፣ ፍትሕ ማግኘት አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡
የአውሮፓ ኅብረት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ለጉባዔው ባቀረበው መግለጫ፣ በኤርትራ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያሳስበኛል ብሏል፡፡
በተመሳሳይ በዚሁ መድረክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ባቀረበው መግለጫ፣ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የቆመበትን የፕሪቶሪያ ስምምነት እየጣሱ መሆናቸውን ጠቅሶ ከአካባቢው እንዲወጡ ሲል አሳስቧል፡፡
‹‹የዋና ኮሚሽነሩ ቢሮ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ግልጽ የሆነ ጥቃት፣ ጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የንብረት ዘረፋና የዘፈቀደ እስራት እየፈጸሙ መሆናቸውን ተዓማኒ የሆነ መረጃ አለው፤›› ብሏል፡፡ በመሆኑም የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ በማለት ጥሪ አቅርቧል፡፡
ተመድ በመግለጫው በሁለቱ አገሮች መካከል ሰላም ከወረደ በኋላ፣ የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሠልፈው ሲዋጉ እንደነበር አስታውሷል፡፡
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጰያና በኤርትራ መንግሥታት መካከል በተለያየ መንገድ የሚገለጹ የፖለቲካ ትኩሳቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡
[ @MadoNews ]