MADO NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


. Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
📩 @Mado_Inbox

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ናይጀሪያ በጾም ሰዓት ምግብ ተመግበዋል በሚል 25 ሰዎችን አሰረች‼️

የናይጀሪያዋ ኮኖ ግዛት በረመዳን የጾር ላይ ምግብ ሲመገቡ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን 20 ሰዎች ስራለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አምስት ሰዎች ደግሞ ምግብ ሲሸጡ ነበር በሚል የጣሰሩ ሲሆን ሁሉም ታሳሪዎች በሸሪዓ ህግ እንደሚዳኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚች ግዛት በእስልምና የጾም ወር ወቅት በአደባባይ ምግብ መመገብ ክልክል ነው፡፡

የግዛቲቱ ፖሊስ ያልተገባ የጸጉር አቆራረጥ፣ የተገላለጠ እና ሰውነትን የሚያሳይ አለባበስ የሚከተሉ ሰዎችን እንደሚያስር አስጠንቅቋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው ተመሳሳይ የጾም ወቅት ፖሊስ የማይጾሙ ሰዎችን አስሮ የነበረ ሲሆን ታሳሪዎቹ እንደሚጾሙ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ከእስር ተለቀው ነበርም ተብሏል፡፡

[ @MadoNews ]


ኤርትራ‼️

ኤርትራ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች በጠላት ድሮኖች እና በኦፕሬተሮቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ማደናቀፍ የሚችል  ቋሚ እና በእጅ የሚያዙ የድሮን ማምከኛ/Jammer/ተግባራዊ ማድረጓን ከኤርትራ የዜና ምንጮች ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል‼️
ኤርትራ ይህንን ያደረገችው ድሮኖች በኤርትራ ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ስጋቶችን ለመከላከልና የብሄራዊ ደህንነትን ለማጎልበት ያለመ ነው ተብሏል።
የጽህፈት መሳሪያዎቹ የድሮን ግንኙነቶችን ለመጥለፍ እና ለማጥፋት ሰፊ ሽፋን በመስጠት በተመረጡ ቁልፍ ቦታዎች ላይ ስልታዊ በሆነ መንገድ መተከላቸውን የዜና ምንጩ ጠቅሷል።
የሰው አልባ አውሮፕላኖች የግንኙነት ማደናቀፊያ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈለገው ሀገሪቱ ላይ ጣልቃ በመግባት ጥቃቶችን ወይም የስለላ ተልዕኮዎችን ለመከላከል እና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ያለመ ነው ተብሏል

[ @MadoNews ]


ፕሬዝደንት ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ከተጋጩ በኋላ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጡ

የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የአሜሪካ ኮንግረስ ለዩክሬን የ175 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ እርዳታ ማድረሱን የነንፓርቲዚያን ኮሚቴ መረጃ ያመለክታል
ፕሬዝደንት ትራምፕ ከዘለንስኪ ጋር ከተጋጩ በኋላ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ እርዳታ አቋረጡ።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ሳምንት ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ ለዩክሬን የሚደገውን ወታደራዊ ድጋፍ ማቋረጣቸውን ኃይትሀውስ ማስታወቁ ተገልጿል።

ይህ እርምጃ የመጣው ፕሬዝደንት ትራምፕ ወደ ኃይትሀውስ ከገቡ በኋላ አሜሪካ በዩክሬንና ሩሲያ ላይ የምትከተለውን ፖሊሲ ከቀየሩና ባለፈው አርብ እለት በኃይትሀውስ ከዘለንስኪ ጋር ኃይለቃል ከተለዋወጡ በኋላ ነው።

ፕሬዝደንት ትራምፕ አሜሪካ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ላደረገችው ድጋፍ በቂ ምስጋና አላደረጉም ሲሉ ዘለንስኪን ትችተዋቸዋል።

"ፕሬዝደንቱ ትኩረታቸውን ሰላም መሆኑን ግልጽ አድርገዋል። አጋሮቻችንም ለዚህ አላማ ቁርጠኛ እንዲሆኑ እንፈልጋለን። እርዳታችን ለመፍትሄው አስተዋጵኦ ማበርከቱን ለማረጋገጥ አቋርጠን እየገመገምን ነው" ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኃይትሀውስ ባለስልጣን መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

በዚህ ጉዳይ የፕሬዝደንት ዘለንስኪ ቢሮም ሆነ በአሜሪካ የሚገኘው የዩክሬን ኢምባሲ ያለው ነገር አለመኖሩን ዘገባው ጠቅሷል።
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከኤፒ ጋር በነበራቸው ቆይታ የጦርነቱ ማብቂያ "በጣም፣ በጣም ሩቅ" ብለው መናገራቸው ትራምፕ ተናደው መልስ እንዲሰጡ አድርጓቸዋል።
 
[ @MadoNews ]


የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ማስጠንቀቂያ

የአዲስ አበባ መጅሊስ ከዚህ በኋላ በመስጂዶች ጉዳይ አይታገስም።

1446ኛው ታላቁ የረመዳን ወር መስጂዶች ደምቀውና ተውበው ህዝበ ሙሊሙን በተገቢው መንገድ በመቀበል እያሰተናገዱ ነወ።
በአብዛኛዎቹ መስጂዶች ህዝበ ሙሰሊሙ እምነቱ በሚያዘው መሠረት ዒባዳውን እያከናወነ ሲሆን በጣት በሚቆጠሩ መስጂዶች ሁከት ለማስነሣት የተደረጉ ሙከራዎችን በየመሰጂዱ የሚገኙ ኮሚቴዎች፣ ሀዲሞችና ህብረተሰቡ ባደረገው ጥረት በቁጥጥር ሰር ሊውሉ ችሏል።
    
በተለይም ጠሮ መስጂድ ፣ሎሚ ሜዳ(ዓሊ) መስጂድና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው ሀምዛ መሰጂድ የረመዳንን መግባት ተከትሎ በአንዳንድ  ሰውር አላማ ያላቸው ግለሰቦች ሁከትና ብጥብጥ በማሰነሣት ከፍተኛ ችግር ሲፈጥሩ የቆዩ አካላት መሸሸጊያ ሆኖ የቆየ ቢሆንም መጅሊስ ከዛሬ ነገ ይቀየራሉ ብሎ ሁኔታውን አባታዊ በሆነ ትዕግሰት ይዞት ቆይቷል።

መጅሊሰ በእነዚህ ጥቂት መስጂዶች የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶችን ቢያደርግም ዕድሉን ባለመጠቀም ቡድኑ መሰጂድ ሰብሮ በመግባት፣ ጄነሬተር በማጥፋት፣ ለደህንነት የተገጠመ ካሜራን በመሰባበር እና አማኞች የተረጋጋ ዒባዳ(የአምልኮ ስርዓት) እንዳይከውኑና የረመዳንን ወር የብጥብጥና የረብሻ አውድማ የማድረግ እንቅሰቃሴያቸውን ቀጥለውበታል።

ከወራት በፊት ማዕከላቸውንና የብጥብጥ መነሻቸውን ዓሊ መስጂድ በማድረግ ሴቶችና ህፃናትን ከፊት በማሰለፍና የተወሰኑ ግለሰቦችን በገንዘብ በመደለል የተጀመረው ውንብድና  ኢማሞችን ማይክ ቀምቶ በመደብደብ የተራዊ ሰላት እንዲቋረጥ እሰከ ማድረግ ደርሰዋል።
የአ/አ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
     
[ @MadoNews ]


የዲጂታል ካርታ ጥያቄ ያቀረቡ ተገልጋዮች ይዞታቸውን መነጠቃቸውን ተናገሩ

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የዲጂታል ካርታ ጥያቄ ያቀረቡ ተገልጋዮች ይዞታቸው ለካራ ቆሬ አፓርታማ እንደተሰጠባቸው ተናገሩ።

ለመሠረት ሚዲያ አስተያየታቸውን የሰጡ ባለጉዳዮች እንዳሉት ለመኖሪያ ቤት የዲጂታል ካርታ ጥያቄ በኦላይን ካቀረቡና የአገልግሎት ክፍያ በቴሌ ብር በኩሉ እንዲከፍሉ ከተደረገ በኋላ የኦላይን አገልግሎቱ መቋረጡን እና ሰነዳችሁ አልተሟላም ተብለው በኦላይን መልስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። 

አገልግሎቱ ለምን እንደተቋረጠባቸው ለመጠየቅ ወደ ክፍለ ከተማው ባቀኑበት ጊዜ ደግሞ ይዞታቸው ለካራ ቆሬ አፓርታማ እንደተሰጠባቸው በመሃንዲሶች በኩል መገለጹን እንደሰሙ አስረድተዋል።

"መፍትሄ የሚሰጠን አካል የለም" የሚሉት የክፍለ ከተማው የዲጂታል ካርታ ተገልጋዮች "ለበርካታ አመታት ለፍተን የሰራነውን ቤትና ይዞታ በቀላሉ ለካራ ቆሬ አፓርታማ ተሰጥቷል መባሉን አንቀበልም" ብለዋል።
መሰረት ሚዲያ

[ @MadoNews ]


👀በስህተት የባንኩን ጠቅላላ ገንዘብ ወደ አንድ ሰው አካውንት የላከው የባንክ ባለሙያ

መቀመጫውን በዓለማችን ቁጥር አንድ የዲፕሎማሲ ማዕከል ኒዮርክ ያደረገው ሲቲ ባንክ ከሰሞኑ አነጋጋሪ ድርጊት ፈጽሟል፡፡

የባንኩ አንድ ደንበኛ 280 ዶላር ለመላክ በአካል መምጣቱን ተከትሎ የባንኩ አንድ ሰራተኛም አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

ይሁንና ይህ የባንክ ባለሙያ በስህተት በርካታ ዜሮ ቁጥሮችን በመንካት በጠቅላላው 81 ትሪሊዮን ዶላር ያስተላልፋል፡፡

ሂሳቡ እንዲዘዋወር መፍቀድ የነበረበት ሌላኛው የባንክ ሰራተኛም ትኩረት ሳያደርግ የመጀመሪያው ባለሙያ የሰራውን ስህተት አሳልፎታል ተብሏል፡፡

የተላለፈው ገንዘብ መጠን ገንዘቡ የደረሰው ሰው ባንድ ጊዜ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ ይሆናል የተባለ ሲሆን የኢለን መስክን ጠቅላላ ሀብት 200 ጊዜ እጥፍ ሀብት ኖረዋል ይሆናል፡፡

የገንዘብ ዝውውሩ የሚያጸድቀው ሶስተኛው እና የመጨረሻው ባለሙያ እንደ ቀልድ ሊያሳልፈው ሲል ማየቱን ተከትሎ ባንኩ ከኪሳራ መዳኑን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ይህ ባንክ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት ውስጥ 10 ጊዜ በስህተት አንድ ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ በስህተት አስተላልፎም ነበር፡፡

እንዲሁም በ2023 ደግሞ 13 ጊዜ በስህተት ገንዘብ ልኮ የነበረ ሲሆን ከአምስት ዓመት በፊት ደግሞ 900 ሚሊዮን ዶላር በስህተት ከላከ በኋላ ገንዘቡ በህግ ክርክር ከተደረገበት በኋላ ገንዘቡ ቢመለስም የባንኩ ስራ አስኪያጅ ግን ስራቸውን አጥተዋል፡፡

የሲቲ ባንክ አጠቃላይ ሀብት 150 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ሲሆን ሊልከው የነበረው ገንዘብ ግን ከዚህ በጣም ብዙ እጥፍ ነበር፡፡

[ @MadoNews ]


የሶማሊያ ጦር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን ባካሄደው ዘመቻ ከ40 በላይ የአልሸባብ ታጣቂዎች ተገደሉ

የሶማሊያ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣብያ ባሰራጨው ዘገባ ከ40 በላይ የአሸባሪው ቡዱን አልሸባብ ተዋጊዎች ስኬታማ በነበረ ኦፕሬሽን ተገድለዋል ብሏል።

የሶማሊያ ጦር የሰጠው መግለጫ ኦፖሬሽኑ እንደተካሄደ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ አጋሮቻችን ጋር በመተባበር በሂርሻቤለ ግዛት ቢያ ካዴ አከባቢ የተሳካ ዘመቻ አካሂደናል ብሏል። የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ከዓለም አቀፍ አጋሮቹና የአከባቢው ሰዎች ጋር በመሆንም ሌላ ተጨማሪ የአሸባሪው ቡዱን ክንፎችና አባላት ከአከባቢው ለማፅዳት እየሰሩ መሆኑ የሶማሊያ ጦር በኤክስ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እኤአ በ2004 በሶማሊያ የተመሰረተው አልሸባብ እኤአ ከ2010 ጀምሮ የተለያዩ የሶማሊያ ግዛቶችን መቆጣጠር የቻለ ሲሆን ከሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዶሾ ግን እኤአ በ2011 እንዲወጣ ተደርጓል። በዚህም ከዛን ጊዜ ጀምሮ አልሸባብ የሽምቅ ተዋጊ በመሆን በተለያዩ የሶማሊያ አከባቢዎች በሞቃዲሾ መንግስት ጦርና አጋሮች ላይ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶችን ሲፈፅም ቆይቷል።

አልሸባብ እኤአ ከ2012 ጀምሮ በይፋ የአልቃይዳ ክንፍ መሆኑንም ያወጀ ሲሆን በዚህም ሶማሊያ መረጋጋት የተሳናት ሰላም የራቃት ሀገር ትሆን ዘንድ የራሱን ከፍተኛ ሚና ሲወጣ ቆያቷል።

[ @MadoNews ]


በ4ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳላቸው

በ4ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ተጥሎ የነበረው እገዳ ተነሳላቸው፡፡

የሲቭል ማህበረሰብ ድርግቶች ባለስልጣን ከወራት በፊት በ4ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ላይ ጥሎት የነበረው እገዳ ከዛሬ የካቲት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተነሳ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ተናግሯል፡፡

ኢሰመኮ ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን እና ከታገዱት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በማድረግ ለጉዳዩ መፍትሔ ለማስገኘት ሢሠራ እንደቆየ አስታውሷል፡፡

ኢሰመኮ በድርጅቶቹ እገዳ ላይ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እንዳከናወነ ተናግሮ የደረሰባቸውን ግኝቶች እና ምክረ ሐሳቦች ለሚመለከታቸው አካላት አጋርቻለሁ ብሏል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ከወራት በፊት እገዳ የጣለባቸው ድርጅቶች፤ በታኅሣሥ ወር 2017 ዓ.ም. የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችን በድጋሚ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል ናቸው።

የሚከሰቱ ችግሮችን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ እና ሀገራዊ ጥቅምን በማስቀደም በመቀራረብ እና በመወያየት የመፍታት ልምዳችን ሊለመድ ይገባል ሲል ኢሰመኮ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

[ @MadoNews ]


#ሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ #ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በመግደል ተከሰሱ

የሳዑዲ አረቢያ ድንበር ጠባቂዎች እ.ኤ.አ ከ2019 እስከ 2024 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከየመን ድንበር ለመሻገር የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መግደላቸውን ዘ ጋርዲያን ያሰባሰባቸው ምስክሮች እና ከሂዩማን ራይትስ ዎች ግኝቶች አመላከተ።

በርካታ ስደተኞች በመሳሪያ በተተኮሰባቸው ጥይት እና በፈንጂዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካታ ሴቶች ደግሞ ጾታዊ ጥቃት እና አካላዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በ2022 የስደት ጉዞ ለማድረግ የሞከረው አንድ ኢትዮጵያዊ ከጎኑ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ መመልከቱን ለዘጋርዲያን ተናግሯል። "አንድ እግሬ በሳውዲ አረቢያ ጥይት ተጎድቷ" ያለው ግለሰቡ “በዙሪያዬ የተጎዱና የሞቱ ሰዎች ነበሩ” ብሏል።

ሌላኛው ስደተኛ ደግሞ በጥር 2023 ድንበር ላይ “ወደ አፈርነት እየተቀየሩ ያሉ አስከሬኖችን” ማየቱን ገልጾ አንዳንዶቹ “በእንስሳት መበላታቸውን” ገልጿል።

[ @MadoNews ]


ብሄራዊ ባንክ አዲስ ህግ አጸደቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አነስተኛና አዲስ የተቋቋሙ የፋይናንስ ድርጅቶች በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ቅርንጫፍ እንዳይሠሩ የሚያግድ ረቂቅ መመሪያ አወጣ።

ባለሙያዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ውሳኔ በባንኮች መካከል ውህደትን ለማበረታታት ሰፊ ስትራቴጂ አካል ነው

[ @MadoNews ]


"የፈጠራ ክስ ቀርቦብኛል"- ኤርትራ‼️

ተመድ እና የአውሮፓ ህብረት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ድንበር ገብተው ጥቃት እየፈፀሙ መሆናቸውን ተከትሎ ያቀረበባትን ክስ ኤርትራ አስተባበለች።

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስቴር የማነ ገ/መስቀል በx ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አውሮፓ ህብረት እና ተመድ እንደዚህ ቀደሙ ሁሉ ተመሳሳይ እና የፈጠራ ክስ በኤርትራ ላይ መስርቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በጄኔቫው ስብሰባ ላይ ኤርትራ በትግራይ ክልል ወረዳዎች ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀመች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይሁንና ኤርትራ ክሱን የፈጠራ ክስ ነው ስትል አስተባብላለች።

[ @MadoNews ]


በረከቱ ለኢትዬጲያም ይድረስ
ለሃገሪቱ ዜጎች ቤት በነፃ ሊያድል የተዘጋጀው መሪ
‼️

ቡርኪናፋሶን በሽግግር ፕሬዝዳንትነት እየመሩ የሚገኙት ወጣቱ ኢብራሂም ትራኦሬ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና ቤት ለሌላቸው ቡርኪናቤዎች ነፃ ቤቶችን መገንባት መጀመራቸውን አስታወቁ።

በ 2030 እያንዳንዱን የቡርኪናፋሶ ህዝብ የቤት ባለቤት ለማድረግ ራዕይ ተይዞ እየተሰራ ነው ብለዋል።
እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ከደመወዝ ምንም አይነት ቀረጥ አይቀነስም ብለዋል።

ኢብራሂም በሁለት አመት የስልጣን ቆይታ ብቻ ቡርኪናፋሶን ወደ ገነት እና ከድህነት የጸዳች ሀገር እያሸጋገረ ነው ሲሉ ከበርካታ መሪዎች እና ግለሰቦች አድናቆት እየተቸረው ይገኛል።
ኢብራሂም ትራዎሬ ምንም አይነት የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት የለውም

[ @MadoNews ]


የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 22 የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወሰደ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 የመጀመሪያው ሰባት ወራት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና ብልሹ አስራርን ለመቀረፍ ባከናወናቸው ተግባራት በ22 አመራርና ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል፡፡

እርምጃው የተወሰደው ከደንበኞች በቀረቡ የብልሹ አሰራርና ሙስና ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ ሲሆን፣ አስፈላጊው ማጣሪያ ተደርጎ በ22ቱም አመራር እና ሰራተኞች የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል።እርምጃ ከተወሰደባቸው አመራር እና ሰራተኞች መካከል ሶስቱ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እና 19ኙ ደመወዝ እንደተቀጡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዮኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በሰባቱ ወራት ውስጥ ከ 50 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ስርቆት እና ውድመት ተቋሙ ላይ ተፈፅሟል፡፡የተፈፀመው ስርቆትና ውድመት የኃይል ሰርቆት፣ የትራንስፎርመር ስርቆት፣ ቆጣሪ መነካካት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጉዳት፣ የመሰረተ ልማት ሰርቆት፣ የተቋሙ ሰራተኞችን ስራ እንዳይሰሩ ማወክ እና የኬብል ሰርቆትን የሚያጠቃልል ሲሆን፤ በአጠቃላይ 163 ወንጀሎች ተፈጽመው ክትትል እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

ከእነዚህ መካከል ውሳኔ ያገኙ የወንጀል ጉዳዮች 11 ሲሆኑ፤ በዚህም 13 ተከሳሾች ከሁለት ወር ቀላል እስራት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት እና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ተቀጥተዋል፡፡በተጨማሪም በሰባቱ ወራት ውስጥ የፍጆታ ክፍያ ለማይከፍሉ ለ368 ደንበኞች ማሰጠንቀቂያ በመሰጠት ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ ለድርጅቱ ገቢ ማድረግ መቻሉን አቶ መላኩ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

[ @MadoNews ]


ሶፍያ ሺባባው

[ @MadoNews ]


.......... የቀጠለ.......

እንደ አስተያየት ሰጪዋ፣ በቦታው የሚገኘው ካምፕ አራት መጋዘኖች አሉት፡፡ ሦስቱ መጋዘኖች ከተለያዩ አካባቢዎች ታፍሰው የሚመጡ ወንዶች የሚገኙበት ሲሆን አንደኛው ለሴቶች ተብሎ የተለየ ነው፡፡

‹‹መጋዘኖቹ በሰው የተጨናነቁ ናቸው፣ የምንበላው ደረቅ ዳቦ ነው፡፡ ንፅህና የሚባል የለም፣ ሽንት ቤቱም የሚገኘው እዚያው ነው፤›› የምትለው አስተያየት ሰጪዋ፣ በተላላፊ በሽታና በተለያዩ ምክንያቶች በየቀኑ የሰው ሕይወት ያልፍ እንደነበርም ተናግራለች፡፡

የፈጸመችው ምንም ዓይነት ወንጀል እንደሌለና ይህን አድርገሽ ተገኝተሻል የሚላት የሕግ ሰው ሳይኖር፣ ከተያዘች ከ15 ቀናት በኋላ መለቀቋን ተናግራለች፡፡

‹‹በካምፑ ውስጥ እያለሁ ታመምኩ፡፡ ፖሊሶችም ሕክምና ትሄጃለሽ ብለው በመኪና አውጥተው ስሙን የማላስታውሰው ጤና ጣቢያ ጥለውኝ ተመለሱ፤›› የምትለው አስተያየት ሰጪዋ፣ ‹‹ፖሊሶች ቆሎ፣ ለውዝና የመሳሰሉትን መንገድ ዳር መሸጥ አትችሉም በማለት በየጊዜው ከምንሠራበት ቦታ እየመጡ ያባርሩናል፤›› ስትልም ታክላለች፡፡

በጫማ መጥረግ ሥራ የተሰማራውና በካምፑ ሁለት ሳምንት መቆየቱን የሚናገረው ወጣት ስጦታው ካስትሮ እንደገለጸው፣ ጫማ ከሚጠርግበት ቦሌ አካባቢ ፖሊሶች ይዘውት በመኪና ጭነው ቃሊቲ ማሠልጠኛ ውኃ ልማት አካባቢ ወደሚገኘው ካምፕ መወሰዱት ተናግሯል፡፡
‹‹ካምፑ በየዕለቱ ታፍሰው በሚመጡ ሰዎች የተጨናነቀ ነው፡፡ ወንዶችን ከሚያስተናግዱት ሦስቱ መጋዘኖች በአንዱ ብቻ በርካታ ሰዎች ይገኛሉ፤›› የሚለው ወጣቱ፣ በዚህም ምክንያት ከንፅህና ጉድለት ተያይዞ በሚመጣ ተላላፊ በሽታ የሚጠቁ ሰዎች እንደነበሩ አስረድቷል፡፡

በሁለት ሳምንት የካምፕ ቆይታው በታይፎይድ መጠቃቱንና በአጎቱ አማካይነት ሊለቀቅ መቻሉንም ስጦታው ተናግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ‹‹በጎዳና ላይ ያሉ ሰዎችን ያለ ፈቃዳቸው መያዝና ወደ ማቆያ ማዕከላት ማስገባት፣ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን ስለሚያስከትል ሊቆም ይገባል፤›› የሚል መግለጫ ከአንድ ወር በፊት አውጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ኢሰመኮ በመግለጫው፣ ‹‹በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ‹‹ቃሊቲ አካባቢ›› ተብሎ በሚጠራው የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ አካባቢ ባለ ሰፊ መጋዘን ውስጥ ከጎዳና ላይ የተነሱ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንና ይህ ሰዎችን የመያዝና ወደ ማቆያ ማዕከል/ቦታ የማስገባት ድርጊት አሁንም እንደቀጠለ ነው፤›› ማለቱ አይዘነጋም፡፡

‹‹ውሎና አዳራቸውን በጎዳና ላይ ያደረጉ ሰዎችን በግዳጅ ወደ ማቆያ ማዕከል (ቦታ) አስገብቶ መያዝ ወይም ያለ ፈቃዳቸው ወደ ተለያዩ አካባቢዎች መውሰድ/እንዲሄዱ ማስገደድ፣ የነፃነት መብትና ከቦታ ቦታ በነፃነት የመንቀሳቀስን ጨምሮ፣ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ስለሚያስከትል በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል፤›› ሲልም አሳስቦ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ፣ ‹‹በአዲስ አበባ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ወጣቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች እየታፈኑ የት እንደገቡ ሳይታወቅ መሰወራቸውን፣ ከቤተሰቦቻቸውና ከተለያዩ አካላት መገንዘብ ችለናል፤›› ሲል አስታውቆ ነበር፡፡

‹‹ይህን የመንግሥት ተግባር ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው ታፍነው የተወሰዱ ወጣቶች የት እንደሚገኙ አለመታወቅና ቤተሰቦቻቸውም በመንግሥት አካል የተያዘ ግለሰብ ሊገኙባቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ቦታዎች ቢያስሱም ማግኘት አለመቻላቸው ነው፡፡ በተጨማሪም አንዳንዶቹ ከተወሰኑ ቀናት መሰወር በኋላ በድንገት የት እንደነበሩ እንኳ መናገር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ናቸው፤›› በማለት ኢዜማ መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ካልሆነ በስተቀር ፖሊስ በዘፈቀደ ከመንገድ ዳር አፍሶ የሚያስረው ሰው የለም ብለዋል፡፡

‹‹በወንጀል የሚጠረጠር ሰው ካለ ሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን ነው የሚደረገው፤›› ያሉት ምክትል ኮማንደሩ፣ በመንግሥት የተቋቋመ ካምፕ መኖሩንና ሰዎችም ታፍሰው ወደዚያ ይወሰዳሉ የሚባለው ከእውነት የራቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

[ @MadoNews ]


📌ከሥራ ቦታቸው ታፍሰውና ለሁለት ሳምንታት ታስረው የተለቀቁ ግለሰቦች ስለቆይታቸው ተናገሩ

📌‹‹በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ካልሆነ በስተቀር ፖሊስ በዘፈቀደ ከመንገድ ዳር አፍሶ አያስርም››
- አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን


ከሥራ ቦታቸው ታፍሰው አዲስ አበባ ቃልቲ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ አካባቢ ውኃ ልማት ጀርባ በሚገኘው ካምፕ ለአሥራ አምስት ቀናት ያህል ቆይተው መለቀቃቸውን፣ ከካምፑ የወጡ ግለሰቦች ተናገሩ፡፡ በወንጀል የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን ካልሆነ በስተቀር ፖሊስ ከመንገድ ዳር አፍሶ እንደማያስር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምላሽ ሰጥቷል፡፡

በለውዝ ንግድ የምትተዳደረውና ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አስተያየት ሰጪ ለሪፖርተር እንደተናገረችው፣ ለውዝ ከምትነግድበት ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም. ከቀኑ አምስት ሰዓት ፖሊሶች በፓትሮል መኪና ጭነው እንደወሰዷት ተናግራለች፡፡

‹‹የምሸጠውን ለውዝ እንደያዝኩ ፖሊሶች በመኪና ጭነው አዲስ እየተገነባ በሚገኘው ‹አደይ አበባ› ስቴዲየም አካባቢ ወዳለው ፖሊስ ጣቢያ ይዘውኝ ሄዱ፤›› የምትለው አስተያየት ሰጪዋ፣ ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው በሚታሰሩበት በዚሁ ፖሊስ ጣቢያ ለሦስት ቀናት ማደሯን ተናግራለች፡፡

ከሦስት ቀናት የፖሊስ ጣቢያ ቆይታ በኋላ ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ከሌሎች እንደ እሷ ከመንገድ ከታፈሱ ወንዶችና ሴቶች ጋር በመሆን በአውቶቡስ ተጭነው፣ ቃሊቲ የአሽከርካሪዎች ማሠልጠኛ አካባቢ ወደሚገኘው ካምፕ መወሰዳቸውን ገልጻለች፡፡..........................

[ @MadoNews ]


የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል በ #ዳሎል እና #ኮናባ ወረዳ አካባቢ ከለሊቱ 10:00 ጀምሮ ከ ዘጠኝ ጊዜ በላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።

ይህ መሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.3 የተለካ ሲሆን ብዙ ቤቶችን አፍርሷል ብለዋል።
ህብረተሰቡ ተደናግጦ እቃውን አውጥቶ ውጭ ላይ ለመዋል እና ለማደር ተገዷል ብለዋል።

[ @MadoNews ]


ተመድና የአውሮፓ ኅብረት የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ድንበር ለቀው እንዲወጡ አሳሰቡ

የአውሮፓ ኅብረት በጉባዔው ላይ ባቀረበው መግለጫ፣ ሳይወጡ የቀሩ የኤርትራ ወታደሮች ከድንበሩ ለቀው እንዲወጡ፣ ተፈጽመዋል በተባሉ የመብት ጥሰቶች ላይ ተዓማኒና ገለልተኛ አካል ሙሉ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት በሰብዓዊ መብትና በዓለም አቀፍ ሰብዓዊ አገልግሎቶች ላይ ተፈጽመዋል ባላቸው ጥሰቶች ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያንና ጥገኝነት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የሸሹ ኤርትራውያን፣ ፍትሕ ማግኘት አለባቸው ሲል አሳስቧል፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ለጉባዔው ባቀረበው መግለጫ፣ በኤርትራ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያሳስበኛል ብሏል፡፡

በተመሳሳይ በዚሁ መድረክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ባቀረበው መግለጫ፣ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የቆመበትን የፕሪቶሪያ ስምምነት እየጣሱ መሆናቸውን ጠቅሶ ከአካባቢው እንዲወጡ ሲል አሳስቧል፡፡

‹‹የዋና ኮሚሽነሩ ቢሮ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ግልጽ የሆነ ጥቃት፣ ጠለፋ፣ አስገድዶ መድፈር፣ የንብረት ዘረፋና የዘፈቀደ እስራት እየፈጸሙ መሆናቸውን ተዓማኒ የሆነ መረጃ አለው፤›› ብሏል፡፡ በመሆኑም የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ ክልል ለቀው እንዲወጡ በማለት ጥሪ አቅርቧል፡፡

ተመድ በመግለጫው በሁለቱ አገሮች መካከል ሰላም ከወረደ በኋላ፣ የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ባደረገው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተሠልፈው ሲዋጉ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጰያና በኤርትራ መንግሥታት መካከል በተለያየ መንገድ የሚገለጹ የፖለቲካ ትኩሳቶች እየተስተዋሉ ነው፡፡

[ @MadoNews ]


እንጀራ ለማግኘት ጾታውን የካደው!!

ለ6 ዓመታት ሴት በመምሰል በተለያዩ ሆቴሎች ሰራተኛ በመሆን ሲያገለግል የነበረ ሲሆን በማህበረሰቡ ዉስጥ ጥርጣሬን ስለፈጠረ በቁጥጥር ስር ዉሎ ፆታዉ ሴት ሳይሆን ወንድ መሆኑ ታውቋል።

[ @MadoNews ]


ልጆቼ ይቅርታ!

ለልጆቼ የማወርሰው የለኝም፣ የምኖረው በቤት ኪራይ ነው የምሰራው የመንግስት መስሪያ ቤት በሹፌርነት ነው!

ለበርካታ ዓመታት ያጠራቀምኳትን የልጆቼን ውርስ ለመቄዶንያ ለመስጠት ነው የመጣውት!

አካውንቴ ላይ 107ሺህ ብር አለ ያሉት አቶ አብርሃም 100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎልናል!

አቶ አብርሃም ልጆቼ ይቅርታ የማወርሳችሁ ገንዘብ አይደለም
ለእናንተ የሚጠቅማችሁ መቄዶንያን ባወርሳችሁ ነው ብለዋል!

[ @MadoNews ]

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.