ምዕራፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 14 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር
ሙሽሪኮች የአላህን (ሱ.ወ)አንድነት ይቀበሉ ነበር። በዛት (በአካሉ)፣በሲፋቱ (በባህሪያቱ)እና በድርጊቶቹ አንድነቱን ይቀበሉ ነበር።አላሁ ተዓላ ፈጣሪ መሆኑን ሰማያትንና ምድርን፣በመካከላቸውም ያለውን ነገርና ሁሉንም ነገር የፈጠረ መሆኑን ያውቁና ይቀበሉት ነበር።የሁሉም ነገር ባለቤት መሆኑን፣የሰማያትና የምድር እንድሁም በመካከላቸው ያለውን ነገርም ሆነ የሁሉም ነገር ሥልጣን በእጁ መሆኑን፣ሰውን፣እንስሳትንና ሌሎች ሕይወት ያላቸውን ነገሮች በሙሉ የሚረዝቅ ፣ነገሩን ሁሉ ከሰማይ ወደ ምድር የሚያዘጋጅ፣የትንሹንም ሆነ የትልቁን ነገር የብናኙንም ሆነ የጉንዳኑን ጉዳይ ሁሉ የሚያስተናብር፣ የሰማያትና የምድር፣ በመሀከላቸውም ያለው ነገር፣ የታላቁ አርሽና የሁሉም ነገር ጌታ መሆኑን፣ፀሀዩን ጨረቃውን ከዋክብቱን፣ዛፉን፣እንስሳቱን፣ጂኑን፣ሰውንና መላእክቱን፣ ሁሉ ያገራና ሁሉም ለሱ የሚተናነሱና የሚዋረዱ መሆኑን፣ የፈለገውን በፈለገው ላይ አሸናፊ የሚያደርግና በሱ ላይ ማንንም ምንንም በፍፁም አሸናፊ ማድረግ የማይቻል መሆኑን፣የሚያኖርና የሚገድል፣የፈለገውን የሚያደርግና የፈለገውን የሚፈርድ፣ለፍርዱም ተቺ የሌለውና ውሳኔው የማይመለስበት መሆኑን ይቀበሉ ነበር።
በዚህ መልኩ የአላህን አንድነት -በዛቱ፣በሲፋቱና በድርጊቱ-አንድነቱን በግልፅ ከተቀበሉ በኋላ እንድህ ይሉ ነበር፦አላህ ከባሮቹ እንደ ነቢያት፣ሩሱሎች፣ወልዮችና ሷሊሆች ባለሟሎች ስለ ፍጡሮቹ ጉዳይ የመፈፀም ከፊል ሥልጣን ይሠጣቸዋል። ልጅን መስጠት፣መከራን የመመለስ፣ጉዳዮችን የመፈፀም፣በሽተኛን የማዳንና የመሳሰሉትን ችሎታዎች በአላህ በአላህ ይሠጣሉ ። አላህ ይህን ሥልጣን የሰጣቸው ለሱ ቅርበት ስላላቸውና በሱ ዘንድ ስለተከበሩነው። አላህ ይህንን ስልጣንና ምርጫ ስለሰጣቸው ለሰው በማይታይና በማይታወቅ መንገድ(በገይብ)የባሮችን ጉዳዮች ይፈፅማሉ፣ጭንቅና መከራን ያነሱላችኋል፣የወደዱትን ሰው ወደ አላህ ያቃርባሉ፣ በአላህ ዘንድ ያማልዳሉ።ይሉ ነበር።
ሙዝሪኮች በዚህ አባባላቸው መሠረት እነዚህን ነቢያት፣ወሊዮችና ሷሊሆች ወደ አሏህ መቃረቢያ (ወሲላ) አደረጉዋቸው (ሙሽሪኮችንና አላህን የሚያቃርቡ ማለትነው።)ወደነዚህም የሚቀርቡበትንና ውደታቸውን የሚያገኙበትን ድርጊቶችንና ተግባራትን ፈጠሩ።እነዚህን ድርጊቶች ከፈፀሙ በኋላ ይተናነሱላቸዋል፣ጉዳዮቻቸውንም እንድፈፅሙላቸው ይለምኑዋቸዋል፣በመከራ ጊዜ እርዳታን ይጠይቁዋቸዋል፣በፍራቻ ጊዜም ይጠበቁባቸዋል(ጠብቁን) ይሉዋቸዋል።
ወደነዚህ ለመቃረብ የፈጠሩት ድርጊቶች ለነዚህ ነቢያት (አንቢያ) ወሊዮች፣(አውሊያ)እና ሷሊሆች (ሷሊሁን) የተወሰነ ቦታ ይመርጡላቸውና ቤቶችን ይገነለመቃረብና ከዚያም በቤቶቹ ውስጥ ምስሎቻቸውን ሰርተው ያስቀምጣሉ። የሚቀርፁት ምስሎች የነቢያቶቹና የወሊዮቹ ትክክለኛ ምስሎች ወይም ሀሳባው ምስሎችናቸው። በነሱ አባባል የአንዳንዶቹን ወልዮችና ሳሊሆች መቃብሮች ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ከሆነ ግን ምስሎቻቸውን ሳይቀርፁላቸው ቤት ብቻ ይገነቡላቸዋል። ከዚያም ወደነዚህ ምስሎችና መቃብሮች በመሄድ በረከት(ረድኤት)ለማግኘት መቃብሮቹንና ምስሎቹን ያብሱዋቸዋል። ይዞሯቸዋል (ጠዋፍ)ያደርጉባቸዋል፣ያልቋቸዋል፣ያከብሯቸዋል፣ያወድሷቸዋል፣ወደነሱ ለመቃረብና ችሮታቸውን ለማግኘት ሲሉ ስለቶችንና ቁርባኖችን ያቀርቡላቸዋል። እነዚህ ሙሽሪኮች ለነዚህ ነገሮች የሚሳሉት አላህ ከሰጣቸው ሲሳዮች(ርዝቆች) ከእርሻው፣ከአትክልቱ፣ከእህሉ፣ከመጠጡ፣ከእንስሳቱ፣ከወርቁ፣ከብሩ፣ከእቃዎችና ከገንዘቦችነው። ይህን ሁሉ የሰጣቸው አላህ ሲሆን ለሌላ ስለት ወይም ነዝር ያደርጋሉ።
ይቀጥላል
https://t.me/Menhaj_Asselefiya