ምዕሬፍ 3 የደዕዋ ግልፅ መውጣት
ክፍል 15 የተውሂድ ጉዳይ አብይ የመወያያ ርዕስና የልዩነት መሠረት ነበር
የእርሻውን ውጤት አትክልቱንም፣እህሉንም፣መጠጡንም ወርቁንም ብሩንም ፣እቃውንም፣ገንዘቡንም ወደ እነዚህ የሷሊሆች ቦታዎች፣መቃብሮችና ምስሎች የሚያቀርቡት በመቃብሮቹና ቦታዎቹ አካባቢ ቸጎራብተው በሚኖሩ ሰዎች አማካኝነት ነው።በአብዛኛው ጊዜ በነሱ አማካኝነትና አገናኝነት (ዋሲጣ)ካልሆነ በስተቀር አይቀርብም።
እንስሳቶችን ግን ለነዚህ ሷሊሆች የሚያቀርቡበት ሌላም ወደ አላቸው። በነዚህ ባለ መቃብሮች ና ምስሎች ሷሊሆች ስም እንስሳዋን ይለቋታል፦ ወደነሱ ለመቃረብና ለመወደድ።ይቺን የተለቀቀችውን እንስሳ ያከብሯታል፣በፍፁም በክፉ አይነኳትም፣የፈለገችውን ትበላለች፣ወደ ፈለገችው ቦታ ትዘዋወራለች። በመጨረሻም በነዚህ ወልዮች መቃብሮችና ለነሱ በተለዩ ቦታዎች ላይ ያርዷታል።ወይም ደግሞ በሌላም ቦታ ሊያርዷት ይችላሉ ነገርግን በሚያርዷት ጊዜ በአላህ (ﷻ)ስም ፋንታ የነዚያን ወልዮቾና ሷሊሆች ስሞች ይጠራሉ።
ከሚያደርጉት ስራዎች አንዱ በነዚህ ወልዮችና ሷሊሆች ምክንያት በገነት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ በአላትን ማዘጋጀት ነበር። ሰዎች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደነዚህ መቃብሮችና ለነሱ ወደተለዩት ቦታዎችበመሄድና በተለየ ቀናት በመሠብሠብ በአላትን ያከብራሉ። ከላይ በጠቀስነው መሠረት ለበረካ በማለት መቃብሮቹንና ቦታዎቹን ያብሳሉ፣ይዞራሉ፣ስለቶችንና ቁርባኖችን ያቀርባሉ። ልክ እንደ ሀጅ የቅርቡም ሆነ የሩቁ፣ሀብታሙም ሆነ ደሀውም ይገኙበታል። ስለቶቻቸውን አቅርበው የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት ሲሉ ሁሊም ይጎርፉበታል።
ሙሽሪኮች ለነዚህ አውሊያ እና ሷሊሂን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ወደነሱ በመቅረብና በመወደድ ከአላህ ጋር እንድያቃርቧቸውና በበላህና በነሱ መሀል አገናኞች እንድሆኑላቸው ነው። ወደ አላህ ያቀርባሉ በአላህ ዘንድም ያማልዳሉ ብለው ያምናሉ። በራሳቸውም ሆነ በማማለድ የተነገራቸውን ነግር ሰምተው ለተጠየቁት ነገረ መልስ መስጠት፣ጉዳዮችን መፈፀምና ጭንቅንም ማስወገድ ይችላሉ ብለው ያምኑ ስለነበር ጉዳዮቻቸውን (ሃጃዎቻቸውን) እንድፈፅሙላቸውና ጭንቅ እንድያስወግዱላቸው ይጠሯቸው ነበር።
ይህነበር በአላህ ማጋራቸው፣ከአላህ ሌላ መገዛታቸው፣ከአላህ ሌላ አምላክን መያዛቸውና ለአላህ ሸሪኮችን ማድረጋቸው።እነዚህ ወልዮች (አውሊያዕ)፣ሷሊሆች (ሳሊሁ ን) እና የመሳሰሉትን የሙሽሪኮቹ አምላኮች ነበሩ።
ይቀጥላል.............
https://t.me/Menhaj_Asselefiya