Postlar filtri


አንዳንዴ እኮ አንዳንድ ጊዜ ሐጃዎችንን፣ ችግሮቻችንን፣ ድካሞቻችንን፣ ህመሞቻችንን ... ሌላው ቀርቶ ደስታዎቻችን ጭምር የማንናገርበት ጊዜ አለ።

ወዳጆቻችን ሆይ ደብቀን ወይም ለናንተ ቦታ አጥተን ሳይሆን እናንተኑ ላለማስቸገር ብለን ነው። እንዴት ሳይነግረን፣ እንዴት ሳንሰማ፣ እንዴት ሳይጠራን፣ እንዴት ሳናውቅ ... ብላችሁ ብትወቅሱ በርግጥ እውነት አላችሁ ። በዚያው ግን መልካም ጠርጥሩ።

ዱንያ የብዙዎችን ዐቅል ይዛለች። ብዙዎችን በውክቢያ ዓለም ውስጥ ከታለች። ለሐዘኑም፣ ለሰርጉም፣ ለዐቂቃውም፣ ለምርቃቱም፣ ለማግባቱም፣ ለህመሙም፣ ለችግሩም ... ሰውን ማስቸገር ደግም አይደል የሚል ሀሳብ አለን።

በረካ ሁኑልን።

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ሙእሚን በሌሎች ወንድሞቹ ላይ ተስፋን ለማስረጽና ደስታን ለማድረስ ፈገግ ሲል ምንዳ እንደሚያገኘው ሁሉ፤

ፈገግታ ከፊቱ ጠፍቶ የከፋው ቀን፣
በብሶት እንባው በፈሰሰበት አጋጣሚም፣
ባይተዋርነትና ብቸኝነት በተሰማው ቀንም፣
ሀሳብና ጭንቀት ያገኘው እንደሆነም፣
ሐዘን የወረሰው ጊዜም፣
ችግርና መከራ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ አጅር ያገኛል።
አጥፍቶ ሲፀፀት ጭምር እንዲሁ አጅር ያገኛል።
ባላችሁበት ሁኔታ ደስተኛ ያልሆናችሁ ሁሉ፤
ትንሽ ትልቁን ጉዳያችሁን ሁሉ ወደ አላህ አስጠጉ።
አትድከሙ፣ አትስነፉ፣ አትታክቱ፣ አትዘኑ። አብሽሩ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish




Nejashi Printing Press dan repost
መፃሕፍትን እቤትዎ ወይም ሥራ ቦታዎ ድረስ እናምጣልዎ
***

ፕሌይ ስቶርን በማውረድ ወደ Nejashi Bookstore  ወይም በዌብሳይታችን WWW.NEJASHIBOOKS.COM በመግባት
የመፃሕፍት ዝርዝሮች በማየት የፈለጉትን መጽሐፍ ይምረጡ። ዋጋው እዚያው አለላችሁ ።

ከዚያም ወደ 0945858585 በመደወል የመረጡትን መጽሐፍ ይዘዙ።
ለአዲስ አበባ ደንበኞች
የትራንስፖርት 50 ብር ብቻ ይከፍላሉ ።

ወደ ክልሎች በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

https://t.me/NejashiPP




ምን ይዠ ልሂድ፣ ልኑር፣ ልግባ፣ ልውጣ .... አትበሉ።
አትፍሩ፣
አታስቡ፣
አትጨነቁ፣
ኢስቲግፋራችሁን በደንብ ያዙ።
ሁሉም ነገር ይገራላችኋል።

አዎ ሁሉም ነገር ...

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሁሉም ሰው ያሳዝነኛል ።
አዎ ሁሉም ።
ለምንድነው ግን???

መሳአል ኸይር


https://t.me/MuhammedSeidAbx




ቁምነገሩ ጉዞን አብሮ መጀመር አይደለም ። ማን ሳይሠለች፣ ሳይቀየር አብሮን ይቀጥላል ይጨርሳል የሚለው ነው።


https://t.me/MuhammedSeidAbx




ጁምዓ ነው።

በዱዓችሁ ውስጥ አሰቡን።

https://t.me/MuhammedSeidAbx


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ዝም አትበሉ።

ለራሣችሁ ዱዓ አድርጉ።
ዱዓ ብዙ መልካም ነገርን ያስገኛል ።
ብዙ መከራንም ይመልሳል ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሰዎችን ከሚገባው በላይ አትንከባከቡ። አትክልትም ውሃ ሲበዛበት ይሞታል ።


https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሙሐመድ ሆይ!
ስለርሱ ብለህ ያደረግከውንና የምታደርገውን ሁሉ አላህ ያውቃል፣
ለርሱ ብለህ ያሰብከውን አላህ ያውቃል፣
ለርሱ ብዬ አደርጋለሁ ብለህ ሞክረህ ያልተሳካልህንም አላህ ያውቃል፣
የርሱን ምንዳ አስበህ የታገስከውንም አላህ ያውቃል፣
ህመምህን፣ ሀሳብህን ጭንቀትህን ሁሉ አላህ ያውቃል፡፡

አላህ ሁሉ ነገርህንና ሁሉ ሁኔታህን እስካወቀ ድረስ ምን አስጨነቀህ ወዳጄዋ፡፡

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


ሰሞኑን አንድ ሰው ድሆችን ምግብ አብላልኝ ብሎ በሠጠኝ ገንዘብ ድሆችን አበላን፡፡ ኦሪጅናል ደስታ ፊታቸው ላይ አየን፣ የሞቀ ምርቃታቸውንም ተቀበልን፡፡

ወዳጆቼ!
ብዙ ቦታ ላይ የዕለት ጉርስ ከብዷል፤ ሰዎች በይፋም ሆነ በድብቅ ልመና ጀምረዋል፡፡ የተረፋቸውን ሀብታሞች ለተትረፈረፈ ድግሰ ከምትጠሩ ድሆችን ሰብስባች ምግብ አብሉ፡፡ የተራቡትን መግቡ፡፡ ጉዳዩ በዋናነት የሚመለከተው እነርሱን ነውና፡፡ ትልቁን በረከት የምታገኙት በነርሱ በኩል ነውና፡፡
የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ. እንዲህ ብለዋል፡-
“ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አብዙ፣ ምግብ መግቡ፣ ሰዎች በሚተኙበት የሌሊት ሰዓታት ተነስታችሁ ስገዱ፣ ጀነትን በሰላም ትገባላችሁ፡፡”

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx


በረሕመቱ አነጋን፣ እሱ እንደሻው አደርን፣ እሱ እንደፈቀደው ሌሊቱን አለፍን፡፡

ሰው እንዴት አደራችሁ ይላል፡፡ እንዴት እንዳደረ ባለቤቱ ያውቃል፡፡

በቤተሰቡ፣ በልጆቹና በሚወዳቸው ሁሉ መካከል ሰላም ጤና ያደረ አላህን አብዝቶ ያመስግን፡፡

ሰው የጎደለ ሚዛኑ ይሞላለት፣ የነበረ ትሩፋቱ ይቀጥልለት፣ የያዘው ኸይሩ ይጨመርለት፣ የነካው ነገር በረከቱ ይበዛለት ዘንድ አልሐምዱ ሊላህ ይበል፡፡

እንዴት አደራችሁ ወዶቼ፣
ጉድ ሞርኒንግ!
ሶባሐልኸይር፡፡


https://t.me/MuhammedSeidAbx


ፈተና ካልተማራችሁትም ሊወጣ ይችላልና በደንብ ተዘጋጁ።" አለን አስተማሪያችን ።

ዱንያ እንደዚህ ናት። አንዳንዴ በማታውቀው በኩል ትመጣብሃለች።

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.