ሙሽሮች በጌታ ደስ ይበላችሁ | ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ
ሙሽሮች በጌታ ደስ ይበላችሁ
ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ /2/
የበረከት አምላክ ይግባ ከቤታችሁ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፍቅርን ያላብሳችሁ /2/
ለሰው ኹሉ ይታወቅ ይገለጥ ሥራችሁ
ለአምላክ ክብር ይኹን ይባረክ ሰርጋችሁ
በጸሎት በምልጃ ከምስጋና ጋራ
ለእግዚአብሔር አስታውቁ ኹሉን ያውቃልና
አዝ =======
የእግዚአብሔር ሰላም እንዲበዛላቸው
በእውነት ይታነፅ የትዳር ኑሮዋቸው
ጽድቅ ይሞላበታል ፍጹም ንጽህና
የፍቅር ባለቤት ክርስቶስ ነውና
አዝ =======
መልካም ዜና ኾኖ በዓለም ይነገራል
በደስታ በሐሤት በመንፈስ ይፀራል
ሀሌ ሉያ ለእርሱ ዘላለም ምስጋና
የአርያም ዝማሬ ይገበዋልና
አዝ =======
እምነት ተስፋ ፍቅር ሦስቱም ይኖራሉ
ከኹሉ በሚበልጥ በፍቅር ይጸናሉ
አንድነት የሰጠን አንድ አምላክ ነውና
ጌታን እንልበሰው ፍቅር እርሱ ነውና
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ሙሽሮች በጌታ ደስ ይበላችሁ
ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ /2/
የበረከት አምላክ ይግባ ከቤታችሁ
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፍቅርን ያላብሳችሁ /2/
ለሰው ኹሉ ይታወቅ ይገለጥ ሥራችሁ
ለአምላክ ክብር ይኹን ይባረክ ሰርጋችሁ
በጸሎት በምልጃ ከምስጋና ጋራ
ለእግዚአብሔር አስታውቁ ኹሉን ያውቃልና
አዝ =======
የእግዚአብሔር ሰላም እንዲበዛላቸው
በእውነት ይታነፅ የትዳር ኑሮዋቸው
ጽድቅ ይሞላበታል ፍጹም ንጽህና
የፍቅር ባለቤት ክርስቶስ ነውና
አዝ =======
መልካም ዜና ኾኖ በዓለም ይነገራል
በደስታ በሐሤት በመንፈስ ይፀራል
ሀሌ ሉያ ለእርሱ ዘላለም ምስጋና
የአርያም ዝማሬ ይገበዋልና
አዝ =======
እምነት ተስፋ ፍቅር ሦስቱም ይኖራሉ
ከኹሉ በሚበልጥ በፍቅር ይጸናሉ
አንድነት የሰጠን አንድ አምላክ ነውና
ጌታን እንልበሰው ፍቅር እርሱ ነውና
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All