ለዚህም መልስ አለው | ዘማሪ ዲያቆን ናትናኤል ሳሙኤል
ለዚህም መልስ አለው
እግዚአብሔር መልስ አለው
ለተዘጋበት ሰው እግዚአብሔር በር አለው
ለልቤ ጥያቄ ውስጤን ላስጨነቀው
ይዘገያል እንጂ እግዚአብሔር መልስ አለው
ከዚህ የበለጠ ፈተና አይቻለሁ
እግዚአብሔርን ይዤ ተሻግሬዋለሁ
አልቀሰቅሰውም ልጠፋ ነው ብዬ
ወጀቡን ያዘዋል ማዕበሉን ጌታዬ/2/
እንኳን ከመከራ ያስመልጣል ከሞት
ካሳ ሆድ ሸሽጎ ያተርፋል ከመዓት
ይታመናል እርሱ ይታመናል ጌታ
እምነቴን ሊያየው ነው ማብዛቱ ዝምታ/2/
አዲስ እየሆነ ቢከብድም ለጊዜው
ካሳለፍኩት ችግር አይበልጥም ይሄኛው
እጠይቀዋለው ደግሞ እንደትላንቱ
ትቶኛል አልልም አውጥቶኝ ከስንቱ/2/
ተጨነኩኝ እንጂ መስሎኝ የማላልፈው
የዛሬው ለቅሶዬ ነገ ዝማሬዬ ነው
የማያልቀው ተስፋ ይመጣል አይቀርም
በጌታዬ ስራ አላጉረመረምም/2/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ለዚህም መልስ አለው
እግዚአብሔር መልስ አለው
ለተዘጋበት ሰው እግዚአብሔር በር አለው
ለልቤ ጥያቄ ውስጤን ላስጨነቀው
ይዘገያል እንጂ እግዚአብሔር መልስ አለው
አዝ
ከዚህ የበለጠ ፈተና አይቻለሁ
እግዚአብሔርን ይዤ ተሻግሬዋለሁ
አልቀሰቅሰውም ልጠፋ ነው ብዬ
ወጀቡን ያዘዋል ማዕበሉን ጌታዬ/2/
አዝ
እንኳን ከመከራ ያስመልጣል ከሞት
ካሳ ሆድ ሸሽጎ ያተርፋል ከመዓት
ይታመናል እርሱ ይታመናል ጌታ
እምነቴን ሊያየው ነው ማብዛቱ ዝምታ/2/
አዝ
አዲስ እየሆነ ቢከብድም ለጊዜው
ካሳለፍኩት ችግር አይበልጥም ይሄኛው
እጠይቀዋለው ደግሞ እንደትላንቱ
ትቶኛል አልልም አውጥቶኝ ከስንቱ/2/
አዝ
ተጨነኩኝ እንጂ መስሎኝ የማላልፈው
የዛሬው ለቅሶዬ ነገ ዝማሬዬ ነው
የማያልቀው ተስፋ ይመጣል አይቀርም
በጌታዬ ስራ አላጉረመረምም/2/
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All