ስሜን በደም ጻፍከው | ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
ስሜን በደም ጻፍከው በህይወት መዝገብ
ከመፍጠርህ ልቋል የማዳንህ ጥበብ
ህመምህ ህመሜ ቁስልህ ቁስሌ ነበር
በእኔ መቃብር ውስጥ ሦስት ቀን ባታድር /2/
ሕይወቴን በዋዛ በከንቱ ስጥላት
በእኔ ላይ ሰልጥኖ እርግማንና ሞት
ሕይወቴን ልትመልስ ሕይወትህን ሰጥተህ
ከሞት ልታድነኝ ሞቴን አንተ ወስደህ
ሕዝብህን በጉዞ በፍቅር የተከተልክ
አለቱ አንተ ነህ በቃዴስ የነበርክ
ሌንጊኖስ ቢመታህ የጎንህን አለት
የፈሰሰው ውሃ አረካኝ ከጥማት
መውደቅህ አቆመኝ ተወግዶ ነውሬ
መስቀል ስትሸከም ወደቀ ቀንበሬ
በመገረፍ ቁስል ከቁስል ፈወስከኝ
እጅ እግርህ ሲታሰር ከእስር ተፈታሁኝ
መናቅህ ክብሬ ነው የሆነልኝ ለኔ
ይህንን መስክሬ አያቆም ልሳኔ
ከወንበዴዎቹ ጋር አብረህ ስትቆጠር
ለኔ በአፌ ሞላህ ውዳሴና መዝሙር
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All
ስሜን በደም ጻፍከው በህይወት መዝገብ
ከመፍጠርህ ልቋል የማዳንህ ጥበብ
ህመምህ ህመሜ ቁስልህ ቁስሌ ነበር
በእኔ መቃብር ውስጥ ሦስት ቀን ባታድር /2/
አዝ
ሕይወቴን በዋዛ በከንቱ ስጥላት
በእኔ ላይ ሰልጥኖ እርግማንና ሞት
ሕይወቴን ልትመልስ ሕይወትህን ሰጥተህ
ከሞት ልታድነኝ ሞቴን አንተ ወስደህ
አዝ
ሕዝብህን በጉዞ በፍቅር የተከተልክ
አለቱ አንተ ነህ በቃዴስ የነበርክ
ሌንጊኖስ ቢመታህ የጎንህን አለት
የፈሰሰው ውሃ አረካኝ ከጥማት
አዝ
መውደቅህ አቆመኝ ተወግዶ ነውሬ
መስቀል ስትሸከም ወደቀ ቀንበሬ
በመገረፍ ቁስል ከቁስል ፈወስከኝ
እጅ እግርህ ሲታሰር ከእስር ተፈታሁኝ
አዝ
መናቅህ ክብሬ ነው የሆነልኝ ለኔ
ይህንን መስክሬ አያቆም ልሳኔ
ከወንበዴዎቹ ጋር አብረህ ስትቆጠር
ለኔ በአፌ ሞላህ ውዳሴና መዝሙር
@Orthodox_Mezmur_For_All
@Orthodox_Mezmur_For_All