❤ቅዱስ ሩፋኤል🌹
✳ትርጉሙ እንዲህ ነው ፣ በልሳነ ዕብራይስጥ ሩፋ ማለት ጤና ፣ ፈውስ ፣ መድሃኒት ሲሆን ኤል ማለት ደሞ አምላክ ፣ እግዚአብሔር ማለትነው።
♨አምጻኤ ዓለማት እግዚአ መላዕክት እግዚአብሔር በነገደ መላዕክት አለቆች ይኾኑ ሰብዓቱን ሹሟል ። ቅዱስ ሩፋኤልን ከሊቃነ ነገደ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል በመቀጠል በማዕርግ ሶስተኛ ኾኖ የተሾመው ሊቀመላዕክት ነው ፣ ዮሃንስ ወንጌላዊ ቀደም ብሎ ተናግረዋል እንዲህ ይላል ርኢኩ ሰብዓተ መላዕክተ እለ ይቀውሙ ቅድመ እግዚአብሔር ራእ 8:21 ቅዱስ ሩፋኤል የሴቶችን ማህጸን ይፈታ ዘንድ ሥልጣን ተሰጥቶታል ። መላኩ ሩፋኤል በ 23 ነገደ መላዕክት መናብርት ተብለው የሚጠሩት የተሾመው ብርሃናዊ መላክ ነው ። የነገድ ስማቸውን እንዲህ ነው ፣ አጋእዝት ፣ ሓይላት ፣ ሥልጣናት ፣ ሊቃናትና መናብርት ፣ መኳንንትና አርባብና ፣ ኪሩቤልና ሱራፌል አዕላፍም ፣ ድርገታትም ተብለው ይታወቃሉ ። አለቆቻቸውም ዓስር ናቸው ። እሊኽም ፣ ቅዱስ ሚካኤል ፣ ቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ሩፋኤል ፣ ቅዱስ ፋኑኤል ፣ ቅዱስ ራጉኤል ፣ ቅዱስ ኡራኤል ፣ ቅዱስ ሱርያል ፣ ቅዱስ ሰዳክያል ፣ ቅዱስ ሰላትያል ፣ ቅዱስ አናንኤል ናቸው ። እሊኽ ነገደ መላዕክትም ለዘለዓለም በሰማያት ሕያዋን ኹነው ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር ወሰናቸው ። ነገር ግን እግዚአብሔር ግን በጠራቸው ግዜ ፈቃዱን ለመፈጸም እሊኽ መላዕክት እስከ ጽርሃ አርያም ይወጣሉ ። በላካችውም ግዜ የፍጥረተ ሁሉ ወሰን እስከኾነችው ጨላማይቱ የባርባሮስ ሥፍራ ድረስ ይወርዳሉ ። ተመልሰውም ብቻውን የነበረው ያለና የሚኖር በአገዛዝ ላይም ሁሉ ሥልጣን ያለው እርሱን ከማመስገን በቀር በሽታም ሞትም ቢሆን ሓዘንም ቢሆን ወደሌለባቸው ቦታቸው ይገባሉ ። እግዚአብሔር ከሊቃነ መላዕክት ሩፋኤል ሠራዊት መርጦ በመንበሩ ዙርያ አቆማቸው ፣ ከእሳት ወርቅ የተሰራ ጽናዎችምና የሚያንጸባርቅ የብርሃን አክሊል አንጓቸው ብርሃን የሆነ ዘንግንም ሰጣቸው ። መልኩ መብረቅ የሆነ የክህነት ልብስን አለበሳቸው ። ከማዕጠንታቸውም ምስጋና የተሞላ መዓዛውም ደስ የሚያሰኝ ዕጣን ይወጣል ፣ እግዚአብሔርም በማዕጠንታችሁ የቅዱሳን ሁሉ ጸሎት ወደኔ ይቀርብ ዘንድ ይደረግላችሁ አላቸው ። አዎ ወደ ፈጣሪያቸውን እግዚአብሔርም ሳያቋርጡ ዘወትር ስለሰው ልጆች ይለምናሉ ፣ በሰማያት የሚኖር የአብም ገጽ ዘወትር ያያሉ ፣ ንስሐ ስለሚገባው አንድ ሓጥእም በእግዚአብሔር መላዕክት ታላቅ ደስታ ይደረጋል ፣ እግዚአብሔር ቅዱሳን መላዕክት ሁሉ ስለዚህ ነገር ፈጥራችኋል ። አዎ ከእግዚአብሔር በስተቀር የመላዕክትን ተፈጥሮ የሚያውቅ ማንም ማንም የለም ። ኩፋሌ 2:7
ቅዱስ ሩፋኤል ቅዱሳን ጻድቃን በገድላቸውም የሚረዳቸው ፣ የምያጽናናቸው ፣ የሚደግፋቸው እርሱ ነው ፣ ፈታሄ ማህጸን ፣ ዐቃቤ ሆህት ፣ ሰዳዴ አጋንንት ፣ ከሣቴ ዕውራን ፣ ፈዋሴ ዱያን ተብሎ በመሆኑ ይታወቃል ።
ሄኖክ 6:3 ዘፍ 3:24
🌹❤️የቅዱስ ሩፋኤል በረከት ፣ የዕልፊ አዕላፍ ነገደ መላዕክት ረድኤት ፣ አማላጅነት ፣ የእግዚአብሄር በጎ ቸርነትና ምህረት ዛሬም ዘወትርም ከኛ ጋር ይሁን 🙏አሜን አሜን አሜን🙏🙏🙏
ወስብሃት ለእግዚአብሄር ።
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
💓💖❤️💙💜💚💖❤️💙
https://t.me/Orthodoxtewahdoc